የተቦርነ በየነ በቴዲ አፍሮ ላይ ያለው ጥላቻ መነሻ እና ከአፈርኩ አይመልሰኝ

ቤተልሄም ክፍሌ ከቨርጂኒያ

ተቦርነ በየነ በወያኔ ራድዮ ላይ ሲያገለግል የቆየና በአሁኑ ወቅት ደግሞ በኢሳት ራድዮ ላይ የሚሰራ ጋዜጠኛ ነው:: ይህ ሰው ስለሙዚቃ ያለው እውቀት የሚያስወድሰውን ያህል በቴዲ አፍሮ ላይ ያለው ጥላቻ ግን እጅጉን የሚስተዛዝብ ነው::

ቴዲ አፍሮ እምነቱን በሙዚቃዎቹ የሚያስተላልፍ ጀግና በመሆኑና ተቦርነ እንደሚያደንቃቸው ዘፋኞች ስለጥርስና ስለአይን የማይዘፍን አርቲስት ባለመሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ የተከበረ ሆኖ እንዲቆይ አድርጎታል:: ቴዲ አሁን ባለው ስርዓት በየጊዜው የሚደርስበት ጫና እና ስም ማጥፋት ሳይበግረው ዛሬ ድረስ በጥንካሬ አለ::

ከ9 ዓመት በፊት በስልጣን ላይ ያለው መግስት በቴዲ አፍሮ ላይ በየራዲዮው የስም ማጥፋት ሲጀምር ተቦርነ አንዱ አራጋቢ ነበር:: ቴዲ አፍሮ “እንደ ቢራቢሮ’ የሚለውን ዘፈን ከሰው ወስዶ እንደሰራ በማስመሰልና የፈጠራ ሰው እንዳልሆነ በማድረግ እያቀረበ በሕዝብ ዘንድ ያለውን ከበሬታ እንዲቀንስ ከወያኔ ጋር ተባብሮ ቢሰራም አልተሳካለትም::

ዛሬ ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ “እንደ ቢራቢሮ” የሚለውን ዘፈን በሸክላ ሰርቼው ነበር ሲል ሃብቴ አወሎም የተባለ ዘፋኝ በባላገሩ አይዶል የመዝጊያ ዝግጅት ላይ መናገሩን ተከትሎና ተቦርነ በየነም በፌስቡክ ገጹ ላይ የአወሎምን ንግግር ይዞ ፈንጠዝያውን ሲለቅ ታዝቤ ነው::

እንደቢራቢሮ የሚለውን የሃብቴ አወሎምን ዘፈን ደጋግሜ ሰማሁት:: የቴዲ አፍሮን በደንብ ሰማሁት:: “እንደቢራቢሮ ሁሉን አትቅሰሚ እኔ እበቃሻለሁ ተይ ፍቅሬ ስሚ” ከምትለው አዝማች በቀር የሁለቱም ዘፈኖች አይገናኙም:: በሃገራችን አማርኛ ላይ እንደቢራቢሮ እንዲህ አትሁኚ የሚለው አባባል የተለመደና በዘወትር አነጋገራችን ላይ የምንጠቀምበት አረፍተ ነገር በመሆኑ ይህ አዝማች የሃብቴ አወሎም ነው ብሎ መደምደም አይቻልም::

ቴዲ አፍሮም በቢሆን በመጀመሪያ አልበሙ ላይ የሰው ዘፈኖችን በሲዲው ላይ ማካከቱን አስመልክቱ በወቅቱ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ባሰጠው ቃለ ምልልስ ቃል በቃል ባይሆንም እንዲህ ብሎ ነበር:: “የመጀመሪያ አልበሜ እንደመሆኑ አሳታሚዎች ሲዲው ይሸጣል ብለው እምነት አይኖራቸውም… ስለዚህ አንድ ሁለት የሰው ዘፈኖችን እንድታካትት ያስገድዱሃል:: የራሴ ብዙ ሥራዎች ቢኖሩኝም የሰዎችን ዘፈኖች ያካተትኩት በአሳታሚዎች ግፊት ነው”

በወያኔ ራድዮ ላይ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር በመሆን የቴዲ አፍሮን ስም ሲያጠፋ የከረመው ተቦርነ ለሰይፉ ፋንታሁን ሰርግ ቭዲዮ ቀርጾ መልዕክት ለማስተላለፍ ጊዜውን ሲያጠፋ በቴዲ አፍሮ ላይ መንግስት ባደረገው ጫና የአዲስ ዓመትም ሆነ የመስቀል ኮንሰርት ሲሰረዝ ድምጹን ሲያሰማ አላየነውም:: የዘፋኞች ጉዳይ ሲነሳ እኔ አውቃለሁ ብሎ በቅድሚያ ፊት የሚቆመው ተቦርነ አንዳችም ቀን በቴዲ አፍሮ ላይ ይህ መንግስት የሚሰራበትን ግፍ “ግፉ ይብቃ” ብሎ ሲናገር አላየንም – አልሰማንም:: ያስተዛዝባል:: አሁን የሃብቴን ንግግር ተከትሎ ከ9 ዓመት በፊት እኔም ይህን ስል ነበር እያለ ራሱን እንደ እውነተኛ አድርጎ ለመቁጠርና ዛሬም ድረስ በቴዲ አፍሮ ላይ ያለውን ጥላቻ “ትክክል ነበርኩ” በሚል ለማሳረግ መሞከሩ እርግጥም ጥላቻው አብሮ ያደረ እንደሆነ ያሳብቅበታል:: ካፈርኩ አይመልሰኝም ነው::

ቴዲ አፍሮ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ የተወደደና የተከበረ ነው:: በተቦርነ እና በቤተሰቡ ተወደደ አልተወደደ የሚመጣበት ነገር የለም:: (ከ2 ዓመት በፊት “ቴዲም በዚህ ቁመቱ ‘ሰው በልኬ’ እያለ ዘፈነ” ሲል መድረክ ላይ ማን እንደተዋረደ ሁላችሁም ታስታውሳላችሁ)

ይልቁንም ከአዲስ አበባው የወያኔ ራድዮ ተንደርድሮ የምንወደው ኢሳት ጓዳ የተቀላቀለው ተቦርነ በቴዲ ላይ እጅህን አንሳ:: በሃገሩ ላይ በነፃነት እንዳይሰራ እየተዋከበ ያለው ቴዲ አፍሮን በቤተሰባዊ ጥላቻ ከማጥቃት ይልቅ ከጎኑ ቆመን ወከባውን የምንጋራበት ወቅት ላይ ነን:: ወያኔ የሚያሰቃየው ይበቃዋል እላለሁ::

በቀጣይ እስከምንገናኝ ቸር እንሰንብት – አለ ጋዜጠኛ::

posted tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s