የኢትዮጵያውያን ቀን በሳንሆዜ በደማቅ ስነ-ሥርዓት ተከበረ

(ዘ-ሐበሻ) እየተካሄደ ባለው 31ኛው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል አንዱ አካል የሆነው የኢትዮጵያውያን ቀን ዛሬ ጁላይ 4 ቀን 2014 ዓ.ም በደማቅ ስነስርዓት ተከበረ። በበዓሉ ላይ የኔልሰን ማንዴላ ጠባቂ የነበሩት ሻምበል ጉታ ዲንቃ በሕይወት ዘመናቸው ላደረጉት አስተዋጾ ተሸልመዋል።https://i1.wp.com/www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2014/07/esfana-san-jose-cali-1.jpg

በጣም ደማቅ በነበረው በዚህ በዓል ላይ ቅኝት የባህል ቡድን ሕዝቡን ቁጭ ብድግ ያደረገ የባህል ትር ኢቶችን ያሳየ ሲሆን በተጨማሪም ቴዎድሮስ ታደሰ፣ ፋሲል ደመወዝ፣ ጃኪ ጎሲ፣ ፋንትሽ በቀለና ሌሎችም ይህንን በዓል በከፍተኛ ሁኔታ ሲያደምቁት አምሽተዋል።

በሳንሆዜ እየተደረገ ባለው በ31ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌስቲቫል ላይ የተለያዩ ንግድ ድርጅቶች፣ የፖለቲካ ተቋማት፣ ምግብ የሚያቀርቡ፣ ጌጣጌጥና አልባሳት የሚሸጡ፣ የእስልምና፣ የኦርቶዶክስና የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችና ሌሎችም የራሳቸውን ድንኳን በመከራየት አላማቸውን እና ሥራዎቻቸውን ካለፈው እሁድ ጀምሮ ሲያስተዋውቁ የከረሙ ቢሆንም ከትላንት ሐሙስ ምሽት ጀምሮ ጥሩ ደንበኞችን ሲያስተናግዱ ቆይተዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s