የኤርትራ ተቃዋሚ ቡድን በኤርትራ የጦር እዝ ላይ ጥቃት ፈጸመ

Thumb 1የኤርትራ የተቃዋሚ ቡድን ‹‹የቀይ ባህር አፋር ዲሞክራሲያዊ ድርጅት›› (RSADO) የኤርትራ መንግስት የደህንነት ሃይሎችን መግደሉን እና ማቁሰሉን አስታወቀ፡፡

የድርጅቱን ሃላፊ ኢብራሂም ሃሮንን ጠቅሶ ሱዳን ተሪቢዩን እንደዘገበው ከሆነ ድርጅቱ ጥቃቱን ያደረሰው በደቡባዊ ቀይ ባህር አልሃን ግዛት ውስጥ በሚገኝ የጦር ካምፕ ላይ ነው፡፡

የድርጅቱ መሪ በኤርትራ 15ተኛ ክፍለ ጦር ላይ ጥቃት በማድረስ 27 የደህንነት ሃይሎችን መግደላቸውን እና ሌሎች በርካቶችን ማቁሰላችን ገልጸዋል፡፡

የተቃዋሚ ድርጅቱ ሃላፊ አክለውም ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ለስምንት ሰዓታት ያህል የእዝ ማዘዣውን ተቆጣጥረው እንደቆዩና የተለያዩ አይነት እና መጠን ያላቸውን የጦር መሳሪያዎችንም መማረኩን የተናገሩ ሲሆን ጥቃት በሚከፍቱበት ወቅትም ማንም የኤርትራ የደህንነት ሃይል ሊዋጋቸው እንዳልቻለ ፤ ይልቁኑም ‹‹የእግሬ አውጭኝ ›› እርምጃ እንደወሰዱ የተናገሩ ሲሆን ይህ መሆኑ የኤርትራ መንግስት ጦር ምን ያህል የተዳከመ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

የኤርትራ መንግስት በኤርትራ የአፋር ህዝብ ላይ የሚያደርሰው ግድያ እና ጭቆና እየተባባሰ መምጣቱንም ተናግረዋል

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s