የሕወሓት ሊቀመንበርነት ሽኩቻ እየተደረገበት ይገኛል

አምዶም ገብረስላሴ እንደዘገበው የህወሓት 12ኛ ጉባኤ መካሄድ ተከትሎ የሊቀ መንበርነት ስልጣን ሽኩቻ እየተካሄደበት ይገኛል። ኣብዛኛው የትግራይ የፌስቡክ ኣክትቪስቶች፣ ወጣቶችና ሙሁራን የህወሓት ኣባላት፣ ሌሎች ለውጥ ፈላጊ ኣክትቪስቶችና ሌሎች ፖለቲከኞች በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ። የኣርከበ በድምፅ በጉባኤው መሳተፍ ለብዙዎች የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ወደ ኣሸናፊነት የተጠጋ ቢመስላቸውም ጉዳዩ ሌላ ነው። ኣርከበ ተመልሶ የማይወዳደር መሆኑ ስላረጋገጡ የትግራዩ ኣንጃም እንዲሳተፍ በኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ ታስረው የመጡት የወረዳ ተሳታፊዎች(ማንበብና መፃፍ የማይችሉ የሚገኙባቸው ሴቶችና ገበሬዎች የሚገኙባቸው የኣባይ ወልዱ ታማኞች ) እንዲፈቅዱለት ኣድርገዋል። እንዲሳተፍ የተቀሰቀሰው ” ኣርከበ የመጣው ለሊቀ መንበርነት ሳይሆን በባቡርና ኢንዳስትሪ ከፍተኛ ስራ እንዲሰራ ነው። ስለዚ ቢሳተፍ ችግር የለውም ” የሚል ተነግሮሯቸው ነው። “ኣባይ ደራ” የሚል የበረሃ ስሙ በመጥራት ” ከመለስ ሞት በሗላ ድርጅቱ ኣጋጥሞት የነበረው ከፍተኛ ችግር ያለ ኣባይ ደራ ምርጥ መሪነት ድርጅታችን ለመበታተን ይዳርጋት ነበር ” የሚል ፕሮፖጋንዳ ተምረው ኣጥብቀው በመያዝ ኣሁንም ሌላ ኣማራጭ እንደሌለ ኣምነው ለማስፈፀም ተዘጋጅተዋል። ወፍ የለም “ኣባይ ደራ ” የኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ ሲቆጣጠሩ የቴሌው ኔትወርክ ደግሞ ዶክተር ደብረፅዮን በእጃቸው ይገኛል። ኣባይ ወልዱ የቴሌው ኔትወርክ ለመቆጣጠር ሞባይል ስልክ ወደ ኣዳራሽ እንዳይ ገባ ኣድርገዋል። እነ ዶክተር ደብረፅዮን ደግሞ የኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ እንዳይሰራ መበተን ይጠበቅባቸዋል። ለውጥ ……………… የምትጠብቁ የዋሆች እርማቹ ኣውጡ። በስብሰባው ኣንድ ተሳታፊ ህዝቡ ክፉኛ ተቀይሞናል፣ የመረጠንም ዕሬት ዕሬት እያለው ነው። ስለዚ ለውጥ የህልውናችን ጉዳይ ነው። ኣለበለዚያ ጥፋት ቅርብናት በማለት የተናገረው ደማቅ ጭብጨባ ኣስገኝቶለታል። ስብሰባው ከተያዘለት ግዜ በላይ እንደሚፈጅ ታውቋል። የመቐለ ከሓወልቲ እስከ ኣክሱም ሆቴል ያሉ ጎዳናዎች በቖልዑ ኣሸንዳ ምትክ ብሬን የጫኑ ፓትሮል የፌደራል ፖሊስና የክልል ልዩ ሃይል እየጠበቁ ነው። –

post tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s