የታዋቂው ፖለቲከኛና ጸሃፊ አብርሃ ደስታ እህት ከስራ ታገደች

  •  


ethsatሐምሌ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአረና የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ወይዘሪት ተክለ ደስታ የኣብራሃ ደስታ እህት በመሆንዋ ብቻ ከስራዋ ታግዳለች ። ወይዘሪት ተክለ ደስታ የጤና ባለሙያ ስትሆን የህወሓት ኣባልና የራያ ዓዘቦ ወረዳ የጤና ፅህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ሁና ታገለግል ነበር።

የወረዳው ባለስልጣናት “አንቺ እንደ ወንድምሽ ዓረናነሽ ፣ ላንቺ የሚሆን የህወሓት ሃላፊነትም ይሁን የሞያ ስራ የለንም፣ ላንቺ እንኳን ስራ፣ መሬቱም እሳት ሆኖ ያቃጥልሻል ” በማለት ከስራዋም ከህወሃት አባልነትም እንዳባረሩዋት ድርጅቱ አስታውቋል።

የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኣባይ ወልዱ ታላቅ ወንድም የሆነው ኣቶ ኣውዓሎም ወልዱ የዓረና መስራችና ኣመራር ኣባልነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ወይዘሮ ኣልጋነሽ ገብሩ በህወሓት መንግስት “ኣሸባሪ” ተብላ ከተከሰሰች ጀምሮ 3ቱ ህፃናት ልጆቿ የጎዳና ሂወት መምራት መጀመራቸውን ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

ህፃናቱ ኣባታቸውን  ከ9 ዓመት  በፊት  በሞት  ያጡ  ሲሆኑ፣  ጠላ እየጠመቀች ታስተዳድራቸው የነበረችው እናታቸውን በእስር ምክንያት ካጡ ብሗላ ትምህርታቸው ኣቋርጠው ፣የጎዳና ሂወት መግፋት ጀምረዋል።

እናታቸው  በ”ኣሸባሪነት” ተፈርጃ  በእስር ያጡ  ህፃናትን ለመንከባከብ በህብረት ባንክ መቐለ ቅርንጫፍ በ202 041 606 379 3018 የሚልየአካውንት ቁጥርተከፍቷል።

የሂሳብ ደፍተሩ የተከፍተው በወይ ዘሮ ኣልጋነሽ ታናሽ እህት ወይዘሮ ፅጌ ገብሩነው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s