መፅሐፈ ሄኖክ፣

በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተፃፈው አርባዓቱ ወንጌል፣

አፄ ቴዎድሮስ ለእንግሊዟ ንግስት ቪክቶሪያ የፃፉት ደብዳቤ፣

የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር የሚተነትነው “ባሕረ ሃሣብ” የተሰኘው መፅሐፍ እና

ለ131 በሽታዎች መድሐኒት ሊሆኑ የሚችሉ የዕፅዋት ዝርዝር የያዘው “ዕፀ ደብዳቤ” መጽሐፍ

ቴምብር ተሰርቶላቸው ገበያ ላይ ዋሉ፡፡

ቴምብር ከተሰራላቸው ከነዚህ አምስት መፃህፍት መካከል ሦስቱ በዩኔስኮ በአለም የፅሁፍ ቅርስነት የተመዘገቡ ናቸው፡፡

ቴምብሮቹ የታተሙት የኢትዮጵያ ቤተ-መፃህፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመት ምክንያት ሆኖ ነው፡፡

ቴምብር የታተመላቸው መፅሐፍትም መፅሐፈ ሄኖክ፣ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተፃፈው አርባዓቱ ወንጌል፣ አፄ ቴዎድሮስ ለእንግሊዟ ንግስት ቪክቶሪያ የፃፉት ደብዳቤ፣ የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር የሚተነትነው ባህረ ሃሣብ መፅሐፍ እና ለ131 በሽታዎች መድሐኒት ሊሆኑ የሚችሉ የዕፅዋት ዝርዝር የያዘ ዕፀ ደብዳቤ የተባሉ መፅሐፍት ናቸው፡፡

የታተሙት ቴምብሮች ብዛት አንድ መቶ ሺህ ነው የተባለ ሲሆን የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የመሸጫ ዋጋ አውጥቶላቸው ከዛሬ ጀምሮ ገበያ ላይ ውሏል ተብሏል፡፡

የቴምብሮቹ መታተም መፅሐፍቶቹን በኢትዮጵያም በአለምም በማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ሲባል በበዓሉ ላይ ሰምተናል፡፡

ብሔራዊ ቤተ-መፅሕህትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ ከተመሰረተበት 1936 ጀምሮ ከ430 ሺህ በላይ ለመረጃ ምንጭ የሚሆኑ ቅርሶችን ማሰባሰቡንና ማደራጀቱን ተናግሯል፡፡

ይሁን እንጂ እንዳለው የፅሁፍና ሌሎች የመረጃ ምንጮች ለጥናትና ምርምር በማዋሉ በኩል ገና ብዙ የሚቀሩኝ ሥራዎችም አሉኝ ብሏል፡፡

በ2006 ዓ.ም 70ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ማክበር የነበረበት ቤተ-መፅሐፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ ለበዓሉ ያሳተማቸው ቴምብሮች ህትመት ስለዘገዩበት በአንድ ዓመት ዘግይቶ ዛሬ እያከበረ ይገኛል፡፡

posted tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s