የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የግሉ ዘርፍ ያሉበትን ችግሮች አስመልክቶ በአገር ውስጥና በውጭ አማካሪዎች ያስጠናው ጥናት፣ ዘርፉ ከፍተኛ የገንዘብ አቅርቦት ችግር እንደገጠመው አመለከተ፡፡
ምክር ቤቱ የንግድ አሠራር ሥነ ምግባር መመርያ መጽሐፍ እያዘጋጀ መሆኑን፣ የሴቶችና የወጣቶች ንግድ ሥራን የሚያግዝ ክፍል ማቋቋሙንና ባለፉት ሁለት ዓመታት የተሠሩ ሥራዎችን አስመልክቶ ባዘጋጀው መድረክ፣ የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን እንደተናገሩት አገሪቱ ውስጥ በተጀመሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች፣ መሠረተ ልማቶች፣ በባንኮች አሠራርና በሌሎችም ምክንያቶች የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንቱን ለማስፋፋት የገንዘብ አቅርቦት ችግር ማነቆ ሆኖበታል፡፡
የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊና የአድቮኬሲ መምርያ ሥራ አስኪያጅ አቶ እንዳልካቸው ስሜ እንደገለጹት፣ ጥናቱ የሚያሳየው ባንኮች ብድር በሚጠየቁ ጊዜ በቂ የገንዘብ አቅርቦት እንደሌለ ነው፡፡
ባንኮች ሲያበድሩ ከእያንዳንዱ ብድር ላይ 27 በመቶ ቦንድ እንዲገዙ የሚያስገድድ አሠራር በመኖሩ ምክንያት፣ በኢኮኖሚው ውስጥ ለግሉ ዘርፍ የሚቀርበው ገንዘብ በቂ እንዳይሆን በማድረግ ተፅዕኖ መፍጠሩን ጥናቱ አሳይቷል፡፡
Advertisements