የሕወሓት መንግስት የታጠቁ ኃይሎቹን እና ካድሬዎቹን በማሰማራት በአርማጭሆ ሕዝብ ላይ ሰቆቃ እየፈጸመበት እንደሚገኝ ተዘገበ

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው የህወሓት አገዛዝ የታጠቁ ኃይሎቹን፣ ደህንነቶቹንና ካድሬዎቹን በማሰማራት በላይ አርማጭሆ ህዝብ ላይ እንደዘመተበትና ሰቆቃ እየፈፀመበት እንደሚገኝ ታወቀ፡፡ የህወሓት አገዛዝ በታጠቁ ቡድኖቹ፣ በደህንነቶቹና በካድሬዎቹ ቁም ስቅሉን እያሳየው የሚገኘው በላይ አርማጭሆ ማሂን አቦ፣ ዳዚሆን፣ ገንበራ-አንገረባ፣ ሌዳሆ ማርያም፣ ኩርቢና በሌሎችም በርካታ መንደሮች የሚኖረውን በድህነት የሚማቅቀውን የገበሬ ህዝብ ነው፡፡ የህወሓት አገዛዝ የታጠቁ ኃይሎች፣ ደህንነቶችና ካድሬዎች በጉልበት አልገዛ ያላችውን የአርማጭሆ ህዝብ ‘የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮችን ትቀልባላችሁ’ እና ‘መረጃ ትሰጣላችሁ’ በማለት እየወቀሷቸውና እየከሰሷቸው ሲሆን በተጨማሪም አርበኞች ግንቦት ሰባትን በአካል የተቀላቀሉ ልጆቻቸውን ከበርሃ ካላስመለሱ በእነሱ ላይ ከመቸውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ እርምጃ እንደሚወስድባቸው የአርማጭሆን ነዋሪዎች እያስፈራሯቸው ይገኛሉ፡፡ የህወሓት አገዛዝ የታጠቁ ኃይሎች የአርማጭሆን ገበሬ የሚያረባቸውን ከብቶች፣ በጎችና ፍየሎች በጥይት እየጨፈጨፉ የበቀል እርምጃ በመውሰድ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡ ህዝቡ ደግሞ በበኩሉ በተቃራኒው ምሬቱ አንገቱ ድረስ ደርሶ የበለጠ ዘረኛውን የህወሓት ቡድን ተፋልሞ ነፃነቱን ለመጎናፀፍ ቆርጦ መነሳቱንና እየተዘጋጀ መሆኑን የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች በላኩልት መረጃ አስታውቀዋል፡፡ –

posted tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s