የሕወሓት መንግስት 5 የደህነንት አባሎቹን ወህኒ ወረወረ * ይህ በስርዓቱ ውስጥ ያለውን መፍረክረክና አለመተማመን ገሃድ ያጋልጣል

news
ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው:-

የመከላከያ እና የደህንነት ግምገማዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ::ቀጣዩ ግምገማ ከዛቻና ማስፈራራት ወደ ልመና ሊዞር ነው::ባለፉት ሳምንታት በመከላከያ ሰራዊት በምድር ጦር እና አየር ሃይል እንዲሁም በደህንነት መምሪያ ሲደረጉ የነበሩ ግምገማዎች በስፋት ቀጥለው አባሎቻቸውን እያሰሩ እና እያስፈላሩ በመጭው ሳምንቶችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለስርአቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል::

በመፍረክረክ ላይ ያለው ስርአቱ ባደረበት ከፍተኛ ስጋት እና በገባበት አጣብቂኝ ተከትሎ በመከላከያ ውስጥ እና በደህንነት ውስጥ በተከሰተው አለመተማመን የተጀመረው ግምገማ ወደባሰ ጥርስ መነካከስ መሸጋገሩን የጠቆሙት ምንጮቹ የወያኔ ባለስልጣናት በከፍተኛ ዛቻ እና ማስፈራራት ሰራዊቱን እና ደህንነቱን ለመቆተጠር አለመቻላቸው ሲታወቅ ግምገማው ውጤት ባለማሳየቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምናልባትም ቀጣዩ ግምገማ ከማስፈራራት ወደ ራሳችንን እናድን ልመና ሊሸጋግር ይችላል ሲሉ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል::
ከምድር ጦር እና ከአየር ሃይል ተይዘው የታሰሩትን ጨምሮ በአሁን ወቅት ሌሎች አምስት የደህንነት አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደህንነት ቢሮ ሰራተኞች መረጃ የጠቆመ ሲሆን በዚህም መሰረት :

1ኛ/ አቶ ተክሉ ወልደሃዋርያት .. በንፋስ ስልክ/ላፍቶእና የአቃቂ አከባቢ የስለላ ስምሪት አስተባባሪ

2ኛ/ አቶ አበራ ዋሴአንተ ….በንፋስ ስልክ/ላፍቶ እና ይዋቃቂ አከባቢ የደህንነት ሰራተኛ

3ኛ/ወይዘሪት መብራተይ ገብረአናንያ … በቅርቡ ከትግራይ መታ ቦሌ አከባቢ ካለ ቢሮ ተመድባ የነበረ

4ኛ/አቶ በክሪ አህመድ … የአፋር ክልል አከባቢ ተወላጅ እና በመርካቶ አከባቢ ተመድቦ ሲሰራ የነበረ

5ኛ/አቶ ይህደጎ (ወዲሰራዬ) …ኤርትራዊ ሆኖ ለወያኔ የሚሰራ::

እነዚህ ከላይ ስም ዝርዝራቸው የተጠቀሰው ሰዎች በተለያየ ጊዜ ከተመደቡበት ስራ ውጪ በመንቀሳቀስ በስራቸው ላይ ሆነው የተቃዋሚ ሃይላት በቁጥጥር ስር እንዳይውሉ ጋሬጣ የፈጠሩ ለደምህት ድጋፋቸውን የሚሰጡ የውስጥ ቦጥቧጮች በሚል ግምገማ እና በሃላፊዎች ላይ ጥያቄ በማብዛት በስራ ላይ ሰበብ በመፍጠር የተገመገሙ እና ወደ ጨለማ እስር ቤት የተወረወሩ መሆኑ ታውቋል::በቡድን ህዝብን በመዝረፍ ላይ የተሰማሩ የደህንነት አባላት ግን እንኳን ሊገመገሙ ይቅር እና በእኩይ ስራቸው ቀጥለው እንደሚገኙ ምንጮቹ ተናግረዋል::

– See more at: http://www.zehabesha.

post tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s