ድርቁ ከ4.6 ሚ. በላይ ህጻናትን የረሃብ ተጠቂ ሊያደርግ ይችላል ተባለ

ተመድና ኦክስፋም የተረጂዎች ቁጥር 15 ሚ. ይደርሳል ሲሉ፣ መንግስት 8.5 ሚ. ብቻ ናቸው ብሏል
ፖለቲከኞችና ባለሙያዎች ፖለቲካዊ ጥቅምን ትተን ችግሩን ለመፍታት እንረባረብ አሉ

በኤልኒኖ ሳቢያ በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ፣ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ከ4 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ህጻናትን የርሃብ ተጠቂ ሊያደርግ ይችላል ሲል ሴቭ ዘ ችልድረን የተባለው አለማቀፍ ተቋም አስጠነቀቀ፡፡350 ሺህ ያህል የአገሪቱ ህጻናት የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ችግር ተጠቂ ሆነዋል ያለው ተቋሙ፣ ችግሩ ተገቢው መፍትሄ ካልተሰጠው  በህጻናቱ ዕድገት ላይ የመቀጨጭ፣ የአካላዊና አእምሮአዊ ዝግመት ሊያስከትል ብሎም ለህልፈተ ህይወት ሊዳርግ ይችላል ብሏል፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ኦክስፋም ሰሞኑን ባወጡት ሪፖርት፣ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር እስከ 15 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል የገለፁ ሲሆን፣ መንግስት በበኩሉ፤ የተረጂዎቹ ቁጥር 8.5 ሚሊዮን ብቻ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ታዋቂ የአገሪቱ ፖለቲከኞችና የኢኮኖሚ ባለሙያዎች በበኩላቸው፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት አደጋ ላይ በሚገኝበት በዚህ አሳሳቢ ወቅት፣ ለፖለቲካዊ ጥቅም መሯሯጡን ትተን ድርቁ ያስከተለውን የርሃብና የምግብ እጥረት ችግር ለመፍታት በጋራ መረባረብ አለብን ብለዋል፡፡

 posted tigi flate
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s