የኢትዮጵያ ብሄራዊ የጋዜጠኞች ህብረትን አስጠነቀቀ።

በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ፎረም የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተውብኛል ያላቸውን የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር፣ የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበርንና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የጋዜጠኞች ህብረትን አስጠነቀቀ።
የፎረሙ ፕሬዝዳንት የሆነው በትረ ያዕቆብ እንደተናገረው ሁሉም ማህበራት የጋዜጠኞችን መብት ለማስጠበቅ መቆም እንጂ እርስ በርስ መፎካከርና ስም ማጥፋት ተገቢ አይደለም።

ፎረሙ የተጠቀሱት የጋዜጠኛ ማህበራት መሪዎች በተለያዩ ሚዲያዎች የፎረሙን ስም በማጥፋት ተጠምደዋል ሲል የሦስቱ የጋዜጠኛ ማህበራት መሪዎች በበኩላቸው ደግሞ ፎረሙ አዲስ አበባ ውስጥ ካሉ የምዕራባውያን ኤምባሲዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ሀገሪቱን የመበጥበጥ አላማ አለው ማለታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

ከሦስቱ የጋዜጠኞች ማህበራት የተሰነዘረበትን ክስ አስመልክቶ የፎረሙ ፕሬዝዳንት የተባለውን ክስ የሚያረጋግጥ መረጃ ካላቸው ማቅረብ ይችላሉ ማለቱንና የጋዜጠኞችን መብት በማስከበር ረገድ ከየትኛውም አካል ጋር ለመስራት ዝግጁ እንደሆነ ጠቅሷል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s