የወግዲ ወረዳ መምህራን የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ታወቀ

በደቡብ ወሎ ወግዲ ወረዳ የመሰናዶ እና የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ መመህራን የስራ ማቆም አድማውን ያደረጉት መንግስት ቃል በገባው መሰረት የሃምሌ እና ነሃሴ ወር ደሞዝ ጭማሪ አልከፈለንም በሚል አድማ ማድረጋቸውን ኢሳት የተሰኘው ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።
እንደ ኢሳት ዘገባ ከሆነ መምህራኑ የደሞዝ ጭማሪው ከተገለጸበት ጊዜ አንስቶ በታየው የዋጋ ንረት እየተሰቃየን ነው በማለት የወረዳውን አስተዳዳሪ ለማነጋገር ሙከራ ቢያደርጉም አስተዳዳሪው ለስብሰባ በሜዳቸው ሳይሳካለቸው ቀርቷል። እርሳቸውን የወከሉት አቶ ሃጎስ የተባሉ ሰው ከመምህራኑ ጋር ሃይለ ቃል መለዋወጣቸውን ተከትሎ መጠነኛ ውዝግብ መፈጠሩን ምንጮች ገልጸዋል። መምህራኑ ጭማሪው በአስቸኳይ ካልተከፈላቸው በአድማው እንደሚቀጥሉበት እየተናገሩ ነው።
ኢሳት ሊያነጋግራቸው የሞከረው የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ እንድሪስ ስብሰባ ላይ በመሆናቸው አስተያየታቸውን ለመስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰኞ እለት የተጀመረው መምህራኑን ከስራ ገበታቸው የማፈናቀል ሁኔታ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል አስተያየታቸውን ለየኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ የሰጡ መምህራን አስታውቀዋል:: እንደ መምህራኑ ገለጻ ከሆነ በቅርቡ ከስራ ገበታቸው የተባረሩት መምህራን የመጀመሪያዎቹ እንጂ የመጨረሻዎቹ ሊሆኑ እንደማይችሉ መሆናቸውን ገልጸው ሁሉም መምህር ከህወሀት መራሺ ኢህአዴግ ጋር ተስማምቶ መስራት ካልቻለ ትምህርት ቤቱን ለቆ መሄድ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ እና ዛቻ ከየትምህርት ቤቱ ሃላፊዎች እየደረሰው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል::
በመምህራኑ ላይ እየደረሰ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ለማስቆም በማሰብ በቅርቡ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ የስራ ማቆም አድማ ሊጠራ መዘጋጀቱን ማስታወቁ የሚታወስ ሲሆን ሁሉም መምህር ለዚህ ታላቅ ጥሪ እራሱን አዘጋጅቶ በትእግስት ይጠብቅ ዘንድ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል::

18

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s