የአገዛዙ የቀድሞው የአየር ሀይል አዛዥ የይስሙላው ፓርላማ የአገሪቱን ሀብት ከሚያባክን ይፍረስ ሲሉ ጠየቁ –

የመቶ በመቶ ምርጫ ውጤት አያስጨፍርም የችግር ማሳያ ነው
* ሙስናና የመልካም አስተዳደር ዕጦት አገሪቱን አደገኛ ሁኔታ ላይ ሊጥል ይችላል አሉ

ጥንቅር በሃብታሙ አሰፋ

abebeየአገሪቱ ከፍተኛ ስልጣን የተሰጠው ፓርላማ ህገ-መንግስታዊ ስልጣኑን ተጠቅሞ የዜጎችን ጥቅም ማስጠበቅ ካልቻለ አሁን እንዳለበት የገዥው ፓርቲ የሚሰጠውን ተልዕኮ ለመፈፀም ብቻ ለይስሙላ ከተቀመጠ የህዝቡን አደራ መሸከም ካልቻሉ የአገሪቱዋን ሀብት ያለ አግባብ ከሚባክን ህዝበ ውሳኔ አዘጋጅቶ የማይረባ መሆኑ ህጋዊ ድጋፍ አግኝቶ ተቋሙን ማፍረስ ነው ሲሉ የአገዛዙ የቀድሞ የአየር ሀይል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል አበበ ተክለሀይማኖት በቅፅል ስማቸው ጆቤ ሰሞኑን ይፋ ባደረጉት ጥናት ላይ ገለፁ።
በ1993 ህውሐት ለሁለት ሲከፈል አንጃ ተብለው ከተባረሩት መካከል አንዱ የሆኑት ጆቤ (ሜጄር ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት) ከእነ አቶ ስየ ገብሩ አስራት በተለየ የስርዓቱ ደጋፊ ሆነው የቆዩ ሲሆን ሰሞኑን በኢንተርኔት በተሰራጨው ብልሹ አስተዳደርና የዴሞክራሲ ምህዳር በማስፋትና በተቋማት ግንባታ በሚለው ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ባቀረቡት ጥናት ስርዓቱ እየተባለሸ የሔዱ የፍትህ መጓደልና ሙስናና በሀብታምና በደሃ መካከል ያለው የተጋነነ ልዩነት ድህነት አደገኛ ሁኔታ ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ዘርዝረዋል።
አገዛዙ የሚፎክርበትን የመቶ በመቶ የምርጫ ውጤት ማሸነፉን በተመለከተ ሜ/ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት (ጆቤ) በዚሁ ጥናት እንደገለፁት “ብዙ ማንነቶች፣ በርካታ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች መልስ እንሻለን የሚሉ የተለያዩ ጥያቄዎች ባሉበት አገር አንድ ግንባር (ኢህአዴግ) እና አገሮቹ መቶ በመቶ መቀመጫውን መቆጣጠር እሚያሳየን ነገር አንድም ፖለቲካዊ ስርዓቱ ላይ ችግር መኖሩን አልያም የምርጫ ስርዓቱ ችግር እንደነበረበት ነው። መቶ በመቶ እሚባል ውጤት አስቁኝ ግን ደግሞ አደገኛ ነው ይሔ ውጤት አስቂኝ ግን ደግሞ አደገኛ ነው ይሔ ውጤት አርቆ ለሚያስብ ሰው አደጋ እንጅ የድል ምልክት ተደርጎ መቆጣጠር አይቻልም ሲሉ አጣጥለውታል የዴሞክራሲ ምህዳሩ እየጠበበ መሔድ አገሪቱዋን ወደ አላስፈላጊ መንገድ ይመራል የሚለው ይሄው ጥናት አያይዘውም ተራ ፍርድ የማግኘት ጉዳይ አይደለም ሙስናና የመልካም ያልሆነ አስተዳደር አገርን ሊበትን የሚችል ነው ይላል::
wey enqilf
የቀድሞው የአገዛዙ ጄኔራል በጥናታቸው ለስርዓቱ አደገኛ ያሉዋቸውን ዋና ዋና ችግሮች ያመላከቱ ሲሆን አንድ ገዥ ፓርቲ በእኔ አውቅልሃለሁ ብቻ መራመድ አደገኛ ሁኔታን ይጋብዛል የመንግስትና የፓርቲም ሆነ ጥቂት በግል ስም የሚንቀሳቀሱ መገናኛ ብዙሃን ተራ አድርባይነት መስተካከል አለበት በዚሁ ከቀጠሉ አደገኛ ነው ካሉ በኋላ ህግ ከሚፈቅደው ውጭ ገለልተኛ ሊሆን የሚገባው መከላከያ ሳይቀር ለህውሓት ልሳን የሆነውን ወይን ጋዜጣን በገንዘብ በተዘዋዋሪ መደጎሙ አስገራሚ ዕብሪት ነው ካሉ በኋላ በምርጫ ሰሞን በአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በሙሉ የህውሓት 40ኛ ዓመት ልደት ከፍተኛ ሽፋን መስጠቱ በተቃራኒው ለተቀዋሚዎች የሚተነፍሱበት ሁኔታ መጥበቡን አመላክተዋል።
በሕውሓት ጉባኤ ሰሞን የተወሱ ጄኔራሎች መቀሌ ላይ መታየታቸውን ሰው ነገረኝ ነገር ግን የሔዱት ልግል ጉዳይ ሊሆን ይችላል እንጂ በህግ የሚያስቆጣ ተግባር ስለሆነ የፖለቲካ ተፅዕኖ ለመፍጠር መቀሌ ገብተዋል ለማለት ማስረጃ የለም እያሉ የደረሳቸውን መረጃ በዚሁ ጥናት ያጣጣሉት የቀድሞው የአገዛዙ የአየር ሀይል አዛዥ በጥናቱ እንዳስቀመጡት “በተለይ የመከላከያ ጉዳይ አሳሳቢ ነው በታዳጊ አገር ስለምንገኝ እና ዴሚክራቲክ ተቋሞቻችን ደካማ በሆኑበት ግዜ የታጠቀው ሃይል ወይ ራሳዩ ንጉስ ወይም አንጋሽና አፍራሽ ለመሆን ይዳዳዋል አሁን የታየው ምልክት እንዳይሰፋ ከወዲሁ መጠናት አለበት የሲቪሉ ቁጥጥር መጠናከር አለበት ሲሉ ስጋታቸውን ጠቅሰዋል ። የመከላከያን ከፍተኛ ስልጣን ሙሉ በሚያሰኝ ደረጃ የተቆጣጠሩት ከአንድ የትግራይ ብሔር የተውጣጡ መሆናቸውን ተከትሎ የሚቀርበውን ቅሬታ በዚህ ጥናት ሳያነሱ አልዋል።

የቀድሞው የአገዛዙ የአየር ሀይል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል አበበ (ጆቤ) አቶ ገብሩ አስራት የህውሓትን ገበና ያጋለጡበትን<< ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ>> የተሰኘውን መፅሐፍ ተችተው አቶ መለስና ሜጄር ጄኔራል ሳሞራ የነሱትን ለመደገፍ መሞከራቸውን በዚህ ጥናት ግርጌ የግል መልእክት በሚል ለማስተካከል የሞከረቱ ሲሆን አንዳንዶች ለስልጣን እጅ መንሻ አድርገው እንደቆጠሩባቸው ያም ስህተት ነው ሲሉ ለማስተባበል ሞክረዋል። የጆቤ ዋናው የጥናት ትኩረት ዛሬም እደግፈዋለሁ ያሉትን ስርዓት ወደፊት ለማስቀጠል ይረዳል ያሉትን ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን ስርዓቱ አይታደስም ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል የሚለውን የብዙሃኑን ድምጽ ሳያካትቱ አልፈዋል።

በምርጫ 97 ቅንጅት በከፍተኛ ድምፅ አሸንፎ ህዝባዊ ድጋፍ ሲያገኝ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተሰጠው የህዝብ ድምጽ ሲሰረቅ እና ህዝቡ በየአቅጣጫቀው ተቃቀውሞ ሲያቀርብ ከህውሓት የተባረሩ ጥቂት ጓደኞቻቸውንና በድርጅቱ የተቀየሙትን ለማስተባበርና ህውሃትን እናድን የሚል እንቅስቃሴ የጀመሩ ቢሆንም በህወሃት የበላይነት የሚመራው አገዛዝ ከ193 በላይ ንፁሃን ገድሎ ሁኔታውን በመቆጣጠሩ ዕቅዳቸውን ተግባራዊ ሳያደርጉ መቅረታቸውን ነገር ግን በምርጫ የተሸነውን የሕወሃት-ኢህአዴግ አገዛዝ ለማዳን ከጓደኞቻቸው ጋር መምከራቸውን ያለ አንዳች ሀፍረት ለአንድ መጽሔት በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ መግለጻቸው አይዘነጋም።

በተቃውሞ ጎራው በኩል የስርዓቱ አደገኛ አዝማሚያ አገሪቱን ወደ አልተፈለገ ያለመረጋጋት ሊመራት ይችላል የሚለውን ስጋት የስርዓቱ ደጋፊዎች ጭምር እያሳሰባቸው መምጣቱን የቀድሞው የአገዛዙ አየር ሀይል አዛዥ ሰሞኑን ይፋ ያደረጉት ጥናት የተቃውሞው ጎራ ስጋት አግባብ እንደነበር ተጨማሪ ማስረጃ ሆኖ ይጠቀሳል::

posted tigi flate

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s