“ገብጋባ ውሻ ነክሶ ለጅብ ይሰጣል” (ክፍል ሁለት) ለሀራጥቃ ተሐድሶአዊያን (ከመኳንንት ታዬ)

አንዳንዶች ከተሰበሰበው ሃሳባቸው ሲወጡ እራሳቸውን ከሰፈሩ ያጡታል።ባለባበሳቸው ባካሄዳቸው  በጠቅላላ ኑሩአቸው  የሚኖሩበት ማህረሰብን ያለ መመሳሰልን ነገር  ሲገለፅላቸው  ግራ ይጋባሉ።በዚህን ግዜ ሁሉም ነገር ለእነሱ አዲስ ነው ።ግራ በመጋባት ሄደት ውስጥ ትላንት እንዳልነቡሩና ለምን መንደሩን እንዳልመሰሉ የሚገባቸው ቆይቶ ነው። ወይ መንደሬው  በኑሮው በአብሮነቱ ጥሎአቸው  ከሄደ በኋላ ብሎም እነሱም  ከሰፈሩ መዝገብና ከሰው ልብ ውስጥ  ስማቸው ከጠፋ በኋላ ነው መኖራቸው የሚታሰባቸው። በዚህን ግዜ ቓንቓቸው እንደ ሃገሬው እንደ ሰፈሩ ህዝብ አልሆን ይላቸውና ስህተታቸው ከሰው ሁሉ ትክክል እየመሰላቸው ወጪ ወረጁን ግራ ማጋባት ይጀምራሉ።ለዚህ ያነሳሳኝ መሰረታዊ ሃሳብ  በክፍል አንድ እንዳየነው አሁንም አቅም በፈቀደ  ክፍል ሁለትን እንዲሁ እንድናይ ፈልጌ ነው ። ለመግቢያ  ያህል ይህን ነጥብ ካነሳን ወደሚቀጥለው  መንደር የፊደል እግር እያየን አብረን እናዝግም።ተሐድሶ ባንድም በሌላም መልኩ ሊሆን ይችላል።በዚህ ረገድ በሐይማኖት ስለመታደስ ተነስቶ ነገር ግን ወትሮም ቢሆን በሐይማኖት ውስጥ  እንዳልነበሩ  የሚያሳየንን ስራዎቻቸውን ሰሞኑን  በተለያዩ ቪድዮች ስናይ  ከርመናል ።እነሱንም በነጥባቸው እንይ። 1.በተለያዩ  ግዜያት  የተለያዩ ሙከራቸውን አድርገው እንዳልተሳካለቸው እና በጌታ ነበሩ  በጌታ  አልነበሩም የሚል ቋንቓ ስለመጠቀማቸው። 2.ለረጅም ግዜ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ቆይተው በጣም ብዙ ነብሳትን (6 ሚሊዮን) ከቤተክርስቲያን አስወጥተው  ለፕሮቴስታንቶቹ እንደገበሩ 3.አሁን እነሱ ያነሱት ተሐድሶ የሚለው  ነጥብ ከዚህ በፊት ደቂቀ እስጢፈኖሳዊያን በሚል መጠሪያ በተነሱ ወንድሞች ተነስቶ እንደነበር እና እነሱም እስከዛሬ ድረስ ለማሪያም  እንደማይሰግዱ እና የመሳሰሉትን ነው ። እንግዲህ ከላይ ላነሱት ነጥብ በእኔ ብቻ ብዙ የሚገለፅ ባይሆንም፤ ግን አኔ እንደ ቤ/ክርስቲያን ልጅነቴ አጠገባቸው ብሆን ለእነሱ የምመልሰውን  ከአንባቢያን ጋር ለመጋራት ያህል  ይህን ልበል። ሀራጥቃ ተሐድሶአዊአን (ተዋስያን) በተራ ቁጥር. አንድ  ስላነሳችሁት ጥያቄአችሁ እንደመለስ የምወሰወደው አንድ የመስሃፍ ቅዱስ ቃል ነው ።ይኸውም ።የሐዋርያት ስራ  ም5ቁ34-39 ባለው ላይ ሐዋርያትን  ለማጥፋት አይሁድ በሚመክሩበት ግዜ ገማልያል የሚባል የህግ ሰው  ሲያስረዳ  በተለያየ ግዜያት የተለያዩ ሰዎች ተነስተው ከእግዚአብሔር ስላልነበሩ እንደጠፉ እና እነዚህም(ሐዋርያቱን ማለቱ ነው)  ከእግዚያብሔር ካልሆኑ ይጠፋሉ እንዳለ ያስረዳል። ይህን ስታነቡ በቀላሉ መልሱን የምታገኙት ይመስለኛል ። ወደፊትም ትነሳላችሁ። ከእግዚያብሔር ስላልሆናችሁ አይሳካላችሁም ። ትጠፋላችሁ።ቤተክርስቲያናችን  ግን ለዘላለም ትኖራለች።ጥንትም በቤተክርስቲያኗ ወሰውጥ ስማችሁ ከሰፈሩ አልነበረምና አሁንም ወደፊትም  አትኖሩም።ማስተዋል የላችሁም ።በቤ/ክን ውስጥ በነበራችሁበት ግዜ በፆሙ የላችሁም።በፀሎቱ የላችሁም። በጠቅላላው በእምነት ውስጥ አልነበራችሁም ።ለዚህ ከእግዚያብሔር ያልሆነ ስራ ስትሰሩ አማንያንን  እያሳታችሁ ነው እንጂ ኢ አማንያንን  ወደ እምነት እያመጣችሁ አደለም።ኢትዮጲያ በ4ተኛው ክፍለ ዘመን  ክርስትናን ስትቀበል  በቅጥታ ከሐዋርያት  በተማረችው ትምህርት ትውልዱን ስታስተምር ይኸው እስከ ዛሬ አለች።ታዲያ  ዛሬ እናንተ ከነማን በተማራችሁት ትምህርት ዛሬ ቤተክርስቲያኗን ማደስ ፈለጋችሁ?። ስለዚህ ነው ከእግዚያብሔር አደላችሁም። ስላልሆናችሁም  በየግዚያቱ አፈር ልሳችሁ ብትነሱም  አይሳካላችሁም።ትጠፋላችሁ የምንላችሁ። 2.በሁለተኛ  ላይ ያነሳሁት ነጥብ  የርዕሴም ምክንያት ነው።ምንዛሬውም ብዙ ነው። ግን እንዲህ በቀላሉ እንየው ካልተባለ በስተቀር።ነገሩ እንዲህ ነው ።የስነ ምግባር እኩለነታቸው እራሳቸውን ከተግባር ጋር እንዲያጣምሩ ተፈጥሮ ክህሎቱን ያላደለቻቸው ለሚኖሩበትና ህይወትን ለሚጋሩት ማህበረሰብ የተባይ ያህል ያሳክካሉ።ላሉበት አካባቢ ቀውስ የማይሆኑበትና ሁነቶች በተፈጥሮም ሆነ በስርአት ለሰው ልጆች ምቹ ሆነው እንዳይቀጥሉ በመንገድ ላይ እንዳዋራ  በመበተን ማንም አጣርቶ እንዳያይ  ምክንያት በመሆን የብዙዎችን መንገድ ማሰናከላቸው አውነት ነው። ለዚህም ነው ዛሬም ድረስ ቤ/ክ መረበሿ፤ለዚህም ነው ዛሬም ድረስ የተከተሉት መንገድ ስህተት ያለበት እየመሰላቸው ዘለው ከመናፍቃኑ ጎራ የሚገቡ ቄስ፤ሞለኩሴ፤ዲያቆን መእምን  የመኖራቸው ሚስጥር።እናንተም የምትሉን ይኼና ይኼን መሰል ጉዳየዮች እንዲፈፀሙ ለተግባሩ መሳከት የበኩላችንን አድርገናል ነው።ለምን ብለን አንጠይቃችሁም።አላማችሁ ስለሆነ።በመሆኑም ነው፤ መዕመናን  ከሚኑሩበት ቅድስት ቤተክርስቲአን  አስወጥታቸሁ ለማያቁትና  ወደማያቁት አለም የአውሬው መንፈስ ተካፋይ እንዲሆኑ ስታደርጉ አልፈራችሁም።እስቲ አስቡ እነኚ ወገኖች  ክርስቲያኖች ናቸው ።በእመነታቸው እጅግ ብዙ      ኢ- አማንያን አሉ።እውነት አላማችሁ”ባልበላውም ጭሬ ደፋዋለሁ እንዳለችው ዶሮ” ካልሆነ በስተቀር ስለምን ኦርቶዶክሳዊያን ላይ  መዝመት አስፈለገ።የምዕራብአዊያን ተላለኪዎች ባትሆኑ ኖሮ  ታተኩሩ የነበረው የኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ክ ላይ ባልነበር።  ሰዎችን ክርስትናን እንዲያቁ ለማድረግ ቢሆን ትጋታችሁ የምትዘምቱበትና ጦራችሁን የምትሰብቁበት ቦታ  ቤ/ክ ባልሆነች ።ግና የኔ የምትሉት አላማ የላችሁም።ሲጀመርም ተገዝታችሁ ነው።በአዳራሻችሁም የምትሉት አሁንም አሁንም አሜን! እየሱስ ጌታ ነው የመሳሰሉትን ነው። ምክንያቱም  ስማችሁም ክርስቲያን ቢሆን  በቤተክርስቲያን ግን አልነበራችሁም፡፤ስማችሁ ከመንደሩ ሰዎች ጋር የለም ያልኩት ለዛ ነው።ለዚህ  ገና ጌታን(በእናንተ አጠራር) አዲስ እንዳገኛችሁት ስትወበሩ ለሰማ ያሳፍራል።መነሻና መድረሻችሁ ግራ  ያጋባል።ምክንያቱ ማንን መጥቀም ማንን መጉዳት እንኳን  እንደሆነ አይታውቅም።ነገር ግን የኢ/ኦ/ተ/ቤ ለአም እንኳን አስኪደንቅ ድረስ  ፆም፤ፀሎት፤ስግደት፤መመፅወት፤ቅዱሳንን ማክበር ፤በስማቸው ቀዝቀዛ ውሃ ማጠጣት፤ምግባር ፤አንድነት አብሮ መብላት፤ ብቻ ቆጥሬ ነግሬ የማልጨርሰውን አባይት ሁነቶችን በውስጧ ይዛ ትውልድን እየቀረፀች ኢትዮጲያን ዘመን ያሻገረች ንፅህት ሐይማኖት ነች።እንዳለመታደል ሆኖ እንጂ እናተም  ነበራችሁበት ።ነገር ግን ክፍል ስትቀይሩ ማስተዋልም ቀየራችሁና የክህደት ጅራፋችሁን አጮሃችሁባት።አዲሷም አደለም።የመጀመሪያም አደላችሁም። 3.ስለ ደቂደ እስጢፈኖስ ያነሳችሁት ነው።ዋቢ ይሆነናል  የምትሉትን ሁሉ መሞከሩ መልካም ነው።ጥያቄው ያነሳችሁት መፅሃፍ መፅሃፍ ቅዱስ ውጭ አልሆነባችሁም ወይ ነው? ምክንያቱም ወደ ቅድስት ቤ/ክ ስትመጡ ለማሳሳት  የምትጠቀሙበት ቃል አንዱ ቤ/ክ ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጭ ትጠቀማለች ነው።ይገርማል።ማስተዋላችን ውበታችን ነው።ማስተዋልን የማይጋፋ ማንነት እራስንም ሆነ ማሕበረሰብን የሚጠቅም የሞራል ድጋፍ ከውስጡ ይመነጫል።ለወገንም ለሐገርም የማይቆረስ መስዋትነት  ለመክፋል ያለነጋሪ የሚጠበቅበትን  ለመክፈል ዝግጁ ነው።ክህደት የሚያበዛ እኔነት ሐሳቡ እራሱ ብቻ ነው።ሐገር፤ወገን፤ቤተሰብ ፤መጪው ትውልድ ማለት ከቶም አይታሰብም።ለዚህ እናንተ በፈለጋችሁት መንገድ መሮጥ መሮጥ  መድረሻ የለ መነሻ የለ።ይሁን እናንተ(ሓራጥቃ ተሐድሶአዊያኑ) ያነሳችሁት መፅሐፍ እናንሳና በተሳሳተ ግምት የተሳሳተ ቦታ ቆርጣችሁ በመቀጠል ያሳመነችኋቸው ወገኖች ድንገት ከእንቅልፋቸው ቢነቁ። ነገሩ እንዲህ  ነው ።ሰባኪው(ሓራጥቃ ተሐድሶዊያኑ)ማለቴ ነው።በፕሮፈሰር ጌታቸው ሐይሌ ስለተፃፈው  በህግ አምላክ ደቂቀ እስጢፋኖሳዊያን  አንስቶ በዘመኑ የነበሩ እንኚህ ወገኖች  ከላይ እንዳልኩት ለማሪያም እንደማይሰግዱና አምልኮታቸው አሁን እነሱ ነን እንደሚሉት አይነት እንደነበር በዚህም  በጣም እጅግ  የሚያሳቅቅ  በደል እንደደረሰባቸው   ደጋግሞ ለመጥቀስ ሞክሮአል ።አስቲ ከመፅሐፍና ስለመፅሐፉ ጥቂት  ወስደን ጥቂት እንበል። አውነት ነው። የመፅሐፉ ስምና የመፀሐፉ ደራሲ።ሌላው ጉዳይ ግን አብረን  ጥቂቱን እንመልከት። ደቂቀ እስጢፋኖኦሳዊያን  ተነስተው የነበሩት ሉተር ከመነሳቱ ሰላሳ አመት  በፊት በአፄ ይስሐቅ ዘመነ መንግስት 1406-1421  ሲሆን የመጀመሪያ በሐይማኖታቸው በጣም ጥብቅ የነበሩና ሁሉን  በቦታው የሚሰጡ እንደነበር ያወሳል።እርግጥ ነው መነሻቸው ላይ ለመቤታችን  እና ለመስቀሉ መስገድ አይገባም የሚል ከፉ ትምህርት ነበረባቸው ።ይሁንና  በፀሎት መፅሐፋቸው ሳይቀር የእመቤታችን ስዕል ይዘው ይዞሩ እንደነበር መፅሐፉ ያስረዳል ።ኋላ ላይ ግን በወቅቱ የነበረው ንጉስ ለእኔ አትስግዱም  እያለ ምክንያት እየፈለገ ሲያሳቃያቸው እነሱም ለአብ፤ ለወልድ፤ ለመንፈስ ቅዱስ፤ ብቻ ስግደት  እንደሚገባ  ይነግሩት ነበር።ይህን ምክንያት  አድርጎ በወቅቱ ያለው ጳጳስ  እንዲገዝታቸው ሲከሳቸው እንደምክንያት  ሲናገር “እኔንም አያከብሩኝም  ለእመቤታችንም አይስግዱም  “የሚል ነበር።ጳጳሱም  ይህ የሚባለው አውነት  ነው ወይ? ብለው ጠየቐቸው፤ እነሱም ለሱ አንሰግድም ያልነው አውነት ነው። ስለ እመቤታችን ያለው ግን ስህትተ አለበት ብለው መለሱ።እንዲያ ካላችሁ ተነሱና  አስቲ አብረን ለእመቤታችን  እንስገድ ብሎ አብረው ሰግደዋል።በዚህም የትግራዩ ንጉስ ያለውን ግዝት ባለማድረጋቸው አሳቸውም አብረው ተግዘዋል።አስቲ ለአብነት  ያህል ከመፅሐፍ  ጥቂት ጥቂቱን ወስደን እንይ። “አለ መስገድ  እንደ አለማክበር አያዩትም።እመቤታችንን ማክበራቸው አያጠራጥርም።”ምስለ ፍቅሩ ወልዳ”የሚባለውን ቅድስት ማርያም ልጇን(የጌታችንን)ታቅፋ የሚያሳየውን ስዕል በየመፅሐፎቻቸው ውስጥ ስለው ተገኝተዋል። በራሳቸው በአባ እስጢፋኖስ ገድል ወስጥም አለ።(ገፅ 22ተመልከት)በዚያ ላይ እንደ ሌሎች ሁሉ የቅዱስ ኤፍሬምን ውዳሴ ማሪያም  እና የቅዱስ ያሬድን አንቀፀ ብርሃን ይደግሙ ነበር።እነዚህ  ሁለት ድርሰቶች እመቤታችንን የሚያደንቁና የሚያመሰግኑ በየአንቀፁ፡ሰአሊነ ቅድስት”(ቅድስት ሆይ ኀጢያታችንን ይቅር እንዲለን ከልጅሽ ከወዳጅሽ ዘንድ አማልጅን) የሚል ንባብ ያለባቸው ናቸው።ጳጳሱም ለቅድስት ድንግል ማርያም ብትሰግዱ ስሕትተ አይሆንባችሁም ብለዋቸው  አብረው መስገዳቸውን ራሳቸው መስከረዋል”ደቂቀ አስጢፋኖስ ገፅ30 አንቀፅ 4 ይመልከቱ። ማስረጃ ሁለት።ደቂቀ አስጢፋኖስ ገፀ140 ላይ በፀሎታቸው  ግዜ የፀለዩት ፀሎት”የ አምላክ እናት ሆይ እነሆ ከምህረትሽ ጥላ ስር ተደግፈናል።በጭንቃችን ግዜ ልመናችንን አትናቂ”። አንቀፀ ሁለት  መስመር 10 ይመልከቱ። ማስረጃ ሶስት፤-  ከደቂቀ አስጢፋኖስ ገፅ152 ንጉስ በተናገራቸው ቃል ተቆጥተው ከነሱ ውስጥ አንዱ እንዲህ አለ።”የትምክህታችን አክሊል የሆነች የማርያም ፍቅርና የዚህን የነፍስ አባት የምዕዳን ቃሉን አስታውሼ ነው እንጂ እንኳን በትርን፤ መራቆትን፤ ረኀብን፤ውሃ ጥምን በመፍራት ላደርገው ቀርቶ ጦር አንጀቴን ቢዘረግፈውእንኳን አላደርገውም። እንግዲህ ለአብነት ያህል ይህን  ጠቀስን እንጂ ብዙ ማለት ይቻላል። ምን አልባት መፅሐፉን አለቆቻችሁ ሳይፈቅዱላችሁ ያነሳችሁት እንደሆን ወይ አብሮአችሁ ያሉት ቢሰሙም አይሰሙም  ወይ ሰባኪ ተብየውም  እንዲሁ ይጮሐል እንጂ አይሰማም። አያውቀወም። እንጂ ጠቅላላ ይዘቱን ብታገናዘብ ኖሮ እናንተን(ሃራጥቃ ተሓድሳዊያኑን(ተዋስያኑን) አይመለከትም። በጥቅሉ የመጀመሪያ አጥማቂዎቻችሁን እና ሰባኪዎቹን  እና ተሰባኪዎቹን ሳስብ ይህቺ ከዚህ በታች  ታሪክ እንዳስብ አድርጎኛል ።ለሁሉም ለንስሐ ግዜ  ይስጣችሁና ለመመለስ ያብቃችሁ። በ አንድ ሃገር ሶስት መስማት  የተሳናችው ሰዎች ይኖሩ ነበር።እነኚ ሰዎች ኑሮአቸው አንደኛው የንጉስ ከብቶች ጠባቂ ፤አንደኛዋ  ደግሞ የባለጠጋ ቤት ሰራተኛ  ሆና በተለያየ ጉዳይ የምታገለግል  ስትሆን ሶስተኛው ዳኛ ነበር።ታዲያ ከእለታት በአንዱ ቀን  ከብት ጠባቂው  በድንገት እንቅልፍ ይወሰወደውና ከብቶቹ ይጠፉበታል። በዚህን ግዜ ደንግጦ ተነስቶ ፍለጋ ላይ  እያለ ይህቺኛዋን ሴትየዋ ልጇን ከጎኗ አስቀምጣ የጌታዋን  መሬት እየቆፈረች እያለች  ይህ ጆሮው የማይሰማ ሰውዬ ሴትየዋን እባክሽ የጌታዬ ከብቶች ጠፉብኝ  እና አይተሻቸው እንደሆነ ንገሪኝ ፤ እዛ ውስጥ አንድ እግሩ ሰባራ የሆነ ወይፈን አለኝ። እሱን አሰጥሻለሁ ይላታል። አሷም መስማት የተሳናት ነበረችና  ምን እንዳለ ስላላወቀች እጇን ታወናጭፋለች ። በዚህን ግዜ ወደዛ ሄደዋል ያለችው ይመስለውና  መንገዱን ተከትሎ ሲሄድ ከብቶቹን ያገኛቸዋል።ወደያው ደስ እያለው ወይፈኑን  እየጎተተ ይመጣና በይ እንቺ  ብሎ ቃል በገባው መሰረት  ሊሰጣት ቢል፤ እሷ ደግሞ  አንቺ ነሽ የሰበርሽው ያላት መስሎአት እኔ አደለሁም የሰበርኩት እአለች ። ሁለቱም ሲጯጯሁ መንገደኛ ይደርስና የሁለቱንም ነገር ሰምቶ ሁኔታውን  መዳኘት ስለማይችል  ይዞአቸው  ወደ ሃገሩ ዳኛ ያቀርባቸዋል። እዛ ሲደርሱ ዳኛም መስማት የተሳነው ነው ግን ዳኛ ነው ። ከዛም ነገራችሁን አስረዱ ይልና ለሰውየው እድሉን ይሰጣል።  ሰውየውም  ቃል የገባውን ወይፈን ሊሰጣት ቢል እንቢ እንዳለች ያስረዳና ቁጭ ይላል። ሴትየዋ  በማስረዳት ላይ  እያለች ልጇ ያለቅሳል ። በዚህን ግዜ ከጀርባዋ እያወረደችው  ነገሯን  በማስረዳት ላይ እያለች  ዳኛው በመሃል  ላይ ያስቆማትና  በይ በቃ ዝም በይ፤ ብሎ ወደ ሰውየው ዞሮ” ይህ ልጅ ደሙም ደም ግባቱም አንተን ስለ ሚመስል ከዛሬ ጀምሮ  ሶስት እንቅብ ስንዴ በየወሩ ስፈርላት ብሎ ፈረደ ይባላል።  እናንተም………..ቢሆን ኖሮ። ይቆየን

posted tigi flate

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s