የአንድነት የአዋሳ ሰልፍ “በእስር ተጀምሮ በእስር ተጠናቀቀ”

(ፖሊስ ትናንት የአንድነትን ሰልፍ እንዲበተን ያደረገው እንዲህ ከተማዋን በመውረር ነበር)

ሰኔ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል አንድነት ፓርቲ በአዋሳ ሊያካሂደው የነበረው ሰልፍ ፣ የሰልፉ አስተባባሪዎችና የፓርቲው የአመራር አባላት በመታሰራቸው ምክንያት ሳይካሄድ ቀረ።

ሰልፉ ከመካሄዱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በፓርቲው ቅስቀሳ የተደናገጡት የሚመስሉት የአዋሳ ባለስልጣኖችና ፖሊስ አባላት 37 የሚሆኑ በቅስቀሳ ላይ የተሰማሩ አመራሮችንና ደጋፊዎችን ይዘው በተለያዩ እስር ቤቶች አስረዋቸዋል።

በማግስቱ እስረኞችን ለመጠየቅና ስንቅ ለማቀበል ከሄዱት መካከልም አንዳንዶች መታሰራቸውን በስፍራው የሚገኘው የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ያሬድ አማረ ለኢሳት ገልጸዋል።

ከአዲስ አበባ የሄዱና የአዋሳ የፓርቲው አመራሮች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡና ክስ ሳይመሰረትባቸው በመታሰራቸው የረሀብ አድማ ያደረጉ ሲሆን፣ ዛሬ ሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን አቶ ያሬድ አክለው ተናግረዋል።

መድረክ በአዋሳ በከፍተኛ ወከባ ውስጥ ሆኖ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉ ይታወቃል። አንድነት ፓርቲ በተለያዩ ክልሎች እየዞረ በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት ሰላማዊ ሰልፎችን እያደረገ ነው። በአዋሳው ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሞ ወጣቶች ላይ የተወሰደው እርምጃ፣ የኑሮ ውድነት፣ ከማንነት ጋር በተያያዙ የሚታዩት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና የመሳሰሉት ጉዳዮች ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር።

አንድነት በአዋሳ ለሚያካሂደው የተቃውሞ ሰልፍ ለክልሉ መንግስት የእውቅና ደብዳቤ ያስገባው ከአንድ ወር በፊት ነበር። የከተማው ምክር ቤት እስካለፈው አርብ ድረስ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት እየተነጋገርነበት ነው በማለት ሲያጓትተው ቆይቷል።

አንድነት ፓርቲ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ “በተለየ ሁኔታ በደቡብ ክልል እየታየ ያለው መንግስታዊ አፈናና ጸረ ህግ አቋም እንዲገታ ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ብሎአል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s