የአሩሲና አካባቢው ተወላጅ አማሮች አስቸኯይ መልእክት ለኢትዮጲያዊው!!

የአሩሲና አካባቢው ተወላጅ አማሮች አስቸኯይ መልእክት ለኢትዮጲያዊው!!! (መጋቢት 30፣ 2006 ዓ.ም.)

https://i2.wp.com/www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2014/04/454.jpgበአማራው አናት ላይ እያንዣበበ ያለውን የጅምላ እልቂት እንዴት ወገኖች ከመጤፍ እንዳልቆጠራችሁት ለኔ ትልቅ እንቆቅልሽ ነው የሆነብኝ። መቼም ኢትዮጲያዊያኖች ትልቅ የግንዛቤ ችግር ነው ያለብን። ከሰሞኑ በአሩሲ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች በተገኙበት የተመረቀው በተቆረጠ እጅ ላይ የተቀመጠ ጡት የሚያሳይ ሀውልት ከፍተኛና ምናልባትም በኛ ትውልድ ያልተስተዋለ ጎሳን መሠረት ላደረገ ፍጅት ብዙ እርምጃዎችን ያንደረደረን ድርጊት መሆኑን ምን ያህላችን ያስተዋልነው ጉዳይ እንደሆነ ሳሰላስለው ብዙዎቻችን እያስገመገመ ያለውን አርማጌደን አይቀሬነት አምነን የተቀበልን ያህል እንዲሰማኝ ሆኗል። በምረቃው ቦታ የመገኘት እድል የገጠማቸው የአካባቢው ተወላጅ አማሮች በስነስርዓቱ ላይ ስለተገኘው ግዙፍ መጠን የነበረው ታዳሚ እንዲህ ላለ ታላቅ ጥፋት መሳሪያ መሆን ታሪክ የማይረሳው እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ድርጊት መሆኑን ገልፀው አሳሳቢም ነው ብለዋል።

ታዳሚው ፊት ላይ ይነበብ የነበረውም የጥላቻ ውፍረትና የበቀልተኝነት ስሜት ስለተከታዩ ነገር አመላካች መሆኑን በሀዘን ገልፀዋል። እስከ አሁን ድረስም በኦነግ እና ኦህዴድ ጭፍን ብሄርተኛ ተከታዮች ዘንድ ሲሰበክ የነበረውን የአማራ ጎሳን ከኦሮሚያ የማፅዳት ውጥን የይለፍ ምልክት የሰጠ ድርጊት አድርገን እንቆጥረዋለን ብለዋል። አክለውም ሁኔታውን ተከትሎ ሀውልቱ በቆመበት አሩሲና አካባቢው እየተስተዋለ ያለው አንዳንድ አፍራሽ እንቅስቃሴ ይህን እምነታቸውን ምክንያታዊ እንደሚያደርገው ገልፀዋል። የዚህ ሴራ አንዱና ብቸኛው አላማ አማራውን ማስፈጀት መሆኑን ገልፀው ሀውልቱም ለዚህ በአማረው ላይ ለሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ህያው ማስጠየቂያ እንደሆነ አብራርተዋል። በህዝቡ መካከል ያለመቻቻልና የጥላቻ መንፈስ ስለሌለ እንዲቀሰቀስ የታሰበው የጎሳ ግጭት የመነሳት እድሉ ጠባብ ነው የሚለው የፖለቲከኞች አስተያየት የግል የፖለቲካ አጀንዳን ለመግፋት ሲባል በዜጎች ህይወት ላይ ቁማር መጫወት መሆኑን ገልፀው የፓለቲከኞቹን በንቃት እንሳተፍበታለን ስለሚሉት የሀገሪቱ ፖለቲካና በህዝቦች ተቻችሎ እና ተሳስቦ የመኖር በሀል ላይ ስላሳረፈው አፍራሽ ተፅዕኖ ያላቸውን ዝቅተኛ መረዳትም የሚያሳጣ ነው ብለዋል። ዛሬ ይህን ከአማራ የፀዳ ኦሮሚያን ስለመመስረት የሚያቀነቅኑ እንደ ኦነግ እና ኦህዴድ ያሉ ብሄርተኛ ድርጅቶች ተከታዮች የሆኑ፣ በዚህ አውዳሚ ፍልስፍና የሰከሩና ህሊናቸው የታወረ ፤ ከዚህ በፊት በአርባጉጉ በበደኖ ወዘተ የተፈፀመውን ዘግናኝ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት አይነት ለመፈፀም ወደሗላ የማይሉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ አክራሪ ብሄርተኞች መፈልፈላቸውን በማመላከት የዚህን የእልቂት ጥንስስ አውዳሚ መጨረሻ የተቀረው ኢትዮጲያዊ ተረድቶ በሰላማዊ ሰልፍና በመሳሰሉት የእሪታ ድምፁን በአስቸኯይ እንዲያሰማላቸው ጠይቀዋል። ካራ ተስሎብን ወደ ምታችን የምንነዳ በሚሊዮን የምንቆጠር ዜጎች ፖለቲካው ውስጥ በሚርመሠመሡ ጉዶች ጉዳያችን እንዲህ አትኩሮት መነፈጉ የጉዳዩ ብቻ ሳይሆን የመፍትሄውም ብቸኛ ባለቤቶች የመሆናችንን መሪር ሀቅ የጋተን አጋጣሚ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል። አያይዘውም ኢትዮጲያዊው ወገን ለጥያቄያቸው ባፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የማይችል ከሆነ ግን እነሱ የሚቻላቸውን እንደሚያደርጉና አካባቢውን በጅምላ ከመልቀቅ ጀምሮ የተቀረው የአማራ ተወላጅም አካባቢውን በመልቀቅ የራሱንና የልጆቹን ህይወት እንዲታደግ ሰፊ ቅስቀሳ ውስጥ እንደሚሰማሩም አሳስበዋል።

አምደፂዮን ዘተጉለት፤ ከአሩሲ ነገሌ

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s