መሬት እግር አለው ይሄዳል እንደሰው—“ – በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የሰው ልጅ ሕይወቱ ከመሬት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው።ለዚህም ነው ሕዝቦች ለም መሬት ለማግኘት በግጭት ሲራኮቱ የቆዩት። ለቅኝ ግዛት ታሪካዊ አነሳስም ዋነኛ ሰበቡ ይኸው የመሬት ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ አገራችን ከወራሪዎች ራሷን በመከላከል ዳር ድንበሯን አስጠብቃ የመኖሯ ትርጉም የዜጎች የመሬት ባላቤትነትዕምነታቸው የፀና ስለነበር እንደሆነ ዕሙን ነው። አያ

ት ቅድመ አያቶቻችን ስለመሬት ያላቸው ግንዛቤ ጥልቀትና ምጥቀት ያለው ነበር። አገር፣ ዳርድንበር፣ መሬትን ለመጠበቅ ማንኛውንም መሰዋዕትነት እየከፈሉ ያለፉትም በዚህ ግንዛቤና ዓላማ ላይ ተመስርተው ነው።ምሳሌያዊ ንግግራቸው ፣ ተረቶቻቸው፣ —–ለግንዛቤአቸውና ለዓላማቸው ምንነት ማጠናከሪያ ማስረጃዎች ናቸው።” ከአንድ ጋን ሙሉ ብር አንድ ጋን ማስቀመጫ መሬት”፣ “ እትብቴ የተቀበረበት” ፣” አፈር ፈጭቼ ውሃ ተረጭቼ ያደግሁበት” ፣ “ በርስትና በሚስት ዋዛ የለም “ ፣ “አፅመርስት” ፣——የሚነገሩት ሁሉ መሠረታዊ ትርጉም አላቸው። ቀደምት መሪዎቻችን ባዕዳን መሬታችንን ብቻ ሳይሆን በጫማቸው አፈራችንን አንኳን ይዘው እንዳይሄዱ አራግፈው መላካቸው ሰለአገር፣ ስለህዝብና ስለመሬት ያላቸውን ቀናዒነት ያሳያል። ለዚህ ነው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የአገራቸው ቁራሽ መሬት በባዕዳን እንዳይደፈር የገንዘብ፣ የጉልበት ፣ የሕይወትም መስዋዕትነት እየከፈሉ ዳርድንበር አስከብረው ለእኛ በክብር ያስተላለፉልን። አዎ አያት ቅድመ አያቶቻችን የአገር ዳር ድንበር ሲደፈር ማቄን ጨርቄን ሳይሉ ፈጥነው ተሰልፈው ተስፋፊና ወራሪን አበራይተው እያሳፈሩ መመለሳቸው ከላይ በመጥቀስ ካስቀመጥናቸው ስናልቦናዊ ቅርሶች የመነጨ ነው። በዚሁ ላይ የመሬት ስሪት በአገሪቱ ወጥነት ባይኖረውም በአንዳንድ አካባቢ በግብር ደረሰኝ ሰንጠረዥ “ አፅመርስት” የሚል ሰፍሮ ይገኝ ነበር። የአገራቸውን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ለከፈሉት ዋጋ የሚሆንና እሳቤው ለትውልድ የመተላለፉን ሂደት እንደሚያሳይ መረዳት አያዳግትም። በግለሰብ ደረጃም ከአያት ከቅድመ አያት በውርስ የተገኝን መሬት መሸጥ መለወጥ እንደነውር ይቆጠር የነበረበት ሁኔታ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። “ ይወለድና አንዳንድ ውልግድግድ መሬት ይሸጣል በወለድ አግድ “አየተባለ መዘባበቻ ይሆን ነበር። ጊዜ መስታወት ሆነና ወያኔ የተባለው ድርጅት የተወላገደ ርዕዮት አንግቦ፣ ስግብግብነትና የአገርና የሕዝብ ክህደት ተጠናውቶት፣ ለታሪካዊ ጠላቶቻችን ወኪል ሆኖ የኢትዮጵያ አካል የሆነው ግዛት ተቆርሶ እንዲወሰድ የሚደልል፣ በኢንቬስትመንትም ስም ዜጎችን አፈናቅሎ መሬት በርካሽ የሚቸበችብ ሆኖ እያየን ነው። ከሱዳን ከሚዋሰነው የአገራችን ክፍል ከጎንደር ጫፍ እስክ ጋምቤላ ድረስ ርዝመቱ 1600 ኪሎ ሚትር ወርዱ በአማካይ 60 ኪሎሜትር በጠቅላላው 96,000 ስኳር ኪሎሜትር ለም መሬት ለሱዳን ሊሰጥ ተዘጋጅቷል። በአጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ሱዳን የእንግሊዝና የኢጣሊያን ቅኝ ግዛት በነበረችበት ወቅት ኢትዮጵያን ያላሰተፈና የአንግሊዝ ወታደርና ካርቶግራፈር በነበረ ግለሰብ ሱዳንን ለመጥቀም የተሰመረ ድንበር እንደሕጋዊ እንዲቆጠር ወያኔ ከሱዳንና ከሌሎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በመሆን ሴራውን እያጠነጠነ ይገኛል። ኢትዮጵያ ቀድሞ በነበረችበት ሁኔታ እንደአገር እንዳትቀጥል ወያኔ ጫካ በነበረበት ወቅት ላበረከተችሁ አስተዋጽኦ ለሱዳን መሬታችን እጅመንሻ ሊሆን መቃረቡን እየሰማን እያየን እንኳን ቀን በፀሐይ ሌሊት በጨረቃ ለተቃውሞና ለመስዋዕትነት መውጣት ሲገባን የዝምታ አዚም በላያችን ነግሷል። ይህ ሁኔታ መለወጥ ይኖርበታል። “ መሬት እግር አለው ይሄዳል እንደሰው ፣ ጀግና ልጅ ተወልዶ እዚያው ካልመለሰው።” እንዲሉ ያሁኑ ትውልድ የዚህ አባባል ባለዕዳ ነው።ይህ ጉዳይ አገር የማዳን እንቅስቃሴ አካል ስለሆነ በይደር የሚቆይ አይደለም።ስለሆነም መምህሩ ከማስተማሩ፣ተማሪው ከደብተሩ፣ ገበሬው ከሞፈሩ፣ ቄሱ ከደብሩ፣ ሰጋጁ ከመስጊዱ፣ ነጋዴው ከንግዱ ላይ ተነስቶ፣ ወታደሩ ዝናሩን አንስቶ በአጠቃላይ ሕዝቡ በአመቸው መንገድ ሁሉ አገሩን ከጠላት ዝርፊያ ለመከላከል ፍልሚያ እንዲገባ በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ጥሪ ያቀርባል። ይህ ትውልድ የኢትዮጵያ መከበሪያ እንጂ ማፈሪያ አይሆንም!! ዳርድንበራችን በደማችን!! መሬታችን የቅርጫ ሥጋ አይደለም!!

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s