ሐውልታቸው ብቻ ሳይሆን ክብራቸውም ይመለስ! (መላኩ አላምረው በድሬቲዩብ)

ታክሲ ውስጥ ነው… ከመርካቶ ወደ 6 ኪሎ እየሄድን። ጊዮርጊስ ልንደርስ ስንል የቅዱሱ አርበኛ ሐውልት ተመልሶ የሚቆምበት ቦታ ታጥሮ አየን። ከተሳፋሪዎች መካከል አንዱ ወጣት… “በጣም ደስ ይላል… የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሊመለስ ነው ማለት ነው” አለ። ሌሎቻንም … “አዎ! አዎ… ቢዘገይም መመለሱ ደስ ይላል…” ተባባል።
አንድ በዕድሜ ገፋ ያሉና አብዛኛው ፀጉራቸው የሸበተ ጢማም ሽማግሌ ግን … ቆጣ ብለው… “ኤዲያ… ሐውልቱ ቢመለስ ምን ዋጋ አለው? ክብሩን ቢመልሱልን ነበር መልካም…” አሉ። ሁላችንም እየተቀባበልን …”የምን ክብር? አልገባንም” … ተባባልን። ሽማግሌውም ይህንን አሉ።
“አያችሁ ልጆቼ… የጀግናው አርበኛ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት በልማት ምክንያት ከመነሳቱ በፊት ክብሩ ተነስቷል።
አናስተውልም እንጅ… የእርሱ ክብር ቀሏል። የተሰዋበት ቦታ ላይ ሐውልቱ ቢቆምም በየዓመቱ ክብሩ ሲታወስ አላየንም። ተረስቷል… በዓመት ውስጥ ስንትና ስንት በዓላት በሚደገስባት ሀገር…. ለአንድ ቀን የአቡነ ጴጥሮስን ክብር በሀገር ደረጃ አስታውሰነው አናውቅም። ከእርሱ ክብር በላይ ምን አለ?
ለሀገር ነፃነት ሲሉ ራስን ለጥይት ሰጥቶ ለትውልድ ነፃና አልገዛም ባይ ምድርን ከማውረስ በላይ ለሀገሩ ጀብዶ የሠራ ማን አለ? ባጠቃላይ የአድዋ ጀግኖችን ጨምሮ… የአርበኞቻችን ክብር ተረስቷል። ሐውልታቸው መቆሙ መልካም ሆኖ… ክብራቸውም በትውልዱ ልብ በክብር ሊቆም ይገባል። ክብራቸውን ረስቶ ሐውልት ቢያቆሙ ምን ዋጋ አለው? ሲጀመር ክብራቸውን ቀድመን ባናነሳው ኖሮ… ሐውልታቸውን እንነካካው ነበርን? ኤዲያ… ብዙ አታናግሩኝ … ደህና እደሩ…” ብለው ከታክሲ ወረዱ። ለካስ ንግግራቸው መስጦን ሳናስበው ‘ፌርማታ’ ላይ ደርሰን ኖሯል።
………….. ሽማግሌው አልተሳሳቱም። ቅዱሱን አርበኛ አቡነ ጴጥሮስን ጨምሮ… ለአርበኞቻችን… ለሀገር ጀግኖች የምንሰጠው ክብር ከሄደበት ይመለስ። የተጣመመው ይቃና… የተሸረሸረው ይስተካከል… የጎበጠው ይቃና… ከልባችን ተነቅሎ ከመውጣቱ በፊት… ሁላችንም እንንቃ። ቀስ በቀስ ጀግና የሌለን ባዶ ሀገር… ወደመምሰል እንዳንሄድ።

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s