የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የተጠረጠሩበትን የሽብርተኝነትን ክስ ተቃወሙ

  • 99

     

    Share

የኖርዌይ ዜግነት ያላቸው የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ ኡቻላ (ቅጽል ስም መኖሪያ ካዋናሞ)፣ ሦስት የደቡብ ሱዳን ዜጐችና አራት ኢትዮጵያውያን የተጠረጠሩበትን የሽብርተኝነት ክስ በመቃወም ለፍርድ ቤት ሰኔ 24 ቀን 2006 ዓ.ም. አቤቱታ አቀረቡ፡፡

Okello-Akway-foto-priviat-form-Dagbladet--300x169የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ፣ በተለይ አቶ ኦኬሎ ከ1996 ዓ.ም. እስከ 2000 ዓ.ም. ድረስ በጋምቤላ ክልልና ከኢትዮጵያ ውጪ ሆነው ፈጽመዋል የተባለው የወንጀል ድርጊት በሽብርተኝነት አዋጁ የሚሸፈን አለመሆኑን በማስረዳት ተቃውመዋል፡፡

የተቃወሙበትን ምክንያት አቶ ኦኬሎ ሲያስረዱ፣ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ ፀድቆ የወጣውና በሥራ ላይ የዋለው እሳቸው ባልነበሩበት ጊዜ በነሐሴ ወር 2001 ዓ.ም. ነው፡፡ በመሆኑም የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ ባልነበረበት ጊዜ የተፈጸመ ድርጊት በአዋጁ የሚሸፈን አለመሆኑን ጠቁመው ክሱ ሊሰረዝ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ የተጠቀሱትን የሽብር ወንጀል ለመፈጸም ማቀድ፣ ማሴር፣ መዘጋጀትና መሞከር እንዳለበት የሚደነግገውን ሁሉም ተጠርጣሪ ተከሳሾች የተዘረዘሩትን ለመፈጸም የሚገልጽ አለመሆኑን ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ማመልከቻ ያስረዳል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ይልቁንም የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ጋሕነን) ወይም በጋምቤላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋዴን) ውስጥ አባል ሆነው ይንቀሳቀሱ እንደነበር የዓቃቤ ሕግ ክስ የሚያስረዳ በመሆኑ፣ ክሱ ከወንጀል መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 112 ድንጋጌ ጋር የሚጋጭ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ በመሆኑም የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ 7(1)ን በመጥቀስ ክሱን በወንጀል መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 119 መሠረት ዓቃቤ ሕግ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ተጠርጣሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡

አቶ ኦኬሎ ከ1996 ዓ.ም. እስከ 2000 ዓ.ም. ድረስ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው መሥራታቸውን፣ በዚህ ወቅት በክልሉ ተፈጥሮ በነበረው ችግር ለተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃን የተዛቡና ወገንተኝነት የተሞላባቸው መግለጫዎችን መስጠታቸውን፣ በዚህም ምክንያት የብሔሩን ተወላጆች ለእልቂት ካነሳሱና ግጭቱን ካባባሱ በኋላ ከግል አጃቢያቸውና ከሾፌራቸው ጋር በመሆን አገር ከድተው መውጣታቸውን ጠቅሶ ዓቃቤ ሕግ ክስ አቅርቧል፡፡ አቶ ኦኬሎ ከአገር ከወጡ በኋላም ለኤርትራ ቴሌቪዥን፣ ለኦነግ ሬዲዮ፣ ለቢቢሲ፣ ለቪኦኤ፣ ለካናዳው ጋምቤላ ቱደይና ለሌሎችም መገናኛ ብዙኃን ግጭቱን የሚያባብሱ መግለጫዎች መስጠታቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ መጥቀሱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s