የዕምነት ቤቶች ምን እየአደረጉ ናቸው? | ቁምላችው መኩሪያ

 
   የዕምነት አባቶች በዕኩይ መሪዎች ምክንያት  ፍትህ ሲጓደል፤ ድሀ ሲበደል እና መንገጋው ሲበትን ብሎም በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ፍጡር ሲገድል፤ ሲሰደድ እና በረሃብ አለንጋ ሲገረፍ  በዳዩን የመገሠፅ  የሞራልም ሆነ የዕምነት ግዴታ አለባቸው።
አሁን ግን በዕምነት ቤቶች አከባቢ ይህ ሴደረግ አይተይም። ይባስ ብሎም ስለ ተበደለ ህዝብ መነገር ፖላቲካ ነው  ወይም ከዕምነት አሥተምህሮት ውጪ ነው አሊያም ሁለቱንም ናቸው በማለት ውኃ የማይቆጥር  ምክንያቶች ሲደረድሩይ ይደመጠሉ። 
በትልቁ መጽሐፈችን በመጽሐፍ ቅዱስ ግን (እርግጠኛ ነኝ በቅዱስ ቁራኑም ቢሆን ሰለ ፍትህ እና ስለ ሰው ልጆች ደህንነት ሳያወሳ አቀይርም  ብዬ አምናለሁ)  የሚከተሉት ተፅፈዋል በዕምነተት ቤቶችም ተሰብካዋል።

 

    • ሙሴ፡ ፋርዖንን ገስፆል ህዝብንም ከባርነት አውጥቷል።

 

    • ነብዩ ናታን፡   ንጉሥ ደዊትን ግስጾል፡ ደዊትም ዕንባ አውጥቶ አልቅሶል።

 

    • ቅዱስ ዮሐንስ፡ ሔሮዶስን ገሥጾል።

 

    • የመይሞተው እየሱስ ክርስቶስ የሞተው የሰውን ልጅ ከባርነት እና ከመካራ ለመታደግ ነው።ምሣሌነቱም የሰው ልጅ በአርዕየ ክርስቶሰ ለተፈጠረው ወንድሙ  በመካራ ቀን ከጎኑ ቁሞ መስዋዕት መክፈል እንደአለበት ለማሳየት ነው።

 

    • አባታችን ብፁ ወቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ መንገውን ሊበትን የመጠን ወራሪ በጎቼን አትንካብኝ ብለው ደረታቸውን ለአሩር ስጠዎል።አሁን ግን አባቶቻችን ያቋሙላቸው ሀውልት የትም ሲጣል ዝምታን መርጠናል።

 

 አባቶቼ ሆይ!!፦ እንደ እናተ አሰተሳሰብ ቢሆን እኒህ ሁሉ ከለይ የተዘረዘሩት ፖላቲካኞች ናቸው ማለት ነው ? የሠሩት ሥራስ ከዕምነት አሥተምህሮ ውጪ ነው ማለት ነው? ለእናንተ ፖላቲካ ማለት ምን ማለት ይሆን? ፖላቲካኞች እኳ እያሉ ያሉት፦ ፍትህ ተጓደለ፡ ድሃ ተበደለ፡ ሀገር በዘውግ ተሸነሸነ፡ ህዝብ በራሃብ አለንጋ ተገረፈ። ወገን ተሰደደ ነው። ይህ የዕምነት ቤቶች ሥራ ከልሆነ ሥራችሁ ንግድ እና ውትድርና  ነው ማለት ነው?
  
የዕምነት አስተምህሮትስ ቢሆን ጥሬ ቃሉ  እኳ የሚለው  ድሓ ሲበደል ጩህ፡ ባልንጃራህን እንደ ራስህ ውደድ ነው። ታዲያ ሀገራችን  ኢትዮጵያ እንዲህ ስታናባ ህዝቦቾ በጥይት እና በራሃብ ሲቆሉ ካላአዘነችሁ ችግራቸውን ካልተነገረችሁ እራኝነቱ እና ባልንጀራን እንድ ራስ መውደድ ምኑ ላይ ነው?  በዚህ አጋጣሚ በስደት ለይ ያለውን የኢትዮጵያ ህጋዊ ሲናዶስ እና ወሺንግተን ዲሲ ያለውን ፈርስት ሂጅራን የኢትዮጵያ እስልምና ምህበርን    አመሰግናለሁ። በሥሩ የሚገኙት አድባራት እና ካህናት እንዲሁም አጥባቂ ምዕመናን ግን ዝምታቸውን መሥበር አለባቸው እላለሁ። የእስልምናውም ቢሆን እንዲሁ።
 
   በርግጥ ሀገርን በዬፊነው የሚያገለግሎ አራት በአዘውንት ዘንድ “ቀአነተ” በሚል ምህፀረ ቃል የሚተውቁ መሰረተዊ አውታሮች ማለትም” ቀዳሽ(ኃይማኖት)፡ አራሽ(አምራች)፡ ነጋሽ(አስታዳዳሪ)፡ ተኮሽ(ወተደር)”   የስፈልጓታል። ይህ ማለት ግን መነኩሴውም ሆኑ ጰጰሱ፡ ሼኪውም ሆኑ ቄሱ፡  ዘመሪውም ሆኑ ፓስተሩ ሀጂውም ሆነ ደብታራው በፖላቲካ እና  በእስተምህሮ ቆፈን ተሸብበው በዝምታ ይቆዝሙ ማለት አይደለም።  ኃይማኖት መልኩን ሲቀይር ሀገርም ደብዛው ሲጠፋ ህሊናቸውን ሊጎሽማቸው ይገባል።
  ሌላው አሳዛኙ “ሀገራችን በሰማይ ነው ስለ ምድር አተስቡ” የሚባለው መፈክር ነው። በርግጥ ስለ ሰማይ ቤተችን ማሰቡ ጥሩ ነው ። ዕውነተኝውን የሰማይ ቤት የምናገኘው እኳ በምድር ለይ ሆነን በሰረነው በጎ ሥራ ነው። በምድር ለይ ሆነን  የወገንን ሥቃይ ለመታደግ  ለባረከትነው  ልቅሶነው።በምድር ለይ ሆነን ወገንን ከባርነት እና  ከሞት ለመታደግ ለደረግነው መልካም ሥራ ነው። 
  ይህንን ምድር ሆነን ካልሰረን የትኘው ሰማይ ነው ሀገራችን የሚሆነው?
    ያ የሰማዩ መንግሥት(ቦታ) እኳ  እንደ ወየኔ መንግሥት በዘመድ ወይም በአገር ልጅነት ወይም እንደ ኮንደሚኒያም በማጎብደድ አይተደልም። እባካችሁ ወገኖቼ ዕምነትን በትክክል እንተርጉም።
  ወገኖቼ ሆይ!!፦ ሀገር በመንታ መንገድ ለይ ነት። ወየኔ በፈጠርው ጧስ ወገን በጥይት እና በራሃብ አላንጋ እዬተገረፈ ነው። መሬት እዬተቆረሰ ለሱደን፤ ለሰውዲ ዓረቢያ፧ ለቻይና፤ ለህንድ፤ ለግብፅ፤ ለኴያት እና ለቤልጂያም እዬተደለ ነው። ሀገሬቷን የዘር ፖላቲካ እዬአናዋጣት ነው።ኢትዮጵያን የመሰለች ትልቅ ሀገር ወደብ አልባ ሆናለች። ውርደት እና ራሃብ መለዮችን ሆናዋል። ዝም ብለን ከአየናቸው እነዚህ የጣሊያን ቡችሎች ሀገረችንን በጥቂት ጊዜ ውስጥ ያጠፎታል።  ስሞንም ይቀይሮታሎ።
 የትግራይ ወጣቶች ሆይ!!  ከሌሎች ኢትዮጵያውኖች ጎን ቁሙ። ራሳችሁን ከታሪክ ተጠየቂነት አድኑ። የትግራይ አባት እና እናቶች ሆይ!! ልጆቻችሁን ሀይ በሎቸው። ከአብራካችሁ የወጡ ልጆቻችሁ ሀገር አያጥፉ፡ ወገንም አይጨርሱ ነው።
 
አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ!!!
“ኢትዮጵያ ታበፅህ እደዊሃ ሀበ ኢግዚአብሔር”!!!!!!
posted by tgi flate
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s