በጎንደር የታክሲ አሽከርካሪዎች የሥራ ማቆም አድማ መተው ዋሉ

(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር ከተማ የሚገኙ የታክሲ አሽከርካሪዎች ዛሬ የሥራ ማቆም አድማ አድርገው በአደባባይ የመኪናቸውን ጡሩምባ ሲያሰሙ መዋላቸው ተሰማ።

የከተማ የታክሲ አሽከርካሪዎች ለሥራ ማቆም እና ለተቃውሞ ያነሳሳቸው ዋናው ምክኒያት “አዲሱን የትራፊክ የቅጣት ደንብ በመቃወም” እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት በጎንደር አዲስ የወጣው የትራፊክ ቅጣት ደምብ ለተከታታይ 3 ጊዜያት ቅጣት የተጣለበት አሽከርካሪ ለ6 ወራት እንዳያሽከረክር የሚከለክል ሲሆን የታክሲ ሹፌሮቹ ሙሉ ቀን ስንነዳ እንደመዋላችን ከዚያ በላይ ጥፋት ሊሰራ ይችላል በሚል ቅጣቱን ተገቢ አይደለም ሲሉ ለተቃውሞ ሥራቸውን አቁመው ውለዋል። በተጨማሪም የታክሲ ባለንብረቶች የታሪፍ ማስተካከያ አልተደረልንም በሚል ከነዚሁ አሽክርካሪዎች ጋር የሥራማቆም አድማውን መቀላቀላቸውም ተሰምቷል።

አድማው እስከማምሻውን ድረስ ቀጥሎ እንደነበር የገለጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች የከተማው አስተዳደር አድማ የመቱት አሽከርካሪዎች ተወካይ ልከው እንነጋገር ቢልም፤ ሹፌሮቹ “መንግስት የሕዝብ ተወካዮችን በማሰር የታወቀ ነውና ተወካይ አንልክም” ማለታቸውም ተሰምቷል ሲሉ ዘግበዋል።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሆነ የመጓጓዣ እጥረት ችግር ያለ ሲሆን የታክሲ ሾፌሮቹ አድማ በሕዝቡ የ ዕለት ተ ዕለት ተግባር ላይ ተጸእኖ አሳድሮ ውሏል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s