አቃጠሉት አሉ!!! -ከ-ከተማ ዋቅጅራ

  •  

Awasaትላንትና ማታ ለአዋሳ ከተማ ነዋሪዋች ከባድ ቀን ነበረ። ከባድ ብቻ  ሳይሆን አስደንጋጥም ነበረ። በአዋሳ ከተማ አዲስ ከተማ  ተብሎ የሚጠራው ቦታ የገበያ ማእከሉ ከፍተኛ ንብረት እና በሰው ህይወት ጉዳት ያስከተለ የእሳት አደጋ አስተናግዳለች። በዚህ ሌሊት በከተማዋ የተነሳው እሳት እየተንቀለቀለ ወደ ሰማይ ይወረወር ነበረ። ይህ ለአዋሳ ህዝብ ከባድ ሌሊት ላይ ጭኸቱ ከየት እንደሆነ በማይታወቅ መልኩ ከተማዋ በሃዘን ጭኸት ስትናወጥ ነበረ። እጅግ ዘግናኝ ሌሊት ነበረ።

አዋሳ ! አዲስ ከተማን ማን አቃጠላት? የእሳቱስ መንስኤ ምንድን ነው? በጅምላ በአንድ ላይ እሳት ይነሳል እንዴ? አካባቢዋን እንቃኛት።

አዲስ ከተማ ተብሎ በአዋሳ ውስጥ የተመሰረተች አዲስ መንደር አዲስ ሰፈር በአዲስ ምስረታ የተመሰረተች እና እያደገች ያለች ከተማ ናት። ይህቺ ከተማ በእሳት የጋየችውን መንደር  መንግስት ለመንገድ ስራ እንደሚፈልገው እና በመንደሯ ውስጥ የሚያልፍ መንገድ ለመገንባት እንደሚያስብ ለነዋሪው ተነግሮአቸው ነበረ። ታዲያ ልማትን የሚቃወም የለም። ህዝቡ ተጠቃሚ የሚያደርግ እና ትክክለኛነቱን የታመነበት ከሆነ መንገድ በመሰራቱ ተቃውሞ  የሚያሰማ አለ  ብዬ አልገምትም። ታዲያ መንገድ ለመስራት እሳት ማስነሳት ለምን አስፈለገ? መንገድና እሳት ምንድነው ዝምድናቸው? እሳት ከመንገድ ጋር ምንም ዝምድና የላቸውም። እሳት ከወያኔ ጋር ግን ዝምንድና አላቸው። ተዛማጅነታቸው በ3 መንገድ ነው።

1ኛ. ለግምት የሚያወጡትን ወጪ ስለሚያስቀርላቸው። ምክንያቱም እሳቱ  የተነሳው በግለሰቦች የጥንቃቄ ጉድለት ነው በማለት እሳቱ ንብረትን ማውደሙን ካረጋገጡ በኋላ እሳት አደጋ መጣ ለማስባል ባለቀበት መጥቶ ውሃውን ረጨት ረጨት አድርጎ ካጠፋ በኃላ ቦታው አካባቢው ከሳቱ በፊትም ከሳቱ በኋላም በፌድራል እንዲከበብ በማስደረግ እዝቡን ካራቁ በኋላ ሌላ ተቀያሪ ቦታ ይሰጣችኋል በማለት ህብረተሰቡን ለከፋ እንግልት መዳረግ እና መንግስት የራሱን  ጥቅም ማስጠበቅ።

2ኛ. የሰው ህይወትን ጉዳት ላይ መጣል አልያም የንብረት መውደም ስለሚያስደስታቸው ነው። ወያኔ ህዝብን የመጥላት እና የመናቅ ሰይጣናዊ አባዜ ስለተጠናወተው እንደዚ አይነቱን ተግባር በማድረግ ህዝብን ለስቃይና ለመከራ ሲዳረጉ ማየት ስለሚያስደስተው።

3ኛው እና ዋንኛው ደግሞ ጭንቀት ሲበዛበት ነው። ይህ ማለት ወያኔ ከፊቱ ከባድ ነገር እንደሚመጣበት በሚያውቅበት ግዜ ሃሳብን ለመስረቅ የሚጠቀምበት ዘዴ ነው። በአሁኑ ግዜ ወያኔን አንፈልግህም፣ ወያኔ አያስተዳድረንም፣ ወያኔ በቃን፣ የሚሉ ጥያቄ በርትቷል። በትጥቅም ትግል ያስጨነቁትም ኃይሎች አሉ፣ ታዲያ የህዝቡ ሃሳብ በአንድ ተቀናጅቶ ትኩረቱን ወደ ወያኔ ካዞረ ስልጣኑን እንደሚያጣው ያውቃል ስለዚህ ለዚህ ፍራቻው እንደዚ የወረደ ተግባር እና ሰይጣናዊ ስራ ይሰራል።

ወያኔ መንግስት ከአሁን በኃላ ሁሉም ነገር ያበቃለት ይመስለኛል። አንዴ ድሬድዋን ቢያቃጥል አንዴ አዲስ አበባን ቢያቃጥል አንዴ አዋሳን ቢያቃጥል የህዝቡ መልስ ግን አንድ ነበረ። ይህንን የወረደ እና አሳፋሪ ስራ የሚያደርገው ወያኔ እንደሆነ አረጋግጠው በመናገር ላይ ናቸው። ህዝብ መሪ ነን ከሚሉት ቀድሞ ሄዷል።

ለአዋሳ ህዝብ ይህ ድርጊት በደል ነው። ወያኔ ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው ዛሬም በአዋሳ ህዝብ ላይ አድርጎታል። ልክ እንደ ጸበል የሁሉንም ክልል እንደሚያደርስ ጥርጥር የለኝም። የህዝ ንብረት እንዳይቃጠል፣ ህዝባችን የእሳት ሰለባ እንዳይሆን፣ የህዝባችን እንባ በከንቱ እንዳይፈስ፣ ህዝባችን ለፍቶ ያፈራው ንብረት በአንድ ሌሊት በማጣት ወደ ስቃይ እንዳይገባ፣ ዋናውን እሳት ቤንዚን እና ክብሪት የሆነውን ወያኔን ቀድሞ ማጥፋት ነው። ያኔ በህዝብ ላይ እና  በህዝብ ንብረት ላይ እሳት የሚያስነሳ አይኖርም።

ከ-ከተማ ዋቅጅራ

-http://www.zehabesha.com/

post tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s