የደደቢት ጉዞ መዘዝ፤ ከሰራዊት ፍቅሬ እስከ ታገል ሰይፉ

በመጀመርያ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ደጋፊና ተደጋፊ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን በሙሉ ጠሯቸው። ሰበሰቧቸው። እንዲህም አሏቸው። “ወደ ደደቢት አብራችሁን ትሄዳላችሁ፤ እዛ እንደደረሳችሁም አመጣጣችንንና አካሄዳችንን በደንብ አድርጋችሁ ታጤናላችሁ። ከዚያ ስትመለሱ ሁሉንም ነገር ለህዝቡ ትናገራላችሁ።…”
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሃገር መሪ ሆነው የሚሰሩት እኝህ ሰው መልዕክታቸውን በዚህ አላበቁም። አይናቸውን ፈጠጥ፤ ጉሮሯቸውንም ጠረግ-ጠረግ አደረጉና ንግግራቸውን ቀጠሉ “ስለረጅሙና መራራው ትግላችን፤ ከጅምራችን እስከ አያያዛችን የታዘባችሁትን ሁሉ ንገሩን። ጥሩውንም ይሁን መጥፎውን ነገር ሳትደብቁ ተናገሩ።…”
serawit fikre
ድምጻዊው በዝማሬ፣ ጸሃፊው በድርሰት፣ ተዋንያኑ በተውኔት ስለ ህወሃት የአርባ አመት ጉዞ እንዲመሰክሩ የተሰጠች ትእዛዝ መሆንዋ ነው። አጭር፣ ግልጽ እና ቀጭን መልዕክት ነበረች።

የስርዓቱ ደጋፊ ሳይሆን ይልቁንም ተደጋፊ የሆኑት ሁሉ የዘመቻውን ጥሪ በደስታ ተቀበሉ። ወደ ደደቢትም አመሩ። የታዘቡትንም ነገር ሲናገሩ ሰማን።
ልብ እንበል! እነዚህ የጥበብ ሰዎች ናቸው። ጥበብ ደግሞ የሕዝብ አገልጋይ ናት። ጥበብ ለእውነት የምትቆም ዘብ ናት። ጥበብ አንድን ህብረተሰብ የመቅረጽ እና የመለወጥ ሃይል አላት።
በአለማችን የጥበብ ሰዎች ሚና ጎልቶ የሚታየው ተፈጥሮ ባደላቸው የጥበብ ስራ ብቻ ሳይሆን፤ እነዚህ ሰዎች በጥበብ ስራቸው ውስጥ ለህዝብ በሚያስተላልፉት እውነተኛ መልእክትም ጭምር ነው።

አርቲስቶች አክቲቪስቶች መሆን አለባቸው ብሎ መከራከር አይቻልም። ይህ የራሳቸው ምርጫ ነው። መሆን ካለባቸው ግን

እንባ ማበስ ነው የሚገባቸው። ወቅቱን ጠብቆ እንደሚቀየር ድሪቶ መንግስት ሳይሆን

ክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)http://www.zehabesha.com

posted tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s