የUS ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ ኤሪትራ ስለሚደረጉ ጉዞዎች ያወጣው ማስጠንቂያ

የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ ኤርትራ የሚደረግ ጉዞ ለአሜሪካ ዜጎች አደገኛ መሆኑን አስጠነቀቀ።

የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ከኤርትራ መንግሥት የመውጫ ቪዛ ላያገኙ ስለሚችሉ ወደ ዚያች አገር ከመሄድ መታቀብ እንዳለባቸው ሚንስቴሩ በመግለጫው አስጠንቅቋል።

የኤርትራ መንግሥት የውጪ አገር ዜጎች በአገር ውስጥ በሚያደርጓቸው ጉዞዎች ላይ ገደብ መጣል መቀጠሉን መግለጫው አመልክቶ፤ እገዳውም ማንኛውም ነዋሪና አገር ጎብኚ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶችንም ጨምሮ፤ ከአሥመራ ከ25 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ለመውጣት ከፈለጉ ከአሥር ቀናት በፊት እንዲያመለክቱ የሚጠየቁ መሆናቸውን ገልጿል።

በአብዛኛው ፈቃድ የሚያስፈልገውም የቱሪስት መስህብ ለሆኑት ምፅዋና ከረን መሆኑም ታውቋል። ይሁንና ወደ ድንበር ቀረብ ያሉ ሌሎች አካባቢዎች እና ከዚህ ቀደም ዲፕሎማቶች የማያዘወትሯቸው ስፍራዎች የሚጠየቅ ፈቃድ ግን ፈጽሞ የተከለከለ ነው። በዚህም ሳቢያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ከአሥመራ ውጪ የቆንስላ አገልግሎት ለመስጠት ምንም ዓይነት ዋስትና እንደ ሌለው ተመልክቷል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s