ከሳዑዲ ተመላሾች ወደ ሀገር ቤት ከሚያስገቧቸው እቃዎች ጋር ተያይዞ ቅሬታ እያሰሙ ነው ተባለ፡፡


ከሳዑዲ አረቢያ የተመለሱ ኢትየጵያውያን ወደ ሀገር ያላስገቧቸውን እቃዎች ሰሞኑን እንዲረከቡ እየተደረገ ቢሆንም ተመላሾቹ አንዳንድ ቅሬታዎችን እያሰሙ ነው ተብሏል።

ተመላሾቹ ልባሽ ጨርቅ መውሰድ አትችሉም መባላችንና ፥ ለቴሌዚዥንና ሌሎች የቤት እቃዎችም ቀረጥ መጠየቃቸን ተገቢ አይደለም የሚል ቅሬታዎችን አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ኤርፖርቶች ጉምሩክ ቅንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሩ ጌትነት፤ የተለያየ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ ፍሪጅና የተጋነነ ዋጋ ያላቸው እቃዎችን በተመላሾቹ ስም በማምጣት ህገወጥ ነጋዴዎች በአቋራጭ ለመክበር እየሞከሩ በመሆኑ ችግር ተፈጠሯል ነው ያሉት።
ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ግን መንግስት ባደረገው ጥረት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተመላሾች እቃቸውን እየወሰዱ መሆኑን ተናግረዋል።

በጉምሩክ አሰራር ማንኛውም ሰው ልባሽ ጨርቅም ቢሆን ባለቤቱ ወደ ሀገሩ ሲመጣ የማስገባት መብት ነበረው፤ ይሁንና ተመላሾቹ እነሱና አሁን እየመጣ ያለው እቃ ተለያይቶና ለወራትም ቆይቶ የመጣ በመሆኑ ይህ ሁኔታ ለኮንድሮባንዲስቶች ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ነው የጠቆሙት።

ስራ አስኪያጁ ፥ ልባሽ ጨርቆቹ የተመላሾቹ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ ለባለቤቶቹ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል ለቴሌቪዥን ፣ ለኤሌትሪክ ምድጃና ለሌሎችም እቃዎች ቀረጥ መጠየቁ ተገቢ ነው ፥ ሆኖም ተመላሽ መሆናቸውን እያረጋገጥን ቀረጥ ሳይከፍሉ እንዲወስዱ እያደረግን ነው ፤ ነገር ግን ተመላሾቹ የተጠቀሙባቸውን እቃዎች እንዲያስገቡ ቢፈቀድም አሁን በተመላሾቹ ስም ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ ያሉት የኤሌትሪክ እቃዎች እስከ 50 ሺህ ብር የሚያወጡና የተጋነነ ዋጋ ያላቸው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ችግሮች መፈጠራቸውን ተናግረዋል።

የተመላሾቹ እቃ ከቀን ቀን እየመጨረ በመሆኑ አሰራራችንን የበለጠ ፈጣን በማድረግ ሳይጉላሉ እቃቸውን እንዲያገኙ እየሰራን ነው ብለዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ፥ እቃችሁን ውሰዱ ተብለን ከተጠራን በኋላ እቃችሁ ጠፍቷል እየተባልን ነው ፤ በተሟላ መልኩ እቃችን ማግኘት አልቻንልም የሚል ቅሬታም አንሰተዋል። (ኤፍ.ቢ.ሲ)

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s