የሎጎ ሀይቅ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በእሳት ጋየ

በደቡብ ወሎ ዞን በሀይቅ ከተማ አስተዳደር የሎጎ ሀይቅ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በእሳት ጋየ፡፡ የሰሞኑ የቃጠሎ ሁኔታ ጣይቱ ሆቴልን ጎብኝቶ፤ በባህርዳር አርጎ ደቡብ ወሎ ሀይቅ ላይ ደርሷል፡፡ ቀጣይስ ማን ይሆን??? ሰኞ አመሻሹ ላይ የሀይቅ ከተማ አድማስ በእሳት ነበልባልና በጭስ ታፍኖ ነው ያደረው፡፡ ምክንያቱ እስካሁን ባልታወቀውና ትናንት በ18/05/07 ዓ.ም አመሻሹ ላይ በተቀሰቀሰው የእሳት አደጋ ኮሌጁ ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ወድሟል፡፡ የኮሌጁን የንብረትና ፋይናንስ ክፍል እንዲሁም አይሲቲ ማእከል ጨምሮ በርካታ የስልጠና መሳሪያና ንብረቶችን የያዙ ክፍሎች የእሳት አደጋው ሰለባ ሆነዋል፡፡ ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለፁት ግምቱ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ ንብረት እንደወደመ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በከተማ አስተዳደሩ የእሳት አደጋ መከላከል ባለመኖሩ የጉዳቱ አስከፊነት እንደጨመረና የእሳት አደጋ ቡድን ከዞን ከተማዋ ደሴ ከ 30 ኪ/ሜ በላይ ተጉዞ እስኪመጣ እሳቱ በከፍተኛ ሁኔታ እንደተባባሰና ተቋሙን እንደተቆጣጠረው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሎጎ ሀይቅ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ግንባታው ግማሽ በግማሽ እንኳ ሳይጠናቀቅ ከ7 ዓመት በላይ መቀመጡና የመዋለ ህፃናት ያክል እንኳ ስታንዳርድ አለመኖሩ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ የፈጠረ ሲሆን፤ ህብረተሰቡ ለዚህ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ከበቂ በላይ የሚባል የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ በነፍስ ወከፍ እንዲያዋጣ ተደርጎ ባለበት ሁኔታ እንዲሁም ባዛር ተዘጋጅቶ በርካታ ሚሊየን ብር ከተዋጣና ከተሰበሰበ በኋላ ይህ ተቋም ግድግዳ እንኳ ሳይሰራ ኮለኖቹን ብቻ አቁመው ተረሳ በሚባል ሁኔታ የኮሌጁ ግንባታ ተቋርጦ ለሰልጣኞች ጊዜያዊ በሚል የቆርቆሮና የዳስ ክፍል በመስራት ስልጠናው በመሰጠት ላይ መሆኑ በህብረተሰቡ ለበርካታ ጊዜ ጥያቄ ቢነሳበትም ምላሽ በማጣቱ ህዝቡ ተሰላችቶና መፍትሄ ሰጭ አካል አጥቶ ባለበት ሁኔታ ይህ አደጋ መከሰቱ በህብረተሰቡ ዘንድ የተለያዩ መላምቶች እንዲሰነዘሩ ያደረገ ሲሆን፤ምናልባትም ኮሌጁ ግንባታው ባይቋረጥና ተጠናቆ ቢሆን ኖሮ ይህ አደጋ ሊከሰት የሚችልበትን እድል ያጠበው ወይም ሙሉ በሙሉ ያስቀረው ነበር የሚል ቁጭት ከህብረተሰቡ እየተሰነዘረ ይገኛል፡፡ የሀይቅ ከተማ አስተዳደር በመልካም አስተዳደር ችግርና በተለይ የአመራሮች የሙስና ቅሌት አይን ባወጣ መልኩ እንደሚፈፀምና በተለያየ ጊዜ የአመራር ቅያሬ እንደሚደረግ ይህ ደግሞ የሙስና ቅሌት ፈፅሞ ወደሌላ ቦታ የሚዛወሩ ሀላፊዎችን ተከትሎ የሚመጣው አመራርም የህብረተሰቡን ችግር ከመፍታት ይልቅ ‹‹የድርሻዬን አንስቼ›› እንዲሉ ብሂል፤ ሌላ የህዝብ ሀብት ምዝበራ ይፈፀማል፤…ይህ ደግሞ ከተማ አስተዳደሯ ከማደግ ይልቅ ኋላ ቀርነቷ እየጎላ የመጣበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ ከእሳት አደጋው ጋር ተያይዞ የሚነሱ የህዝብ አስተያየቶችንና ስለከተማ አስተዳደሩ አጠቃላይ ሁኔታ በሌላ ዘገባ የማቀርብላችሁ መሆኑን ለመግለፅ እወዳለሁ:: : http://www.zehabesha.com/

posted tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s