ችሎቱን አሻንጉሊት ብለሃል የተባለው አብርሃ ደስታ ተጨማሪ 9 ወር ተፈረደበት * ፍርዱን ሲሰማ ለ3ኛ ጊዜ በማጨብጨብ አሻንጉሊቱን ችሎት “ደፈረ”

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ለሦስተኛ ጊዜ ችሎት መድፈራቸው ታውቋል፡፡ በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ዛሬ መጋቢት 3/2007 ዓ.ም ፍ/ቤት የቀረቡት አመራሮቹ መጋቢት 1/2007 ዓ.ም በነበረው ችሎት ወቅት ችሎት ደፍራችኋል በሚል አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ እና ዳንኤል ሺበሽ እያንዳንዳቸው በ7 ወር እስር እንዲቀጡ ሲበየንባቸው ብይኑን በመቃወም ማጨብጨባቸውና ሳይፈቀድላቸው መናገራቸው ይታወሳል፡፡ በዕለቱም ድርጊታቸው ችሎት መድፈር ነው በሚል ጥፋተኛ ተብለው ነበር፡፡ በዛሬው ውሎው የቅጣት ውሳኔ የሰጠው ችሎቱ ለሦስተኛ ጊዜ በሦስቱ አመራሮች ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ፍርድ ቤቱ አቶ የሺዋስ አሰፋ እና አቶ ዳንኤል ሺበሽን ‹ብይኑን በመቃወም አጨብጭባችኋል› በሚል እያንዳንዳቸውን በ7 ወር እስራት፣ እንዲሁም ከማጨብጨብ በተጨማሪ ችሎቱን ‹አሻንጉሊት› ብሎ ሰድቧል የተባለው አብርሃ ደስታ ደግሞ በ9 ወር እስራት በድጋሜ ተቀጥተዋል፡፡ አመራሮቹ ዛሬም ለሦስተኛ ጊዜ ብይኑ ተሰምቶ እንዳለቀ በተቃውሞ በማጨብጨብ ለሦስተኛ ጊዜ ችሎቱን ‹ደፍረዋል›፡፡ ፍርድ ቤቱም አመራሮቹ አሁንም ጥፋት መፈጸማቸውን ገልጾ፣ ነገር ግን በይቅርታ እንዳለፋቸው በመግለጽ ድርጊታቸውን እንዲያስቡበት አስገንዝቧል፡፡ ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎ አቃቤ ህግ በ7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሰለሞን ላይ አሻሽሎ እንዳቀረበው የተነገረለትን ክስ ተቀብሏል፡፡ ተከሳሾች መጋቢት 10/2007 ዓ.ም የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

http://www.zehabesha.com/

post tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s