የሰሞኑ ‹‹የኦሮምያ ግርግር›› ግራ ገብቶኛል – መስፍን ወልደ ማርያም

በሁለት ደረጃ የሚቀርቡ ጥያቄዎች አሉኝ፤–
አንድ፡– ግርግሩ የኦሮምያ ነው? ወይስ የኢትዮጵያ? ወይስ ኦሮምያ ከኢትዮጵያ ተለይቷል?
ሁለት፡– የኢትዮጵያ የመሬት ጉዳይ ኦሮሞዎችን ብቻ የሚመለከት ነው? ወይስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ?

አንደኛ፣ ግልጽ ከሆነው እውነት እንነሣ፤ ኦሮምያ ከኢትዮጵያ አልተለየም፤ ስለዚህም ግርግሩ የኢትዮጵያ ነው እንጂ የኦሮምያ አይደለም፤ ጥንቱኑ ለማጋጨት የተሰጠውን ስያሜ በስምነቱ ከማጽደቅ በላይ ለታቀደው ዓላማ አመቺ መሣሪያ ማድረግ ነው፤ ይህ ደግሞ በቅድሚያ መሸነፍን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ከወያኔ በቀር ደጋፊ ያለው አይመስለኝም፤ ቁርጠኛ ትግል ቁርጠኛ ዓለማና ቁርጠኛ ስልት ያስፈልገዋል፤ ስለዚህም ቁርጠኛ መሪ ያስፈልገዋል፤ የሕመሙን መርዝ እየተጎነጩ ከሕመሙ ፈውስ ለማግኘት አይቻልም፤ ግርግሩ የኦሮሞ ከተባለ ሁለት ውጤቶች ይከተላሉ፤ አንዱ ውጤት ከኦሮሞ በቀር ሌላውን ሕዝብ አያገባውም ማለት ይሆናል፤ ሁለተኛው ውጤት የልየነቱ በላቤቶችና ተፋላሚዎች ኦሮሞዎችና ወያኔዎች ብቻ ናቸው ማለት ነው፤ ይህ ትልቅ አደጋ አለበት፡፡
አደጋው ወደሁለተኛው ጥያቄ ይመራናል፤ ገብቶኝ እነረደሆነ የግርግሩ ምክንያት ሁለት ናቸው፤ አንዱ ከቤት-ንብረት መፈናቀል ነው፤ የዜግነት መብትና መገለጫ የሆነውን መሬት ማጣት ነው፤ ሁለቱም መሰረታዊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነትን የዜግነት መብቶች ሚደፈጥጡ ናቸው፤ ልብ በሉ የኦሮሞን የዜግነት መብቶች ይደፈጥጣል አላልኩም፤ የኢትዮጵያውያንን ሁሉ መሠረታዊ መብቶች የሚደፈጥጥ ነው፤ ይህ የማያጠራጥር እውነት ነው፤ ይህንን ከተቀበልን ጉዳዩ የኦሮሞ ብቻ አይደለም፤ ግርግሩም የኦሮሞ ብቻ አይደለም፡፡
ትልቁ አደጋ ያሁንን ግርግር የኦሮምያ ብቻ ካደረግነው ወደፊት ያው ጉዳይ በሌሎች ጎሣዎች መሀከል ሊነሣ ነው፤ ሌሎች ግርግሮች ሊያስፈልጉ ነው፡፡
ጉዳዩ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሆነ ትግሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ነው፡፡

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s