ካምፓላ፤ አሜሪካ በዩጋንዳ ፣ ለዜጎቿ የሽብር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ሰጠች

በካምፓላ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፣ በዓለም ዋንጫ የቴሌቭዥን ሥርጭት ወቅት ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል ስትል ዜጎቿን አስጠነቀቀች።በምሥራቅ አፍሪቃ በየቦታው ፤ በእስላማዊ አማጽያን ሲካሄድ  እንደቆየ የተነገረለት  የፈንጂ ጥቃት በዓለም ዋንጫ ውድድር ወቅት ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይችል ይሆንል የሚል ጥርጣሬ አለ። ኢትዮጵያና  ቡሩንዲም  የተባለው ጥቃት ሊሠነዘር እንደሚችል በማሰብ ዜጎቻቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። ከ 4 ዓመት በፊት ፤ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ሲካሄድ ካምፓkla ውስጥ ከአል ቃኢዳ ጋር ቁርኝት እንዳለው የሚነገርለት አሸባብ በ 2 የምግብ ቤቶች ባነጎደው ፈንጂ ቢያንስ አንድ የኣሜሪካን ዜጋ ጨምሮ በጠቅላላ ቁጥራቸው ከ 76  የማያንስ ሰዎች መገደላቸውን የኤምባሲው መግለጫ ያወሳል።  የጥቃቱ ዒላማዎች፤ ሆቴሎች፤ ምግብ ቤቶች፤ ዳንኪራ ቤቶች፤ የገበያ ማዕከላት ፣ የሃይማኖት ተቋማት ፣ የዲፕሎማቶች  ጽ/ቤቶች፤ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ወይም የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች  ሊሆኑ ይችላሉ ሲል ነው ማስጠንቀቂያው የዘረዘረው። በሶማልያ አሸባብን ለመውጋት  በዛ ያለ ጦር ሠራዊት የላከች ሀገር ዩጋንዳ መሆኗ ይታወቃል። የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የተጠቀሰውን ማስጠንቀቂያ ያቀረበው፤ የዩጋንዳ ፖሊስ ቃል አቀባይ ፍሬድ ኤናንጋ፤  በ 4 ተሽከርካሪዎች የተሣፈሩ አሸባብ አሸባሪዎች ከኬንያ ድንበር አቋርጠው ዩጋንዳ ስለመግባታቸው መረጃ አግኝተናል  ካሉ በኋላ ነው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s