ለኩላሊት ሕመምተኞች የተሰበሰበው ገንዘብ… እያወዛገበ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ

በቅርቡ የተቋቋመው የኩላሊት እጥበት ማዕከል፣ ለኩላሊት ሕመምተኞች የእጥበት ህክምና ለመስጠት በኤስ ኤም ኤስ እያሰባሰበ ያለው ገንዘብ፣ “ለታለመለት ዓላማ አልዋለም”፤ መባሉ እያወዛገበ ነው፡፡ ባለፈው አርብ ጥቅምት 26 ሬዲዮ ፋና ባስተላለፈው ዘገባ፣ ማዕከሉ ለኩላሊት ህመምተኞች የእጥበት አገልግሎት ለመስጠት ከህዝብ ከሚሰበሰበው የበጐ አድራጐት ገቢ፣ ኮሚሽን እየከፈለ መሆኑን ጠቅሶ ድርጊቱ ህገወጥ ነው ብሏል፡፡ 524 ሺህ ብር ኮሚሽን ተቀብያለሁ ያሉ ግለሰብም በዋቢነት ማቅረቧ ታውቋል፡፡ የማዕከሉ የቦርድ አባልና የገቢ አሰባሳቢ ኦፊሰር ደራሲና ዳይሬክተር አንተነህ ሃይሌ በበኩሉ፤ “የኩላሊት እጥበት ማዕከሉ በSMS ከህዝብ ከሰበሰበው 7 ሚሊዮን ብር ውስጥ 4 ሚሊዮን ብር ተመዝብሯል የሚል ዘገባ በሬዲዮ ፋና መሰራጨቱን ጠቁሞ፤ 7 ሚ. ብር የሚለውን ከየት አምጥቶ እንዳወራ አናውቅም ብሏል፡፡ “የፋና ሃሰተኛ ዘገባ የህዝቡን በጐነት የሚረብሽና የህሙማንን ህልም የሚያጨልም ነው፤” ሲልም ተችቷል፡፡“የፋና ዘገባ እውነትን ማዕከል ያደረገ አይደለም፤” ያሉት የማዕከሉ የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር ሳሙኤል ይርጋ፤ “ለሚሠራው ሥራ የሚከፈል ኮሚሽን የለም” ሲሉ አስተባብለዋል፡፡ማዕከሉ ከገራዶ ፊልም ፕሮዳክሽን ጋር ስለፈጸመው የሥራ ውል የተጠየቁት ሰብሳቢው፣ “ማዕከሉ ሥራ ሲጀምር ምንም ገንዘብና የሰው ሃይል ስላልነበረው የኤስኤምኤሱን አጠቃላይ ሥራ እንዲያከናውንና ለእድለኞች ሽልማት ከገቢው ከ10 በመቶ ያልበለጠ ሒሳብ እንዲወራረድለት ውል ፈጽመናል” ብለዋል፡፡

addisadmassnews

posted tigi flate

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s