መልካም አስተዳደርን እውን ለማድረግ ድክመትንና ስህተትን ከመቀበል ያለፈ እርምጃን ይጠይቃል” – ሸንጎ – See more at: http://www.zeabesha.com/amharic/archives/48192#sthash.kI6cpFJe.dpuf

በአለፉት ቀናቶች በልዩ ልዩ የሚዲያ ዘርፎች ሲስተናገድና ትችት ሲሰነዘርበት የከረመው ጉዳይ በቅርቡ የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ስለመልካም አስተዳደርና ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ለመቀራረብ ፍላጎት እንዳላቸው በሰጡት መግለጫ ዙሪያ ነበር። ትልቁ የአንድነት ሀይሎች ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ጉዳዩን ተከታትሎና ሊያስከትል የሚችለውን ጥቅምና ጉዳት በመመርመር የሚከተለውን አቋም ወስዷል። በአገሪቱና በሕዝቡ ላይ የደረሰው በደል ተጠራቅሞ ወሳኝ ደረጃ ላይ በመድረሱ የተነሳ መንግስት እራሱ በአስተዳደሩ ውስጥ የሚታዩ ጉድለቶችን የሚያጠና የባለሙያዎች ቡድን ለማቋቋም ተገዷል።ሸንጎ በመንግስት የተቋቋመው ቡድን ሰፊ ጥናት አድርጎ ያቀረበውን ዘገባ ይፋ በማውጣቱ ነቀፋና ተቃውሞ ባይኖረውም የተደረሰበት ጥናትና የቀረበው ሃሳብ በተግባር መገለጽ እንዳለበት ፣ያ ካልሆነ ግን ለይስሙላና ለማደናገሪያ ብሎም ጊዜ መግዣና ተቃውሞን ለማለሳለስ የተደረገ እርምጃ ሆኖ እንደሚቀር ከወዲሁ ለማሳሰብ ይወዳል። አሁን አገዛዙ በይፋ ያወጣው ውስጣዊ ድክመት ሸንጎና የተቃዋሚው ጎራ ላለፉት ዓመታት እያነሱና እያጋለጡ ሲታገሉበት የነበረ ፣ ሕዝቡም በአንክሮ የሚያሰማው ብሶት በመሆኑ በስልጣን ላይ ያለው አካል ጥፋቱንና ድክመቱን ከማመን ሌላ አማራጭ ስላላገኘ ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም በተወሰነ ደረጃ ያለበትን ውስጣዊ ድክመት ለመቀበል ተገዷል።እዚህ ላይ መቀበል ማለት መፍትሔ መሻትና በተግባር መግለጽ እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል።

posted tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s