ክብርነቶ በተናገሩበት ሳመንት?

 

ሰኞ መያዚያ 13 2006 ባሌ ውስጥ የሁለት ንፁሀን ዜጎችን መገደል በመስማት ሳምንቱን ጀመርነው። አገዳደላቸው ወንጀላችሁን ከባድ ያደርገዋል። የመጀመርያው ልጅ በቁጥጥራችሁ ስር ነበር። በህግ አግባብ መጠየቅ ስትችሉ ነው በነጻ እርምጃ የገደላችሁት። አፉ ውስጥ ሽገጥ አስገብታችሁ ተኩሳችሁ። በሚቀጥለው ቀን ይህን ግፍ ዜጎች ስለተቃወሙ ሌላ ዜጋ ደግሞ በቀን ብረሀን ገደላችሗል።

ማክሰኞ መያዝያ 14 2006 አፋር ውስጥ አስር ንፁሀን ተገለዋል። ከቦታው ያንድ እህት ምስክርነት።” እኔ አራሴ የቆምኩት ስምንት እሬሳ ላይ ነው። ይህ የመጀመርያ አይደለም። በየቀኑ አምስት ልጅ፤ ስድስት ልጅ፤ ሰባት ልጅ፤ ስምንት ልጆች እየቀበርን ነው። ገዳዬች ፌደራል ፖሊሶች ናቸው። እጅግ ለጆሮ በሚከብድና በሚያሳዝን ሁኔታ ልጆ መገደሉ ሳያንስ ነብሰ ጡር እህትም በጽኑ ተጎድታለች። ይህቺ እህታችን ሳትሞትም አልቀረችም’”። በዚሁ ቀን ጋንቤላ ዲማ ላይ መከላከያ ሰራዊት አባለት አስገድደን ፍቶወት ካልፈጸምን ብለው ባስነሱት አንባጓሮ ከመከላከያ ሶስት ከፌደራል አንድ ሞተዋል። “ጋዜጠኛ መሳይ ዝሆኖች ሲጣሉ” ብሎ እንደገለጸው ይህ ገጠመኝ ቁጥሩ ከራት በላይ የሆኑ ንፁሀን ዜጎች ሂወት ያለአግባብ እንዲጠፋ አድርጓል ። ህጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚታገሉት ድርጅቶች ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲ አስራ ስምንት አባላቱ ምንም ወንጀል ሳይሰሩ በዚሁ እለት ታስረውበታል። የአገሪቷ ህግ ተቃውሞ ለማድረግ ፍቃድ የማያሻ መሆኑን ቢደነግግም በዚሁ እለት አንድነት ፍቃድ ከለከልንህ ብላችሁታል።

እሮብ መያዝያ 15 ካመት በፊት ዴሬደዋ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ በተያያዘ የታሰረ ዳንኤል ጎሳ የሚባል ዜጋ አሰቃይታችሁ ገድላችሗል። ይህ ወገን ደብደባ ሲፈፀምበት ነበር። ለእሬሳ ምርመራ ፖሊስ ከቤተሰቡ ጋር ወደ አዲስ አበባ ተልኳል። የተላከው ፖሊስ ገዳዩ እራሱ አለመሆኑ የታወቀ ነገር የለም። የሬሳ ምርመራው አምስት ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ተጠናቋል። ሐኪምቤቱ የሬሳ ምርመራ ውጤት ቅጂውን እንኳ ለቤተሰቡ አልሰጥም ነው ያለው። ባንፃሩ አባት አበበ ጎሳ ልጄን ገድሏል ብለው ከጠረጠሩት አካል ነው የምርመራውን ውጤት ያገኛሉ የተባሉት። አቶ አበበ ያላቸው አንድ ልጅ ብቻ ነው። እሱኑ ነው የገደላችሁባቸው። ልጅ የሙት ልጅ ነው። አባት በወንድ አቅማቸው ብቻቸውን ሆነውና መከራ አይተው ያሳደጉት መሆኑን ተናግረዋል። እናንተ እንዳላችሁት እራሱንም ያጥፋ ወይ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ይገደል በናንተ እጅ እያለ ስለሞተ መንግስቶት ተጠያቂነት አለበት።

ሐሙስ መያዚያ 16 ጎንደር ጪንጋ ላይ ዜጎች ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ የመብት ጥያቄ ማንሳት ከጀመሩ ቀናቶች ተቆጥረዋል። ይህን ምክንያት አድርጋችሁ አራት ዜጎችን ገድላችሗል። እንዲሁ አንድ ፖሊስ ሞታል ሌላ ቆስሏል። ነዋሪው ተቃውሞ ሲያሰማ የነበረው መሳርያ ሳይዝ ስለነበር ህዝብ ፖሊሶቹ እርስ በእራሳቸው ተጋዳድለዋል እያለ ነው። እነዚህ ፖሊሶች የሞቱትም ሆነ የቆሰሉት በየትኛውም መንገድ ይሁን ወናው ጉዳይ እናንተ በተሸነፋችሁ ጊዜ ወይ ከዛም በሗላ አልቻልንም ብላችሁ ስልጣን ስላለቃቅችሁና ሁሌም ችግሮችን ሁሉ በምትፈቱበት የሀይልና ግጭት ያለበት መንገደ ምክንያት ስለሆነ አሁንም ለነዚህም ዜጎች ሞትም በቀጥታ ተጠያቂ ናችሁ። በዚሁ እለት የቆሰሉት ዜጎች ብዙ መሆናቸውና ባህር ዳር ሆስቢታል ልህክምና መግባታቸውን ሰምተናል። አስራ ስድስት ተጨማሪ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ማታሰራቸውንም በዚህ ቀን ነው የሰማነው።

አርብ መያዚያ 17 የሰላማዊ ፓርቲ ሰላሳሶት አባላት ሊቀመንበሩን ጨምሮ መታሰራቸውን ሰምተናል። እነዚህ ዜጎች ያለምንም ጥፋት የታሰሩት ለሰላማዊ ሰልፍ ህዘብን ሲቀሰቀሱ በነበረበት ጊዜ ነው። የጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው ዘግናኝና ልታፍሩበት የሚገባ ግብራችሁን የሰማንበትም ቀን ነው። የዞን ዘጠኝ ስድስት አባላትም መታሰራቸውን የሰማነው በዚሁ ሳምንት ነው። መብራት አገልግሎት ለረጅም ጊዜ እያገኘን አይደለም ያሉ የሽሮ ሜዳ አካባቢ ነዋሪዎችን አፍሳችሁ አስራችሗል።

ቅዳሜና እሁድ ዜና ሰለሌ ነው እንጂ ግድያው፤ እስሩ፤ ማንገላታቱ ይኖራል። ግፋችሁን በማጋለጥ እንኳ እኩል ልንራመድ አልቻልንም። ጨርሼ ሳለቀው ሌላኛው ሰኞ መጥቶ ይህም ሳምንት እንዲሁ በመገደል በማሰር በማሸበር መጀመሩን እየሰማው ነው። በቀጣይ ያንድነት ሰላማዊ ተቃውሞ አለ። የስልምና እምንት ተከታይ ወንድሞቻችን ጥያቄያቸውን ለማስመለስ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አለ። አስተዳድራችሁ አድሏዊ ሆኖ እያለ አዲስ አበባን እናስፋፋለን በሚል ደሀ ዜጎችን ከመሬታቸው ለማፈናቀልና ለማኝ ለማድርግ የዘየዳችሁት እቅድ መረረ ተቃውሞ ከዜጎች እየስነሳ ነው። ጎንደር፤ ጋንቤላ ባጠቃላይ በመላ አገሪቱ የለውጥ ፍላጎት እየተንቀለቀለ ነው። ሰንቱን ገድላችሁ፤ ስንቱን አስራችሁና አሰቃይታችሁ እንደምትወጡት የምናየው ይሆናል።

ይህን እንዳስብ ያደረገኝ ሰባቱንም ቀን በየቀኑ በግፍ ስለተገደሉ እንሰማባቸው የነበሩ ሳምንታት እጅግ ብዙ መሆናቸውን ስለታዘብኩ ነው። በሳምንት አምስቴ፤ ሶስቴ ወይ አንዴ መስማት የተለመደ ነው። የታሰረውን፤ ግፍና ስቃይ የተፈፀመበትን ወይ ያሰደዳችሁትን ዜጋ ጨምረን እንይ ካልን ይህን አይነቱ ወንጀል ሳይፈፀምና እኛም ሳንሰማ ያሳለፍነው ቀን ማግኘት አይቻልም። ይህ እንግዲህ የመገናኛ ሽፋን ለማግኘት የቻለው ብቻ ተወስዶ ነው።

በእርግጥ ንፁሀን ዜጎችን መግደል ማሰር ማሰቃየት ማሰደድ ትግል ላይ እያሉም ያለቆቾ ዋና ሞያቸው እንደነበረ ብዙዎች መስከረዋል። ሚኒልክ ቤተ መንግስት ከገባችሁ ሀያ ሶስትኛ አመታችሁ ላይ ናችሁ። ታዲያ ከሀያ ሶስት አመት በሗላ ዛሬስ ነጻ እርምጃን ማቆም ቻላችሁ ወይ ነው ጥያቄው?። የለመግባባቶችን፤ ልዩነትን ሳትገድሉን ዜጋውን ሳታሸብሩ መፍታት ትችላላችሁ ወይ ነው ጥያቄው?። ከላይ እንዳዩትና ልትክዱት የማያችላችሁ ይህ ችግር ከአመት አመት የሚጨምር እንጂ የሚቀንስ በጭራሽ አልሆነም። ስለዚህ መልሱ ባጭሩ አልቻላችሁም ነው። በእርግጥም ይህን የሀያሁለት አመት እብደት ላየ መግደልና ግፍ መፈፀም እንዳትችሉ እስክናደርጋችሁ ወንጀላችሁ አይቆምም ብሎ ድምዳሜ ዜጋው ላይ ባይደርስ ሲፈጥረው ጅላንፎ ሆኖ ነው ማለት ይቻላል። እርሶ እራሶ ዘላለማዊ ከብርና ሞገስ ብለው ማሀላ ፈፅመው ስልጣን ከያዙ በሗላ እንኳ ብዙ ንፅሀን ዜጎች በነጻ እርምጃ ተገለዋል። ያለጥፋታቸው ዜጎች በገፍ እየታሰሩና ስቃይ እየተፈፀመባቸው ነው። የታዘለች ህፃንም አልቀረላትም። ይህን አይነት መንግስታዊ ሽብር በሚፈፀምበት አገር ለአፍ ካልሆነ ፖለቲካ ማህደሩ ስፍቷልም ጠቧልም ብሎ መከራከር ልብ ድክም ማድረግ ነው።

በጠቅላላው የስልጣን ዘመናችሁ የፈፀማችሁት ፍጅት ቢወዳደር ከደርጉ የሚብስ ይመስለኛል። ምክንያቱም በዚህ ደረጃና በማያባራ ሁኔታ በየቀኑ በግፍ ስለሚገደሉ ስለሚታሰሩ ሰቆቃ ስለሚፈፀምባቸው ንፁሀን ዜጎች በኔ እድሜ ያኔ አይሰማም ነበር። በርግጠኛነት ግን እስቲ ቦንብ አፈንድተን ሀያ ሰላሳ ሰው እንግደልና የዜጋውን ስሜት እናጥና ወይ ፖለቲካ እንስራበት ብለው ፍጅት የሚፈፅሙ መሪዎች አልነበሩም።” ጦርነት ሰርተን” የምትባለው አለቆቾ የሚወዷት የጫወታ አይነትን ማለቴ ነው።

ደርጉም አንባገነን ስርአት ስለነበር ሰፈራ የመሳሰሉ ግብታዊና ጎጂ እቅዶችን ተግባራዊ አድርጓል። ዜጎች ያልተስማሙባቸውና አምርረው የተቃወሟቸው ቢሆንም እንደናንተ ያጉረመረመውን ሁሉ በገፍ መግደል ወና የቅዱ ማስፈፀሚያ ግን አልነበረም። ሰበብ አይሁን ለማለት ነው። ህንፃ ለመግንባት፤ መንገድ ለመስራት፤ አበባ ለመትከል የንፁሀን ሂወት እስርና ስቃይ የግንባታዎቹ ሁሉ መሰረቱ እኮ ነው የሆነው። ይህ የባህሪያችሁ ከመሆኑም በተጨማሪ ሁላችሁም ጋር ከፍተኛ የማስተዳደር እውቀት አለ ማለት ብቻ ነው የሚቻልው።

ክብር የሆነው ለሰው ልጅ ሂወት የሚሰጠው ዋጋ ከፍተኛ በነበረበት ዘመን ዜጎች ግዛው ለምን ለምን ሞተ? ማርታ ለምን ለምን ሞተች ብለው ጉሮሮ ሊይዙ ይደርሱ እንደነበር ያውቃሉ። ዛሬ ከአንድ እስከ አስር ዝም ብሎ ዜናችን ነው። ለምን ተብሎ መጠየቅ አይደለም ገደሏቸው እኮ ተብሎም በቀጣይ አናወራበትም። ሀምሳ፤ መቶና ሶስት መቶ አዲስ ቁጥር አየደለም። ከዚህ በፊት አድርጋችሁታላ። ያዋጣል ካላችሁ ግን ለወደፊቱም በርቱ። ይህን በሚመስል እውነታ ውስጥ ጊዜና ሁኔታ ይመቻቻል። ያኔ ገደላችሁ አይደለም ገላመጣቸሁ የስልጣናችሁን ፍፃሜ እንደሚያደርገው እነግሮታለው። ማወቅ ያለቦት የተለወጠ ነገር የለም ያው ኢትዬጵያዊ ነው።

በግሌ ስልጣኑ የያዙ ለት ያደረጉትን ንግግሮትን ካዳመጥኩበት ጊዜ ጀምሮ ሁሌም ሳዮትም ሆነ ስሰማዎት አብሮአደጌን ሞዘዘኝን ነው የሚያስታወሱኝ። በዛኑ ሰሞን በፃፍኩት ፅሁፍ ስለዚሁ ጉዳይ ልነግሮት ነበር። ሰው ናቸው የሚሉ ሲበዙ አልቸኩል ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ተውኩት። ይህን ክፍል ጎርጄ በሌላ ገፅ ላይ አኖርኩት። ዛሬ ኮፒ ፔስት ነው ያደረኳት። በርግጥ ሰበአዊነት ያለበትና ልጆቼ ተቆጡኝ። ፀለይኩኝም የምትለዋ ቃለ መጠይቆት አጭበርብራኝለች።

ልጆች ሆነን ከልጅነቱ ጀምሮ የመጨረሻ ገንገበት የነበረ ልጅ ነበር። ለዚህ ልጅ የሆነ ጊዜ ላይ ይህን ባህሪውን ያየ ሌላኛው አብሮ አደጌ ሞዘዘኝ ብሎ የቅጥል ስም አወጣለት። ገንገበቶች ገገማ ስለሆኑ እንደተጠመቀበት ወይ እንደሰለጠኑበት ጉዳይ ነው ለመሀበረሰቡ ጠቃሚም ጎጂም የሚሆኑት። አክራሪ የእምነት ሰው፤ ወይ ገገማ ቀልደኛ፤ ጨካኝ መርማሪ ወይ ለእውነት የሚሞት ዳኛ ወይ የሚያናድድ ሊስትሮ ጠራጊ ሊሆኑ ይችላሉ። ሞዘዘኝ ከፍ ሲል የሰፈር የጠብ ቡድን አገኘው። ከዛ አንዷን ጡቷ ላይ በጩቤ ወጋት፤ እትዬ እንትናን በድንጋይ ፈነከታቸው። የዛን ሰፈር ልጅ በብረት ሰንሰለት ቀጠቀጠው። ብቻ ስሙ ባንዴ ዝነኛማ ተፈሪም ሆነ። የጠብ ቡድን ውስጥ ደግሞ ድርሻቸው ማካበድና ማሟቅ የሆነ አሉ። ሀይ ሀይ ስለበዛበት ሞዘዘኝ እስታ ሊል አልቻለም። ቆያይቶ ተገደለ።

እርሶን ሳይ ትግሬ ተጋዳላዮች ምርጥ መጠቀሚያ ነው ከመንጋው መዘው ያወጡት እላለው። ገንገበቶችን እንዲሞቃቸው በማድረግ ብቻ እንደፈለጉ ሊነዷቸው መቻላቸውን አውቀዋል። የዚህ አይነት ሰዎችን ምንም አይነት ወንጀል ማሰራት ቀላል ነው። የሚፈልገው ጎሽ አበጀህ፤ አቤት ድፍረት፤ ለርሶ ሲሆን ባለእራዩም እንዲህ ሊያሳምረው አይችልም ነበር። እስከዛሬም ተሳስተናል አይነት ሙገሳን መጨመር ነው። በርግጠኛነት ከበቀደሙ የፓርላማ ውሎዎ መልስ ብዙዎች ይህን አይነት አስተያየት ሰጥተዎታል። ከዋኖዎቹ ለዚሁ ጉዳይ ተደውሎሎታል። ሙገሳ ያለበት ተመሳሳይ ነገርን ብለዎታል። ለሁሉም መልክቴን ጠቅላይ ሚንስትሩ ሞዝዘውኛል። ብዬ አቆማለው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s