በምስራቅ ጎጃም የመኢአድ አባል በካድሬዎች ድብደባ ሕይወታቸው አለፈ

newsፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው በምስራቅ ጎጃም በነማይ ወረዳ ደንጎሊማ ቀበሌ አቶ ሞሳ አዳነ የተባሉ የመኢአድ አባል ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን ከቤታቸው ወደ እስር ቤት መሄድ አለብህ በሚሉ የብአዴን ካድሬዎች ድብደባ ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ይህን ድርጊት የፈጸሙት ሁለት የብአዴን ካድሬዎች አቶ አዲሱ ጫኔና አቶ ብርሃኑ ታመነ ወደ መኖሪያቸው በመሄድ ወደ እስር ቤት ትሄዳህ በማለት ለማስገደድ ሲሞክሩ በተፈጠረ እሰጣገባ አቶ ሞሳ አዳነ ካድሬዎቹ በፈጸሙባቸው ከፍተኛ ድብደባ ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡ በተያያዘ ዜና በዚያው ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ የመኢአድ አባል አቶ ይበልጣል ወንድሜነህ ቤትህ መሣሪያ አለ በሚል ጥርጣሬ እያሳደዱዋቸው እንደሚገኙና እሳቸውም አካባቢያቸውን ጥለው እንደሸሹ የመኢአድ የሕ/ግንኙነት ኃላፊ ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገልጸዋል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s