በፓርላማው ውስጥ እንቅልፏን የለጠጠችው ወ/ሮ አስቴር አማረ ጋር በእንደርታ ምርጫ ተፎካካሪዋ የነበረው የአረናው አባል ስለሴትየዋ ይናገራል

ፓርላማው ውስጥ ዛሬ በርካቶች እንደተለመደው እንቅልፋቸውን ሲለጥጡት ውለዋል:: ይህን ተከትሎ የተለያዩ ፎቶዎች ሲለቀቁ ውለዋል:: ከነዚህ እንቅልፋሞች መካከል ደግሞ አንዷ ወ/ሮ አስቴር አማረ ናት:: ከ እንደርታ ትግራይ የመጣችው ይህችው የፓርላማው ተቸካይ ጠርጴዛ ላይ ተቸክላ እንቅልፏን ስትለጥጥ ነበር:: ከ እርሷ ጋር በተፎካካሪነት በአንድ ምርጫ ጣቢያ ቀርቦ በሕገወጡ ምርጫ ተሸንፈሃል የተባለው የአረናው ፓርቲ ተወካይ አቶ ሰናይ የሚከተለውን መልዕክት በፌስቡክ ገጹ አስተላልፏል::እኝህ እንቅልፋም ወ/ሮ አስቴር አማረ የተባሉት ሴት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የህወሓት የ ወረዳ እንደርታ(መቀለ ዙርያ) ተወካይ ሲሆኑ በ2002 ምርጫ በ ወረዳው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቀረቡት 7 የሚሆኑ የፓለቲካ ፓርቲዎች እኔም ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉአላውነት በመወከል ስወዳደር እኔና እሳቸቸው ከባድና እልህ አስጨራሽ ፍኩኩር ያደረግን ቢሆንም ምንም የውድድር ሜዳ፣ገለልተኛ የሆነ የምርጫ ቦርድና ፍትሓዊነት ባልነበረው ምርጫ የህወሓት ካድሬዎች 1ለ 5 በማደራጀት ያለና የሌለ አቅማቸው የሀይልም ጭምር በመጠቀም እዚ ግባ በማይባልልና በተጭበረበረ ምርጫ ፓርላማ ሊገቡ ችለዋል። በጣም እሚገርመው ነገር ወይዘሮ አስቴር አማረ የተመረጡበት ወረዳ ያልተወለዱበት፣ያላደጉበትና የማያውቁት መሆኑ ነው።ፓርላማ ገብተው መተኛታቸውም ለመረጣቸው ህዝብ ንቀት መግለጫ ዋነኛ ምስክር ነው።በአሁኑ ግዜ እኔ በፓለቲካ ልዩነቴ ምክንያት በደረሱብኝ ችግሮች ከምወዳት አገሬና ከምወደው ወገኔን ርቄ በስደት ስንከራተት እንቅልፋምዋ ግን ደልታት ፓርላማ ውስጥ ላሽ ብላለች። ወይ አገሬ

posted tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s