ታይላንድ፥ ኢትዮጵያዊው ባለሥልጣን በፖሊስ ተጠየቁ

በታይላንድ ነዋሪ የሆኑት ኢትዮጵያዊው የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት ባለሥልጣን በአንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሠራተኛ የቀረበባቸውን ክስ በተመለከተ መልስ እንዲሰጡ በፖሊስ መጠየቃቸው ተዘገበ። ባንግኮክ ፣ ታይላንድ በሚገኘው  የከፍተኛ ባለሥልጣኑ ዶክተር ዮናስ ተገኝ ቤት ተቀጣሪ የነበረችው  የ25 ዓመት ወጣት የቤት ሠራተኛ  እንግልት ደርሶብኛል ስትል ነው ክስ ያቀረበችው። ዶክተሩ ከባለቤታቸው ጋር በመሆን ደብድበውኛል፣ አንገላተውኛል፣ እንዲሁም  በዘመናዊ ባርነት ገዝተውኛል ስትል ወጣቷ ላቀረበችው ክስ ዶክተሩ መልስ እንዲሰጡ በፖሊስ ተጠይቀዋል። ዶክተር ዮናስ ተገኝ ስማቸውን ለማደስ ከባለሥልጣናት ጋር እንደሚተባበሩ መግለጣቸውን፣ የቀረበባቸው ክስም መሠረተ ቢስ ነው ማለታቸውን PIT የተሰኘው የዜና ምንጭ አክሎ ጠቅሷል። ወጣቷ በቤት ሠራተኛነት ከሰኔ 10 ቀን፣ 2005 ዓም አንስቶ እስከ የካቲት 29 ቀን፣ 2007 ዓም ድረስ በቤታቸው ባገለገለችበት ወቅት እንደቤተሰብ እንደያዟት  ዶክተር ዮናስ ተገኝ ለፈረንሳይ ዜና ወኪል በኢሜል ገልፀዋል። ይኹንና ዶክተሩ ከባለቤታቸው ጋር በመሆን በደል እንደፈጸሙባት አኔት በሚል ስም የተጠቀሰችው የቤት ሠራተኛ ተናግራለች። የታይላንድ የጠበቆች ምክር ቤት በበኩሉ ዶክተር ዮናስ ተገኝን  በአራት የክስ አይነቶች ለመክሰስ በቂ ማስረጃ እንዳለው ጠቅሷል። የድርጅቱ የሠብዓዊ መብት ክፍል ሠራተኛ የሆኑት ሰራፖንግ ኮንግቻንቱክ ድርጅታቸው ዶክተር ዮናስ ተገኝን  በሕገወጥ የሠው ማዘዋወር፣ በባርነት አገዛዝ፣ የልጅቷን ፓስፖርት በመንጠቅ እና ሸሽጎ በማስቀመጥ ወንጀል እንደሚከስ አስታውቋል።  ሕገወጥ የሠው ማዘዋወር ብቻውን በታይላንድ ከአራት እስከ 10 ዓመት ድረስ በእሥራት ሊያስቀጣ  የሚችል ወንጀል ነው።http://www.dw.de/

post tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s