በንፋስ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከ60 በላይ ቤቶችና ድርጅቶች ይፍረሱ መባሉ ጭቅጭቅ ማስነሳቱ ተገለጸ፡፡በንፋስ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ከለቡ አካባቢ ተነስቶ በቱሉ ዲምቱ አድርጎ አዳማ ድረስ ይሠራል በተባለው መንገድ ምክንያት፣ በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ ከ60 የሚበልጡ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶች እንደሚፈርሱ በመገለጹ፣ ነዋሪዎችና ክፍለ ከተማው እየተወዛገቡ መሆናቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

ጋዜጣው ነዋሪዎቹን ጠቅሶ እንደዘገበው የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ተቋማትን ለመገንባት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጥያቄ ያቀረቡት በ1994 ዓ.ም. ሲሆን ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ በ1997 ዓ.ም. አሁን ‹‹ይፈርሳል›› የተባለው ቦታ የአካባቢውን የልማት ዕቅድ በጠበቀ ሁኔታ ስለተሰጣቸው፣ ከባለአንድ እስከ ባለአራት ፎቅ የሚደርሱ ከ60 በላይ የመኖሪያና የንግድ ድርጅቶች ሕንፃዎችን ገንብተው እየኖሩና እየሠሩበት እንደሚገኙ ገልጿል፡፡

ለቡ አደባባይ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ እንደሚገኙና እስከ 500 የሚደርሱ ቤተሰቦችና ሠራተኞች እንዳሏቸው የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፣ ‹‹መንገድ የሚያልፍበት ነው›› በሚል በኑሮ ውድነት ተበድረውና ያላቸውን ጥሪት ጨርሰው የገነቡትን ቤት ማፍረስ ተገቢ አለመሆኑን መግለጻቸውም ተዘግቧል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s