በዳላስ ቴክሳስ በደረሰ የባቡርና የመኪና ግጭት አንዲት ኢትዮጵያዊት ወጣት መሞቷ ተነገረ፡፡

ባለፈው ቅዳሜ በባቡርና መኪና መተላለፊያ ቦታ ላይ የተገጨውን መኪና ስታሽከረክር የነበረችው እድሜዋ በሀያዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ሜላት ማሞ በግጭቱ ስትሞት ባቡሩ ወስጥ የነበሩ 4 ሰዎችም መጎዳታቸው ተጠቅሷል፡፡

ባቡሩ መኪናውን በአሽከርካሪዋ በኩል የገጨ ሲሆን መኪናው ውስጥ ሌላ ሰው እንዳልነበረ ታውቋል፡፡

ሜላት የምታሽከረክረው መኪና ወደ መተላለፊያው የገባው ተሽከርካሪዎችን የሚያግደው የብረት ዘንግ እየወረደ ባለበት ወቅት እንደሆነና ከዚህ በፊት 20 ሰከንዶች ቀደም ብሎ የማስጠንቀቂያ መብራትና ደወል ይሰማ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡
አደጋው በደረሰበት ወቅት ግን የማስጠንቀቂያው መብራትና ደወሉ ይሰማ አይሰማ የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡ የባቡር ድርጅቱ ባለስልጣናት የአደጋው መንስኤ ይጣራል ብለዋል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s