የአንዳርጋቸው ጉዳይ በውጭ ሚዲያዎች ለምን ሳይዘገብ ቀረ? – (በመታሰራቸው ዙሪያ የኔ 3 ጥያቄዎች)

andargachew
ስታየሁ ከዋሽንግተን ዲሲ

በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ ትናንት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መንግስት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ታሰሩ የሚል ዜና ካነበብኩ በኋላ የተለያዩ ጥያቄዎች በጭንቅላቴ ላይ ተመላለሱ።

የመን በመንግስት አሰራር ደረጃ ከአፍሪካ ሃገራት የማትሻልና በሙስና የተጨማለቀ አሰራር ስላላት አቶ አንዳርጋቸው እንዴት ለትራንዚትም ቢሆንም መመረጣቸው ድፍረታቸውን ባደንቅም ውሳኔያቸው ገርሞኛል። ጫት በሚቅሙ የመንግስት ሃይሎች የምትመራው የመን በተለይም አቶ አንዳርጋቸውን በጫት ንግድ ልትለውጣቸው ትችላለች የሚለው የብዙዎች አስተሳሰብ ባይስበኝም እኔን የገረመኝ አቶ አንዳርጋቸውን የሚያህል ትልቅ የተቃዋሚ ድርጅት መሪ የመታሰር ዜና አንድ ሳምንት ሙሉ በሌሎች የውጭ ሚዲያዎች አለመዘገቡ ገርሞኛል።

ዜናውን ከዘ-ሐበሻ ካነበብኩ በኋላ በግንቦት 7 ድረገጽ፣ በኢሳት ዝርዝሩን ሰማሁ። ከዛም ወደ የመን ሚድያዎች ጋር በኢንተርኔት አሰሳ ጀመርኩ። ከዚህ በፊት የግድያ ሙከራ በአስመራ ሊደረግባቸው ታቅዶ ከሸፈባቸው ስለተባሉት አቶ አንዳርጋቸው አንዳችም ጉዳይ የሚያወራ ነገር አላየሁም። በአንዳችም ሚድያ ስለመታሰራቸው የተዘገበ ነገር አለመኖሩ ገርሞኛል።

በተለይም የእንግሊዝ ሃገር ፓስፖርት አላቸው የሚባሉት አቶ አንዳርጋቸው እውነት የእንግሊዝ ፓስፖርት ካላቸው እንዴት እንግሊዞች ዝም አሉ? አንድ ዜጋቸው እንዲህ ያለ መታፈን ውስጥ ሲወድቅ ሚዲያዎቻቸውም መንግስታቸውም እንዴት ዝም አለ?

የኤርትራ ባለስልጣናትም ዝም ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ያሉት ነገር የለም። ምንድን ነው ጉዱ? እንደሚባለው ግንቦት 7ና አለኝ የሚለው ኃይል ቀስ በቀስ ከአስመራ ለቆ ለመውጣት ካለው እቅድ ጋር በተያያዘ አቶ አንዳርጋቸው አንድ ነገር ደርሶባቸው ይሆን?

አልጀዚራን የመሳሰሉ ለኢትዮጵያ ጉዳይ ዜናዎች ቅርብ የሆኑ የሌላ ሀገር ሚዲያዎችስ ይህን ዜና አለመዘገባቸው የሚያሳዩን ነገሮች ምንድን ናቸው?

እስኪ ተወያዩበት።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s