የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የልሳኑ ዋና አዘጋጅ ተጨማሪ ጊዜ ተጠየቀባቸው

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከ28 ቀናት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የምክር ቤት አባል አቶ ዮናታን ተስፋዬና የፓርቲው ልሳን ‹‹ነገረ ኢትዮጵያ›› ዋና አዘጋጅ አቶ ጌታቸው ሺፈራው፣ ለሁለተኛ ጊዜ የ28 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው፡፡
አቶ ዮናታን ጥር 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርቦ ነበር፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በተጠርጣሪው ላይ የቴክኒክ ማስረጃ መሰብሰብና ግብረ አበሮቹን መያዝ እንደሚቀረው ለፍርድ ቤቱ በማመልከት፣ ተጨማሪ 28 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡
የተጠርጣሪው ጠበቃም ለፍርድ ቤቱ እንዳመለከቱት፣ መርማሪ ቡድኑ ላለፉት በርካታ ቀናት ምርመራውን ማጠናቀቅ ይችል ነበር፡፡ በመሆኑም ደንበኛቸው አድራሻ ያለው በመሆኑ በዋስ ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል ጠይቀው ነበር፡፡ አቶ ዮናታንም ለፍርድ ቤቱ እንዳመለከተው ቤተሰብም ሆነ ጠበቃ ሊጠይቀው አልቻለም፡፡ የጤና እክል ገጥሞት እንዲታከም ቢጠይቅም መከልከሉን ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ አቶ ዮናታን በቤተሰቡና በጠበቆቹ እንዲጐበኝ፣ እንዲሁም ሕክምናም እንዲያገኝ እንዲያደርግ ለመርማሪ ቡድኑ አሳውቋል፡፡ ጠበቃው የጠየቁትን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ፣ መርማሪ ቡድኑ የጠየቀውን የ28 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዶ፣ ለየካቲት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ የፓርቲው ልሳን ‹‹ነገረ ኢትዮጵያ›› አዘጋጅ አቶ ጌታቸው ሽፈራው ላይ መርማሪ ቡድኑ ተመሳሳይ ሥራ እንደሚቀረው ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ፣ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቅዶለት ለየካቲት 11 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s