ወያኔዎች ይገድላሉ ያገዳድላሉ | ይገረም ዓለሙ

ኢትዮጵያዉያን በፍቅር በሰላምና በአንድነት ከኖርን በኢትዮጵያ ሥልጣነ መንበር ላይ መቆየት አንደማይችሉ ገና ሀ ብለው ትግል ሲጀምሩ የተረዱት ወያኔዎች ለዚህ መላ ዘይደው እቅድ ነድፈው ነው የተነሱት፡፡ በሀይማኖት በቋንቋ በጎሳ በአካባቢ ወዘተ በማለያየት በኢትዮጵያውያን መካከል ፍቅር ሰላምና አንድነት እንዳይኖር ማድረግ የዚሁ እቅዳቸው አንዱና ዋናው ክፍል መሆኑን ላለፉት ሀያ አራት ዓመታት የፈጸሙትና አሁንም የቀጠሉበት ተግባራቸው በቂ ምስክር ነው፡፡ የጥላቻ መርዝ እየረጩ ርስ በርስ ያናክሳሉ፣ አጀንዳ እየሰጡ በሰላምና በፍቅር አብረው የኖሩ ዜጎች በጥርጣሬ አንዲተያዩ ያደርጋሉ፤ ከዚህ አልፎም ራሳቸው የሚገድሉት አልበቃና አላረካ ሲላቸው ለአመታት አብረው የኖሩ ርስ በርስ እንዲገዳደሉ ያደርጋሉ፡፡

ይህ በ1984 ዓም በበደኖ ወተር አርባ ጉጉ ወዘተ ተጀምሮ ጊዜና ሁኔታ እየጠበቀ በበብዙዎቹ የሀገራችን አካባቢዎች ተግባራዊ ሲደረግ የኖረ የወያኔ እቅድ ሰሞኑን ደግሞ ጎንደርን ወር ተረኛው አድርጓል፡፡ በስፍራው የተፈጸመውና በማህበራዊ ድረ ገጾች ተሰራጭቶ የተመለከትነው ግድያ እጅግ ሰቅጣጭ ነው፡፡ ለምንም ዓላማ ይሁን በማንም ይፈጸም አንዲህ አይነቱ የግፍ አገዳደል ለዛሬ የሚወገዝ ቀን ሲወጣ ደግሞ ለፍርድ የሚያስቀርብ ነው፡፡ ለነገሩ እኛ ነን እንጂ ሁሌ አዲስ የምንሆን ወያኔዎች ለደደቢቱ ዓላማቸው ስኬት ማናቸውንም ነገር ከመፈጸም ወደ ኋላ እንደማይሉ በሀያ አራት ዓመታት የአገዛዝ ዘመናቸው ያቀዱትንና የቻሉትን ሁሉንም ነገር አድርገው አሳይተውናል፡፡አሁንም እያሳዩን ነው፡፡ ለወያኔ ከምንም ነገር ቀዳሚው በሥልጣን መቆየት ነውና፡፡

ሀገር ቆርሰው ሰጥተዋል፤ አሁንም መሬት ለመስጠት እየተዘጋጁ ነው፤ዜጎችን ገድለዋል፤አገዳድለዋል፤አስረዋል አሰቃይተዋል፤ንብረት ዘርፈዋል ሌላም ሌላም፡፡ ሥነ ልቦናችንን ተረድተዋል ደካማ ጎናችንን አውቀዋልና፡ በየግዜው አዳዲስ ነገር እየፈጠሩ ሲግቱን እየተቀበልን ርስ በርስ ከመጠላላት አልፎ ይሄው ሰሞኑን ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ እንደተፈጸመው ርስ በርሳችን አንገዳደላልን፡፡ በዚህ አድራጎታችንም የወያኔን የደደቢት ትልም በዘላቂነት አንዲሳካ መሳረያ በመሆን ምቹ ሁኔታ አንፈጥራለን፡፡

በግልጽ የሚታወቀው እስከዛሬ ያልተለወጠው ስማቸውም የሚያረጋግጠው የወያኔ የደደቢት ትልም የትግራይ መንግሥት መሆን ነው፡፡ ኢትዮጵያን በሙሉ የመያዝ በለስ ሲቀናቸው አንድም ሁሉን መያዝ ከቻልን ለምን በጠባብ እንወሰናለን ብለው ሁለትም ኢትዮጵያን ጎጆ መውጫና መበልጸጊያ ብሎም የዘላቂ ዓላማቸው ማደላደያ ለማድረግ እንጂ የተነሱበትን ዓላማ የሻሩ ላለመሆናቸው ድርጊቶቻቸው በቂ ማስረጃዎች ናቸው፡፡

የሚያሳዝነው ወያኔዎች ለከፋፍለህ ግዛው ስልታቸው ማስፈጸሚያ የፈጠሩዋቸውን ስመ ድርጅቶች የሚመሩ ሰዎች ራሳቸውን ከመጥቀም የዘለለ ምንም ዓላማና ግብ ሳይኖራቸው ለወያኔ የደደቢት ህልም አስፈጻሚ ሆነው መሰለፋቸው ነው፡፡ ሌላው ወያኔን በመቃወም የተሰለፈው ደግሞ ጠንክሮ በመታል ወያኔን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ማንሳት መቻሉ ቢቀር የወያኔን ጥፋት ለመግታት የሚያስችል እንቅስቃሴ ከማድረግ በወያኔ ከፋፋይ መርዝ ተመርዞ ሆድና ጀርባ ሆኖ በመኖር የሚቃወመውን ሀይል እድሜ የሚያራዝም ተግባር ይፈጽማል፡፡አንዳንዱም ለወያኔ የማገዳደል እቅድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአስፈጻሚነት ያገለግላል፡፡

ወያኔዎች ገና ደደቢት እያሉ ያወጡትን እቅድ ደረጃ በደረጃ ግዜ እየጠበቁና የእኛን ሙቀት እየለኩ ተግባራዊ ሲያደርጉ በፈጻሚነት የምንሰለፈው እኛው ነን፡፡የሕዝቦችን ራስ በራስ የማስተዳደር መብት ከወረቀት ጌጥነትና ከፕሮፓጋንዳ መሳሪያነት ተሻግሮ ተግባራዊ አለማድረጉን ሀያ አራት አመታት በተግባር ያየነው ነው፡፡ ከህውኃት ውጪ ያሉት የኢህአዴግ አባል የሚባሉት ድርጅቶች ብአዴን ኦህዴድ ደአህዴንም ሆኑ አጋር የሚሰኙት ድርጅቶች የያዙዋቸውን ክልሎች በነጻነት እንደማያስተዳድሩ በግልጽ ይታወቃል፡፡በዚህ ሁኔታ በይስሙላ ፌዴራሊዝም ሀገሪቱን እየገዛ ያለ አንድ ፓርቲ ለአመታት መለስ ያላገኘን የቅማንት ጥያቄ ዛሬ ድንገት ተነስቶ ጥያቄአችሁ ተቀባይነት አግኝቷል ራሳችሁን በራሳችሁ ታስተዳድሩ ዘንድ ተፈቅዷል ሲል ጎንደሬው “ጠርጥር ከገንፎም አለ ስንጥር” በአንድ ክልል ውስጥ ከዞንም ያነሰ አካባቢ የራስ አስተዳደር መብት ተጎናጽፎ ከወያኔ ፍላጎትና አመራር ውጪ ራሱን ማስተዳደር ይችላል ተብሎ ታምኖ ለዘመናት አብረው በኖሩ ተጋብተው ተዋልደው ክፉንም ደጉንም አብረው እያሳለፉ የአንድ አካባቢ ነዋሪዎች መካከል አለመግባባት መፍጠሩ፤ አለመግባባቱንም ለዘመናት በዘለቀው አካባቢያዊ ዘየ ለመፍታት ከመሞከር መሳሪያ ወደ መማዘዝ ተኪዶ ዘግናኝ ግድያ መፈጸሙ ወያኔ ለዓላማው ስኬት ምን ያህል እኩይ ተግባር አንደሚፈጽም ያሳየ ነው፡፡ በአንጻሩም መለስ ብለው የኋላውን ማስታወስ ቀና ብለውም የዛሬውን ማሰብ የማይችሉ ሰዎችን ወያኔ በመብራ እየፈለገ እንዴት እንደሚጠቀምባቸው አሳይቶናል፡፡

የውድቀታችን ክፋት የመክሸፋችን ስፋት በወያኔ እኩይ ሴራ ትናንትም ሆነ ዛሬ የሰው ልጅ የገዛ ወገኑን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገድል ጠብ የሚያበርድ ሽማግሌ፣ እርቅ የሚፈጥር የሀይማኖት አባት መጥፋቱ ነው፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ሕገ ወጥና ኢሰብአዊ ድርጊት ማውገዝ ቢያቅታቸው፣ መንግሥትን ለእርቅና ለሰላም መጠየቅ ቢያስፈራቸው ወዘተ እንዴት ታች ቀበሌና ወረዳ ላይ የሚፈጸሙ እጅግ ዘግናኝ የሆኑ አረመኔያዊ ድርጊቶችን ማውገዝና ጸብ አብርደው እርቅ ለማውረድ መንቀሳቀስ ይቸግራቸዋል፡፡ እነርሱም እንደኛ የነገሩ ወጣኝ ወያኔ መሆኑን ተረድተው የነገሩን ጫፍ ይዘን ሀረጉን ቢመዙት ከወያኔ እጅ ላይ እንደሚወድቁ ገብቷቸው ይሆን፡፡ አሳዛኝ፡፡ ከዚህ የባሰ ምን መክሸፍ አለ፤ ከዚህ በላይስ ምን የሀገር ሞት ይኖራል፡፡

ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ አንድም ለጥቅም እያደሩ፤ሁለትም በወያኔ ፕሮፓጋንዳ እየሰከሩ ለጥፋት የሚሰለፉ መኖራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ወያኔ ለደደቢት ትልሙ ተግባራዊነት እነዚህን በመሳሪያነት በመጠቀም ጊዜና ሁኔታ እየጠበቀ በሚፈጽማቸው ተግባራት ልዩነታችን አሁን ካለውም እየበሳ በመንደር ደረጃ ሊወርድ የመቻሉን ምልክት ነው ያየነው፡፡አማራ ኦሮሞ ትግሬ ሲዳማ ጉራጌ ወዘተ የሚለው ክፍፍል አላንስ ብሎ ትናንት ስልጤ ጉራጌ አይደለሁም ብሎ ተለየ፡፡ ይህን በማሳካት ግንባር ቀደሙን ሚና የተጫወቱት አቶ ሬዲዋን ሁሴን ከተቀዋሚ ፓቲ መሪነት የመንግሥት ባለሥልጣንነትን አገኙ፡፡ ይሄው ዛሬ ደግሞ ቅማንት ከአማራ ልለይ እያለ ነው፡፡ ወያኔ እስካለ ነገም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ይሄው መለያየትና መናቆር ይቀጥላል፡፡

ወያኔዎች የማይወዱትንና ለሥልጣናቸው ጠንቀቅ አድርው የሚያዩትን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን በአንድ ግዜ ለማጥፋት ብዙ ሞክረው አልተሳካላቸውም፡፡ ስለሆነም ለህዝብ ግልጽ ሆኖ በማይታይና ፈጥኖ በማይታወቅ መንገድ ቀስ በቀስ የማመንመንና የማክሰም ስራ እየሰሩ ነው፡፡ እነርሱ የሀገር መሪነቱን ሥልጣን ባጡ ማግስት ኢትዮጵያ አስራ ምናምን ብጥስጣሽ እንድትሆን እየሰሩ ስለመሆኑ እንደ ቅኝ ገዢዎች በየቦታው የሚቀብሩዋቸው ግዜ ጠብቀው የሚፈነዱ ፈንጂዎች እያሳዩን ነው፡፡

ወያኔን ለመገላገል ከሚደረገው ትግል ባልተናነሰ ይህ ሴራ ከዚህ በላይ ሰፍቶና ከፍቶ አንዳይሄድ በጽኑ መስራት ያስፈልጋል፡፡ስለሆነም ጎንደር ውስጥ ያለውን ውጥረት በቅጡ ሳይረዱ የጠቀሙ መስሏቸው ያልሆነ መልእክት በማስተላለፍ “የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል” አይነት ተግባር የፈጸሙና አሁንም በመፈጸም ላይ ያሉ ወገኖች ቆም ብለው በማሰብ ጠብ እንዲበርድ ውጥረት አንዲተነፍስ በሚያስችል ተግባር ላይ ሊሰማሩ ይገባል፡፡ በጉዳይ ላይ የጠለቀ እውቀት ያላቸውና ነገሩን ከመሰረቱ የሚያውቁም የአካባቢው ሕዝብ እውነቱን ተረድቶ ከወያኔ ሴራ በማምለጥ ለጉዳዩን ራሱ ሰላማዊ መፍትሄ የሚያገኝበትን መንግድ ማመላከት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከተለያየ ጥቅምና ፍላጎት አንጻር ነገሩ እንዲከር የሚያደርጉ ሰዎች ካሉም ተለይተው መታወቅና መጋለጥ ይኖርባቸዋል፡፡

ወያኔ ራሱ የጫረውን እሳት ራሱ መልሶ አጥፊ መስሎ የሚቀርበው ነዳጅ እየጨመረ ይበልጥ ለማቀጣጠል ነውና በተለይ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች በጥንቃቄና በንቃት ሊከታተሉት ይገባል፡፡ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ጠያቂው ስለፈለገ ብቻ የሚያገኘው ሌላው ስለተቃወመውም የሚያስቀረው አይደለም፡፡ እንዴት ለምንና በምን ሁኔታ እንደሚጠየቅና ተግባራዊም አንደሚሆን በህግ የሚታወቅ በመሆኑ ባለሙያዎች ይህን ያብራሩ ያስረዱ፡፡

ራስን በራስ የማስተዳደር ቀልብ አማላይ ጥያቄ ትናንት የኢትዮጵያ ተማሪዎችን አማልሎ በውስጥ የተጠነሰሰውን ሴራ ሳይረዱና ከጀርባ ያለው ተልእኮ ሳይገባቸው ለኤርትራ መገንጠል አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ እንዳባቃቸው ሁሉ ዛሬም ብዙዎች ከቅማንት የማንነት ጥያቄ በስተጀርባ ሊኖር የሚችለውን የወያኔ ስውር ደባ ሳያውቁ ለወያኔ ዓላማ ማስፈጸሚያ መሳሪያ አንዳይሆኑ ማንቃት ማትጋትና ከዚህ የሚያልፉትን ማጋለጥ ይገባል፡፡ ሰሞኑን ያየነው ዘግናኝ ግድያ እንዳይቀጥልም ሁሉም በሚችለው መጣር ይኖርበታል፡ስሙን እንጂ ግብሩን   ላልያዙት የሁልም እምነት አባቶችም እስቲ በዚህ ግዜ አንኳን ድምጻችሁ ይስማ የአስታራቂነት ግብራችሁ ይታይ አንበላቸው፡፡

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s