የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሁለት ጊዜ ተገዶ አረፈ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከቻይና ጓንዙ ከተማ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሲያመራ ባጋጠመው የኢንጅን ችግር በአንድ ቀን ሁለት ጊዜ በህንድ ሙባይ ከተማ ለማረፍ ተገዷል፡፡ 

በበረራ ቁጥር ET607 283 መንገደኞችንና 14 የበረራ ሠራተኞችን ጭኖ ከቻይና የተነሳው ቦይንግ 777-30ER አውሮፕላን፣ ቻሃትራፓቲ ሺቫጂ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ማረፉ ታውቋል፡፡ አውሮፕላኑ በድጋሚ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀና በኢንጅን ችግር ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ በግዳጅ አርፏል፡፡ በዚህም ምክንያት መደበኛ የአሥር ሰዓት ጉዞው በአንድ ቀን ሊዘገይ ችሏል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስለጉዳዩ እውነትነት ለሪፖርተር አረጋግጦ፣ ሚያዝያ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ላይ አውሮፕላኑ በሰላም ማረፉን የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ ገልጿል፡፡ አውሮፕላኑ በቀን ሁለት ጊዜ ለማረፍ የተገደደው ባጋጠመው የኢንጅን ችግር መሆኑን የገለጸው አየር መንገዱ፣ ይህ የተደረገው ለመንገደኞች ደኅንነት ሲባል መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

ትራቭል ዌብሳይት በሚያወጣው መረጃ መሠረት ኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ በዓለማችን ካሉ አስተማማኝ አየር መንገዶች መካከል የስድስተኛ ደረጃን መያዙ ይታወሳል፡፡

 http://ethiopianreporter.com/
poste tigi flate
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s