የጅቡቲ መስመር የከባድ መኪና ሹፌሮች በስራ ባልደረባቸው ግድያ ምክንያት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተሰማ።

 

አድማው የተደረገው በከባድ መኪና ሾፌሮች ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ እንዲቆም ለመጠየቅ መሆኑን በቦታው የሚገኙ የከባድ መኪና ሾፌሮች ለድሬቲዩብ ተናግረዋል።

በአካባቢው ዘረፋ እና ግድያ እየተበራከተ እንደመጣ የሚገልጹት አድመኖቹ ቅዳሜ የካቲት 22 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ ሰባት ሰዓት አካባቢ አንድ የከባድ መኪና አሽከርካሪ ከገዋኔ ከተማ 4 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመትቶ ከተገደለ እና በስለት በአሰቃቂ ሁኔታ ተወጋግቶ ከተገኘ በኋላ መኪናዎቻቸውን በማቆም መፍትሄ ለመጠየቅ መገደዳቸውን ነው የሚገልጹት።

ከእንድፎ ከተማ እስከ ገዋኔ በሚደርሰው 40 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ተሰልፈው የሚገኙት እነዚሁ ከአዲስ አበባ ጅቡቲ እንዲሁም ከጅቡቲ አዲስ አበባ በመሄድ ላይ የነበሩ ከባድ መኪኖች ላለፉት ሶስት ቀናት ከክልሉ አስተዳደርም ይሁን አፌደራል መንግስት ጥያቄያቸውን ሊቀበል ያቻለ አካል እንደሌለ ጠቁመዋል።

«ግመል በሚገጭበት ወቅት ለሳምንታት በእስር እንግልት የሚደርስብን ቢሆንም በተደጋጋሚ በቦታው እየተፈጸመ ያለው ግድያን ግን መንግስት ችላ ማለቱ ተገቢ አይደለም» በማለት ምሬታቸውን ገልጸዋል።

የፌደራል ፖሊሶችም በሰላም መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ምግብ እና ውሃ እንዳናገኝ በማድረግ ጥያቄያችንን እንዳናቀርብ እያደረጉ ነው የሚሉት እነዚሁ ሹፍሮች የስራ ቦታ ደህንነት እና የወደፊት ህይወታችን ማረጋገጫ የለውም ይላለሉ።

ከዚህ በተጨማሪ አአንዳንድ የጭነት መኪናዎች ውስጥ እንስሳትን እና ሌሎች ቶሎ ወደ አዲስ አበባ ሊደርሱ የሚገባቸውን እቃዎች የያዙ መኪኖች እንዳሉ ጠቁመወ ጉዳዩ ቶሎ መፍትሄ ካልተሠጠው እንስሳዎቹ ሊሞቱ እና የወጪ ገቢ ንግዱን በከፍተኛ ሁኔታ ሊጎዳ እንደሚችል ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም መንገዱ አድማ በመቱት ሹፌሮች እና መኪኖቻቸው የተነሳ በገዋኔ በኩል ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የሚወስደው መንገድ እንደተዘጋ ተገልጿል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s