የሁለት ሰው ህይወት ያጠፋው ከባድ የመኪና አደጋ በአዲስ አበባ


በትላንትናው ዕለት ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ በቦሌ መንገድ ወሎ ሰፈር በደረሰ አሰቃቂ የመኪና አደጋ ሁለት ሰዎች ወዲያው ሲሞቱ ሁለቱ ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ ደረሰባቸው፡፡

ሁለቱ ሟቾች በዱባይ መርከበኞች እንደሆኑ ሲታወቅ ቀላል የመቁሰል አደጋ የደረሰባት ወጣት በሐያት ሆስፒታል ህክምና ተደርጎላታል ዛሬ ረፋድ ላይ ወደ ቤቷ መሄዷን ተሰምቷል፡፡

በስካር መንፈስ በከፍተኛ ፍጥነት ሲሽከረከር የነበረው መኪና ፍጥነቱን መቆጣጠር ተስኖት በርካታ ጊዜ ተገለቧብጦ በመውደቁ የመኪናዋን ተሳፋሪዎችና አሽከርካሪውን ለማውጣት ከአንድ ሰዓት በላይ የፈጀ ርብርብ ነበር የጠየቀው።

ተገልብጣ በተጨራመተችው መኪና ውስጥ የነበሩትን ለማውጣት የሚረዱ ቁሳቁሶች ባለመኖራቸው ሊተርፍ የሚችል ህይወት እንደጠፋም በቦታው የነበረ የአይን እማኝ ተናግሯል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s