ኤሊያስ ገብሩ፣ የፕሬስ አዋጅ በላዩ ላይ የተናደበት ጋዜጠኛ

Elias Gebruአውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ) – ከወራት በፊት በዕንቁ መጽሄት በተስተናገደ አንድ መጣጥፍ ምክንያት ክስ እንደቀረበበት
በስልክ ተነግሮት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ እንዲቀርብ የታዘዘው ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ በጥሪው መሰረት ወደ ማዕከላዊ
ወንጀል ምርመራ አቅንቶ ቃሉን ቢሰጥም በፕሬስ አዋጁ መሰረት እስካሁን በዋስ የመለቀቅ መብቱ ሊከበርለት እንዳልቻለ
የመጽሄቱ አዘጋጆች ለአውራምባ ታይምስ ገለጹ፡፡
በጋዜጠኛ ኤሊያስ ላይ የተወሰደው ያልተለመደ እርምጃ እጅግ እንዳስገረማቸው በነጻው ፕሬስ ውስጥ የሚያገለግሉ በርካታ
ጋዜጠኞች አስተያየታቸውን እየሰጡ ሲሆን አውራምባ ታይምስ ያነጋገራቸው አንድ የህግ ባለሙያ በበኩላቸው በኢትዮጵያ
የፕሬስ አዋጅ መሰረት አንድ ጋዜጠኛ ለምርመራ ሲባል በእስር ላይ እንደማይቆይ በአዋጁ ላይ በግልጽ መደንገጉን
ያብራራሉ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት፣ በተለያዩ አለምአቀፍ የፕሬስ ነጻነትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ዘንድ ጋዜጠኞችን
በማሰርና በማዋከብ ቢብጠለጠልም ባለስልጣናቱ ግን ‹‹በጻፈው ጽሁፍ አሊያም በጋዜጠኝነቱ ምክንያት አንድም የታሰረ ሰው
የለም››f የሚል ምላሽ እስካሁን ሲሰጡ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን በዕንቁ መጽሄት ላይ በተስተናገደ አንድ መጣጥፍ
ምክንያት ክስ እንደቀረበበት በግልጽ ተነግሮት ለእስር ስለተዳረገው ኤሊያስ ገብሩ ግን እስካሁን የተሰጠ ይፋዊ ማብራሪያ
የለም፡፡
ነገር ግን ለመርማሪዎቹ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለአውራምባ ታይምስ እንደገለጹት በኦሮሚያ ዩኒቨርስቲዎች የተነሳውን
አመጽ ተከትሎ ሰሞኑን የኦህዴድ ባለስልጣናት ከአምቦ ነዋሪዎች ጋር በካሄዱት ስብሰባ፤ ቴዲ አፍሮ በዕንቁ መጽሄት
አማካኝነት ስለ አጼ ምኒልክ ሰጠ የተባለውን አወዛጋቢ አስተያየት መነሻ በማድረግ መንግስት በዕንቁ መጽሄት ላይ እርምጃ
እንዲወስድ የሚወተውቱ ተሰብሳቢዎች እንደነበሩ ገልጸው ይህንን ‹‹የህዝብ ጥያቄ››fለማብረድ ሲባል ጋዜጠኛ ኤሊያስ ዋጋ
እንዲከፍል መደረጉን ይገልጻሉ፡፡
የታሰሩ ጋዜጠኞችን በመጠየቅ ብሎም በህግ ጥበቃ ስር ያሉ ጋዜጠኞች መብት እንዲከበር ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ድምጹን
በማሰማት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ በቅርቡም በዚህ ድረገጽ በእስር ላይ ስለሚገኘው አብሮ አደግ ጓደኛው
ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ውብ መጣጥፍ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s