አቶ በረከት ስምዖን ከሆስፒታል መውጣታቸው ተገለጸ

ሰሞኑንን ጅዳ ሳውዲ አረቢያ አንድ ሪፈራል ሆስፒታል በህክምና ላይ የነበሩት አቶ በረከት ስሞኦን ሞቱ እይተባለ የሚናፈሰው ዜና ትክለኛ አለመሆኑን የሚገልጹት ምጮች ። የመንግስት ባለስልጣኑ ዛሬ ማምሻውን ከሆስፒታል ወጥተው ሼክ አላሙዲን ወደ አዘጋጁላቸው ሆቴል «ማረፊያ» ማቅናታቸውን አረጋግጠዋል።

እሁድ ለሊት በሼክ አላሙዲን የግል አይሮፕላን ሳውዲ አረቢያ ለህክምና በሚስጠር የገቡት እኚሕ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን የልባቸውን የደም ቧንቧ ለማስፋት የተደረገው ህክምና ስኬታማ እና ለክፉ ችግር የማይሰጣቸው መሆኑን የሆስፒታሉ ምንጮች ቢገልጹም የባለስልጣኑ የሰውነት አቋም ከትጎሳቀለው እና ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የጠቆረው ፊታቸው ገጽታ ሰውነታቸው ውስጥ መልካም ነገር እንደሌለ ያመላክት እንደነበር በአካል ያዮቸው የአይን እማኞች አቶ በረከት በቀርብ ቀን ወደ ሃገር ቤት አሊያም ለተሻለ ህክምና ወደ አውሮፓ ለማቅናት እቀድ እንዳላቸው ገልጸዋል። ዛሬ ረፋዱ ላይ አቶ በረከት ከሚያገግሙበት ሆስፒታል ለቀው ከመውጣታቸው ቀደም ብሎ ለጉብኘት ወደ ሆስፒታሉ አቅንተው የነበሩ ምንጮች በአካባቢው ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳልነበረ እና ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ እንዳልቀሩ የሚገመቱ ነጭ ለባሾች ሆስፒታሉ አካባቢ መታየታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ከአቶ በረከት ስሞኦን ጋር የመጡት የጦር ሃይሎች ሆስፒታል ዶ/ር ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በዝግጀት ላይ መሆናቸውን እነዚሁ ምንጮች አክለው ገልጸዋል። ። የአቶ በረከት ስሞኦን የጤንነት ሁኔታ በተመለከት ከጅዳው የኢትዮጵያ ቆንሳል ጽ/ቤት መረጃ ለማግኘት ያድረኩት ሙከራ ባይሳካም ለዕረፍት ሀገርቤት የሄዱትን ቆንስላ ሸሪፈን ተከተው ወ/ሮ ሙንተሃ ወደተጠቀሰው ሆስፒታል ሰው እየላኩ የኚህን ባለስልጣን የጤነነት ሁኔታ በቀርብ በመከታተል ላይ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ባለስልጣኑ የሚገኙበትን የጤና ሁኔታ ካረፉበት ሁቴል የምናገኘውኝ መረጃ እይተከታተለን ለማቅረብ ይሞከራል

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s