ለአዳማ ከተማ አዲስ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ ነው

-የ20/80 እና የ40/60 ኮንደሚኒየም ቤቶች ግንባታ ይጀመራል

daየአዳማ ከተማ አስተዳደር አዲስ ማስተር ፕላን በማዘጋጀት ላይ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ የአዳማ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ የሱፍ ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንደገለጹት፣ መስተዳደሩ የከተማዋን ዕድገት ያገናዘበ አዲስ

ማስተር ፕላን በማዘጋጀት ላይ ነው፡፡ አዲሱ ማስተር ፕላን የመኖሪያ ክልሎች፣ የንግድ ማዕከላትና የኢንዱስትሪ ዞኖችን ያካተተ እንደሆነ የገለጹት አቶ አህመድ፣ የኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግና የዓለም ባንክ ደግሞ ለፕሮጀክቱ ወጪ የሚውል ገንዘብ እንደሚያቀርብ አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የአዳማ ከተማና የአሜሪካ ዴንቨር ከተማ በተለያዩ ዘርፎች ለመተባበር የሚያስችላቸውን የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ለመፈራረም በሒደት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ አዲሱ የከተማ ማስተር ፕላን አዳማን ከዓለም አቀፍ ከተሞች ጋር የሚያስተካክላት እንደሆነ አክለው ገልጸዋል፡፡

የአዳማ ከተማ የኢትዮ፣ ጂቡቲ የባቡር መስመር ግንባታ ተከትሎ በ1908 ዓ.ም. የተቆረቆረች ነች፡፡ ‹‹የስምጥ ሸለቆዋ እንቁ›› የሚል መጠሪያ የወጣላት አዳማ ከተማ 133.6 ካሬ ኪሎ ሜትር ሥፋት ሲኖራት፣ የሕዝብ ብዛቷ 300,000 ያህል ይገመታል፡፡

የከተማዋ መስተዳደር አዳዲስ የአስፓልትና የኮብልስቶን መንገዶች በመገንባት ላይ እንደሚገኝ፣ በከተማዋ ዙሪያ የአሥር ኪሎ ሜትር የቀለበት መንገድ በመገንባት ላይ እንዳለ፣ የጎርፍ መከላከል ሥራዎችና የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች ግንባታ እየተካሄደ እንደሆነ፣ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ እንደሆነ፣ የአዳማ ከተማ የቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት ተወካይ አቶ ለሜሳ ቱራ ለሪፖርተር የገለጹ ሲሆን፣ ጽሕፈት ቤቱ የ20/80 እና የ40/60 የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ መስተዳደር የጀመረውን የ20/80 እና የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም እንደ ሞዴል በመውሰድ በአዳማ፣ በሻሸመኔና በሌሎች 38 የኦሮሚያ ከተሞች ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ በጨፌ ኦሮሚያ (የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት) መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በአዳማ ከተማ የቦታ መረጣ ሥራ እንደተካሄደ እንደሆነ የገለጹት አቶ ለሜሳ፣ ምን ያህል ቤቶች እንደሚገነቡና የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ወጪ ጥናት እንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡ የቤቶቹ ግንባታ በ2007 ዓ.ም. እንደሚጀመር አክለው ገልጸዋል፡፡ ቀደም ሲል መስተዳደሩ 2,769 ኮንደሚኒየም ቤቶች መገንባቱንና በ2004 ዓ.ም. ባካሄደው የቤት ፈላጊዎች ምዝገባ 16,000 ነዋሪዎች እንደተመዘገቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s