ለ13 ሰዎች ሕይወት መጥፋት መንስዔ


ለ13 ሰዎች ሕይወት መጥፋት መንስዔ የሆነው በጋምቤላ ክልል በማጃንግ ዞን በሜጢ ከተማ መስከረም 1 ቀን 2007 ዓ.ም የተቀሰቀሰው ግጭት በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጋትሉዋክ ቱት ተናግረዋል…

የክልሉ መንግስት ከዞኑ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች ጋር በመቀናጀት ተከስቶ የነበረውን ግጭት መቆጣጠር መቻሉንና ግጭቱን የፈጠሩና በግጭቱ ተሳትፎ ነበራቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እየጣርን ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳደሩ፡፡

በከተማው ብቻ ሳይሆን በገጠር ቀበሌዎችም ተመሳሳይ ግጭት ተከስቶ የሰው ህይወት መጥፋቱን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ ምን ያህል ሰዎች እንደተጎዱ የማጣራት ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

በተፈጠረው ግጭት ተፈናቅለው የነበሩ ነዋሪዎችን ግብረ ኃይል በማቋቋም ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉንና መደበኛ ኑሯቸውን መምራት መጀመራቸውንም ተናግረዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s