የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ብሄራዊ አጀንዳው ያደረገ 4ኛው የኢሳት ክብር በዓል ሲዊዘርላንድ በበርን ከተማ በድምቀት ተከበረ።

456

ዕለተ ቅዳሜ 26.07.2014 በጭምቷ ሲዊዝ ርዕሰ መዲና በበርን ከተማ የአንዳርጋቸው ዓላማን ከግብ እናደርሳለን ያሉ የቆረጡ – የወሰኑ – ለቀጣዩ የትግል ጥሪ ሁሉ አለንልሽ ኢትዮጵያ ያሉ ኢትዮጵውያን በተደራጀላቸው የጋራ መጓጓዣ እንዲሁም በግልም አብዛኞቹ ወደ በርን ያመሩት በጥዋቱ ማልደው ነበር።

በእለቱ ከኢሳት አርቲስት ታማኝ በዬነ፤ አርቲስት መታሰቢያ ቀጸላና የስፖርት ጋዜጠኛው ፍሰሃ ተገኘ በአካል ተገኝዋል። በስካይፒ ደግሞ ከግንቦት 7 ከፍተኛው አመራር አካል ዶር. ታደሰ ብሩ ታዳሚ ነበሩ። ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት የሲዊዝ የኢሳት አሰተባባሪ ኮሜቴ ሰብሳቢ ወ/ት ሂሩተ ገብርኤል ነበሩ። ከዚህ በመቀጠለም የኢትዮጵያን ዬዕንባ ዘመን ያገናዘበ በምስል የተቀነባበረ ትረካ ፤ የነጻ ሚዲያ  ምስረታና ዕድገት በኢትዮጵያ፤ ሥነ ግጥም  ከሲዊዘርላንድ የኢሳት ዝግጅት ክፍል በቅደም ተከተል ቀርቧል።

ቀጣዩ የኢሳት የገለጻ ክፍል አህዱነት በአርቲስት መታሰቢያ ቀጸላ „አቅምን በመገንባት እረገድ የታላቋ ኢትዮጵያን መከራ በንጽጽር ከአደጉት አገሮች ጋር በማቀረብ ቅድሚያ ሊሰጣቸው በሚገቡ መሠራታዊ ጉዳዮች ላይ አትኮሮት የመስጠትን  አስፈላጊነት በማብራራት፤ ኢሳትን ቋሚ በሆነ መልኩ እራሱን ለማስቻል ሊከወኑ በሚጋባቸው አቅጣጫዎች ላይ   ከእነአስፈላጊነት ዕሴታቸው ጋር አብራርታለች።  አርቲስት መታሰቢያ ቀጸላ ታላቋ ኢትዮጵያ ያልተሰራች ሀገር ናት ባይ ናት። ስለሆነም ትውልዱን በሚጠበቁ የገዘፉ ሃላፊነቶች ላይ መራባረቡ ቀጠሮ አያስፈልገውም ብላለች“።  በቀጣይነት ጋዜጠኛ ፍሰሃ ተገኝ በበኩሉ „የነፃነት አስፈላጊነት ትግል ሁሉንም የመኖር መስኮች የሚመለከት ስለመሆኑ በማውሳት ለጤነኛ የእስፖርት ዕድገትና ለጠንካራ ተዋዳዳሪነት የአንዲት ሀገር የዲሞክራሲ ሥርዓት ተስተካክሎ በእኩልነት መስፍን አዎንታዊነቱን፤ እንዲሁም አለመስፈኑ ደግሞ በሙያው ላይ ያለውን አሉታዊና ገጽታዎች አብራርቷል።“

459

በስካይፒ በነበረው የዶ/ር ታደስ ብሩና የአቶ ሥነ ጊዮርጊስ ቃለ ምልልስ ጭብጥም „ዬዘመቻ አንዳርጋቸውን ተሳትፎ በሙቀቱ እንዲቀጥል ለማድርግ ሊተኮር ስለሚገባቸው አምክንያች ገንቢ አስተያዬቶችን አክሎ የቀረበ ነበር። ዶር ታደስ ብሩም በተረጋጋ መንፈስ የዘመቻ አንዳርጋቸው የአጭርና የረጅም ጊዜ መርኃ ግብሮች እንዲሁም ሁለቱን የሚያይዘውን የመካከለኛ ጊዜ ወሳኝ የተግባር ትልሞችን በማስገንዘብ ለተጨባጭ ተግራዊነታቸው የሁሉንም የተዋህደ ተስትፎ  በእጅጉ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ዶር ታደሰ ብሩ የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እኔ ተማሪው እሱ ደግሞ አስተማሪዬ ነው፣ ሁሉን የሰጠው እያዬህ የምትማርበት የተግባር ሰው ነበር በማለት በአውሮፓ ኮሚሽንን በብርቴን መንግሥት ሊደረግ ስለሚገባው ጫና በተመሰጠ አገላላጽ ሃሳባቸውን ገልጸዋል።“

457

በአርቲስት ታማኝ በዬነ በኩል „አንዳርጋቸው ኑሮው በጽናት ላይ የተመሰረተ ተግባርን ያሰበለ በመሆኑ፤ ወያኔ እጥፍ ተግባር ከውነን እናቅጥለዋለን ሲል ገልፆል። የአርቲስት ታማኝ በዬነ የገለጻው ፍላሎት፣ የድምጹ ግርማ ሞገስና የቁጭቱ ግለት ዬወጣቶችን ህሊና በቅጡ የሚያሰናዳ ነበር ማለት ይቻላል።“  እንደ አርቲስት ታማኝ በዬነ ገለጻ „የቆረጠና የነጠረ ትግል ወቅቱ የጠዬቀን ግዴታ በመሆኑ በጠላት ላይ ሊሰነዘር በሚገባው ማናቸውም የማጥቃት እርምጃ ድርድር የለም ብሏል።“

ከዚህ በመቀጠል በነበረው የኢሳት ፈንድ ራይዚንግ ፕሮግራም ጨረታውን የመራው እራሱ አርቲስት ታማኝ በዬነ ስለነበር እጅግ በለሰለሰ – በሚያዝናና – ውብ በሆነ አቀራረቡ የስብሰባውን መሰረታዊ መርሃ ግብር ነፍስ ዘርቶ ሲያስፈልገው ዕንባን – ሲያሰኘው ሳቅን  – ሲለው ወኔን – እንዲያም ሲል እልህን – ሁሉንም ዓይነት ኢትዮጵያዊ ስሜት ፈጥሮ ታዳሚውን በማክበርና በጥሩ አያያዝ ሳይጠገብ ነበር የጨረታው ሂደት የተጠናቀቀው። ወርቅ ዝግጅት ነበር።  ገለጻው በመረጃ የተደገፈ ስለነበርም ጭብጡ ወደ ተግባር ሰራዊቱን ለማሰማራት ልዩ አቅምና ጉልበት ነበረው። ስለሆነም ጨረታው በተግባር ቤቱ የከረንት አፊርስ የመወያያ መድረክ 1300.00 የሲዊዝ ፍራንክ አካባቢ ተጀምሮ በዙሪክ አራት ወጣት አንበሶች በ12.000.00 /አስራ ሁለት ሺህ የሲዊዝ ፍራንክ/ ተጠኗቋል።  የተለያዩ ለሽያጭ የቀረቡ መጸሐፍት፣ ፒኖች፤ አርማዎች ነበሩ። የሲዊዝ የኢሳት አመራር አካላት በሰሞናቱ በተካሄዱ ተከታታይ ሰላማዊ ሰልፎች ሁሉ የተቀናጀ ተግባር የከወኑ ስለነበሩ መሰናዶቸው አንቱ ነበር ማለት ይቻላል። ውጤቱም የሚያመረቃ።

የጨረታው የክብር ታላቅ እንግዳ የነጻነት ትግሉ የጭንቅላት ልብ፤ የመሆን መቻል አድባር፤ የእርቅ ድልድይ፤ የአርቆ ማሰብ አባወራ፤ የማስተዋል ባዕት የሆኑት የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፎቶ ግራፍ ነበር። ዙሪኮች ስንመለስ ከነክብራችን ነበር የተመለስነው። ስለምን? ወጣቶቻችን ሊቀድሙን  – ሊረከቡን አደራውን – በግንባር ቀደምትንት ተሰለፉልን። በማሸነፍ ውላችን በተግባር አስረው ነበር ወደ ባዕታችን የተመለስነው። ዙሪክ የጀግና አባወራውን ምስል በክብር አክብሮ በተግባር ሊያከበር አብሮን መጣ። በውስጣችንም ነጥሮ ጽላታችን ሆነ የመንፈሳችን ዜማ የአንዳርጋቸው ጽናት ሆነ!

458ስብሰባው ሁለንትናው ሙሉዑና ብቁ ነበር። ኢትዮጵያዊነት ፍቹ በድምቀት ታይቶበታል። እንደሚታወቀው በዚህ ወር ብቻ ሲዊዝ ውስጥ ሁለት ሰላማዊ ሰልፍና አንድ ህዝባዊ ስብሰባ መካሄዱ ነው። የሰዉ ጽናት ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ነው። ዛሬ እንዲህ የሚያኮሩና የሚያስመኩ ኢትዮጵውያን አዳራሹን ሙሉት አድርገው፤ በተሟላ ተሳትፎ አንደበተ -ኢሳት ፈክቶ የአርበኛ አንዳርጋቸው ቋያ ሳይበርድ እዩኝ እዩኝ ይል ነበር። እውነት ያስደስት ነበር። ያጽናና ነበር። የሚገርመው ነገር የተከበሩት የሰላማዊ ትግል የስልትና የቅንብር መዲናዎች ድንቆቹ የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ያፈጠሩት አዳረሽ ውስጥ በተዘጋጀላቸው ልዩ ቦታ የተገባውን ከውነው ነበር። ሃሰተኛ ሳልሆን ይህችን ሥንኝ ስጽፋት በሲቃ ዕንባ እዬተናነቀኝ ነው። ይህቺ ቀን ለእምነቱ ተከታዮች የተከበረችና የተቀደሰች ሆና፤ ነገር ግን መከራ ላይ ስለሆኑ እንዲህ ተሚራቸውንና ማናቸውንም የሚያስፈልገውን ነገር በስንቅ ቋጥረው በወል ማዕዶት የእናት ሀገር ዕንባ እዬታሰበ ተከበረ። ይህ ለሲወዘርላንድ ብቻ ሳይሆን በመላ ዓለም ለተበተኑ ህዝብ እስልምና እምነት ተከታዮች አብነቱ ዘመን የሚያሻግር፤ ዘመንም የማይሽረው ጉልት ነው እላላሁ በጣም በበእርግጠኝነት እኔ ዘጋቢዋ ሥርጉተ  ሥላሴ። በሌላ በኩል የነፃነት ትግሉ ዬተዋህዶ ልጆችም ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል በአላቸውን ሉዛን

ቅዱስ ገብርኤል አክብረው ታቦታቸውን አንግሠው፤ የተገባውን ከውነው በኋላም ልባቸውን እንጥልጥል ወደ አደረገው ሀገራዊ ጉዳይ ነበር የገሰገሱት። ወደ ዬቤታቸው አልተመለሱም ነበር።  እነሱም ወደ ዕናባቸው መጡ። አያስደስትም? አያስመርቅም? እውነት አፍርቶ ጽናት እንዲህ አስብሎ ማዬት ነገን ያበጃል። ትውልድንም ይገነባል።

እጅግ የማከብራችሁ የሀገሬ ልጆች አብራችሁኝ እንደምትሆኑ በማመን ሌላም እህታችን ወ/ት ቅድስት ብሩክ ለኢሳት  ዬአንገት የወርቅ ሃብሏን ውልቅ አድርጋ ሰጠች። የተግባር እመቤትንት – ሴቶች!  በቃ! እኛ ጨክነናል! ቆርጠናል! ወስነናል! አንዳርጋቸው የእኛ –  እኛም  የአንዳርጋቸው አሉ ሲዊዞች።

በተረፈ መስተንግዶው ሙሉ ነበር። ጠጁ  – ቡናው – እንጀራው – ዝግኑ – አልጫው  – ድፎው ምን ይቀራቸዋል የሲዊዝ ሴቶች – የሴት አርቂዎች እኮ ናቸው – ፍቅሮች። የዛሬ የሴቶች ተሳትፎ ጎምርቷል። ድምቋል። ዬኢትዮጵያ መከራ የሚያልቀው ሴቶች በነቂስ ወጥተው በባንዳው ወያኔ በሽፍታው ወያኔ ላይ ሲሸፍቱ ብቻ ነው። ቁልፉ ይህ ነው። ፍላጎት ከጸዳ መነገዱ እረዳ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s