ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፊታችን ማክሰኞ በአውሮፓ ፓርላማ ንግግር ያደርጋሉ ተባለ

(ዘ-ሐበሻ) የትጥቅ ትግሉን መንገድ መርጠው ታግዬ አታግላለው ብለው አስመራ የወረዱት የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፊታችን ማክሰኞ ዲሴምበር 2 በአውሮፓ ፓርላማ ንግግር እንዲያደርጉ መጋበዛቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ::

ከአስመራ ወደ ብራሰልስ እንደበረሩ የሚነገርላቸው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለሕዝብ ክፍት በሆነው በዚሁ የአውሮፓ ፓርላማ ላይ ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት በወ/ሮ አና ጎሜዝ ነው ተብሏል:: በዚህ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ መገኘት ለሚፈልጉ – የአውሮፓ ነዋሪዎች በምርጫ 97 ወቅት የአውሮፓ የምርጫ ታዛቢ ለነበሩት ወ/ሮ አና ጎሜዝ ደብዳቤ
ፕሮግራሙ ለሕዝብ ክፍትና ነፃ በመሆኑ አስቀድማችሁ:-

  • ስማችሁን
  • የተወለዳችሁበትን ቀን/ ወር/ ዓ.ም
  • ዜግነታችሁን
  • እና የፓስፓርት ቁጥራችሁን በ Anamaria.gomes@europarl.europa.eu በመላክ መመዝገብ እንደሚቻል የደረሰን መረጃ ጠቁሟል::

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሚገኙበት በዚሁ የአውሮፓ ፓርላማ ላይ ለመገኘት ምዝገባው እስከፊታችን አርብ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን በፓርላማው ላይ ማክሰኞ የሚገኙ ሰዎች ፓስፖርት ወይም ሕጋዊ ወረቀት መያዝ እንደሚኖርባቸው ተጠቁሟል:: የኢትዮጵያ አገዛዝ ፕሮፌሰር ብርሃኑን አሸባሪ እንዲባሉለት የየሃገራቱን መሪዎች በሚለምንበት በዚህ ወቅት ፕሮፌሰሩ በአውሮፓ ፓርላማ መጋበዛቸው ለስርዓቱ ትልቅ የፖለቲካ ኪሳራ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ::

souerc .zehabesha.

posted tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s