ሰበር ዜና፤እነ ዶክተር አክሊሉ ሐብቴ ባስነሱት ብጥብጥ ምክንያት ቤተክርስቲያን ተዘጋ

በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ በምትገኘው ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክስቲያን ውስጥ በዶክተር አክሊሉ ሐብቴ መሪነትና በጥቂት ግብረ አበሮቻቸው ተባባሪነት  ባለፈው ዕሁድ ቅጽረ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተነሳው እረብሻና ብጥብጥ ተባብሶ በምዕመናን ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል የደብሩ ባለአደራዎች ቦርድ ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ ለጊዜው ቤተክርስቲያኑ እንዲዘጋ መወሰኑን በዛሬ ዕለት የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

እነ ዶክተር አክሊሉ ከቀኖና ቤተክርስቲያን፣ ከደብሩ መተዳደሪያ ደንብና ከአገሪቱ ወንጀለኛ መቅጫ ህጎች በተጻረረ ሁኔታ አውደ ምህረት ላይ በገዛ ፍቃዳቸውና በማን አለብኝነት በመቆም የምዕመናንን ሰላምና ጸጥታ ከማወካቸውም በላይ በአባ መላኩ ስር ካሉ ከተለያዩ ቤተ ክርስቲያኖች ሰብስበው ያመጧቸው ደጋፊዎቻቸውን አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንዲገቡ ይቀሰቅሱ እንደነበር ተገልጾልና። በዶክተር አክሊሉ ሐብቴ አጋፋሪነት ታስቦበትና የሰው ኃይል ተመድቦለት በመካሄድ ላይ ያለው ብጥብጥና ረብሻ ከሚያስከትለው መዘዝ ለመጠቀምና የቤተክርስቲያኑን የባለ አደራዎች ቦርድ ተጠያቂ በማድረግ በግርግሩ ቤተክርስቲያኗን በአባ መላኩ መዳፍ ስር ለማስገባት መሆኑን ጉዳዩን እግር በእግር የሚከታሉ ግለሰቦች በመናገር ላይ ናቸው።

የባለ አደራዎች ቦርድ ቤተክርስቲያኗ በሰላማዊና በተረጋጋ መንገድ መደበኛ አገልግሎቷን እንድትቀጥል ለማድረግ ይቻል ዘንድ እየተደረገ ያለውን ህገ ወጥ ደርጊትና እረብሻ በማስቆም ጋጠወጦቹ ላይ አግባብነት ያለው ህጋዊ እርምጃ መውሰድ አለበት እንላለን። ከዚህም በተጨማሪ ዶክተር አክሊሉና ግብረ አበሮቻቸው የምዕመናንን ህሊና ለማቁሰልና እራሳቸውን ተበዳይ አድርገው በማቅረብ በእድሜ የገፉ አርጋዊያንና ጉዳዩ ያልገባቸውን ምዕመናንን በማደናገርና የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ለምሳሌም ቤተክርስቲያኑ ቢዘጋም ከውጭ ሆነው ተዘጋብን በማለት ሙሾ እንዲያወርዱና መንገድ ላይ ነጠላቸውን አንጥፈው እንዲቀመጡ ለማድረግ ምክር መያዛቸውን የደረሰን ጥቆማ ጨምሮ ያመልክታል። እራሱ አስረጅ የሆነውን ማሳሰቢያ ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህጋ ይጫኑ። ር.አ.ደ.ሰ.ቅ.ማ.ቤ.ክ. የባለ አደራዎች ቦርድ ያወጣው ማሳሰቢያ

 

souers  EthiopianReview.com

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s